Pages

Friday, August 28, 2015

እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ (ምሳሌ 8፡22)

በይብራይስጥ የይሖዋ ምስክሮች ራስ ምታት ምሳ 8:22 " የመንገዱ መጀመሪያ "

አንባቢያን በይብራይስጥ ማለቴን አስተውሉ፡፡ ብሉይ ኪዳን መጀመሪ የተጻፈው በይብራይስጥ ቋንቋ ነው፡፡ ሌሎቹ ሁሉ ትርጉም ናቸው፡፡ ምናልባትም የመጀመሪው ትርጉም በግሪክ ቋንቋ የተጻፈው የሰባዎቹ ልቃውንት ትርጉም የሚባለው ነው፡፡ ይህ ትርጉም የተሰራው በግሪኮች ቅኝ ግዛት እና ወረራ ምክንየት እስራኤላዊያን በየአገሩ ተበትነው ስለነበር እና የግሪክ ቋንቋ (ጽርዕ) ዛሬ እንገሊዝኛ በየ አገሩ እንደሚወራው በሰፊው የግሪክ ግዛት ልክ አቴንሰ የሚወራውን የህል ይወራ ነበር፡፡ መሆኑም የእስራኤል ትውልዶች ቋንቋቸው መናገር እያቃታቸው ሲመጣ ይህ የግሪክ ትርጉም ተሰራ፡፡ የግሪክ ቋንቋ ከክርስቶስ ልደት በኋላ እንኳን በሰፊው በአገልግሎት ላይ ነበረ፤ የወቅቱ የቤተክርስቲያን አባቶችም ብዙ ጽሁፎቻቸውን የጻፉት በግሪክ ነበር፣ እንዲሁም አዲስ ኪዳን መጀመሪያ በግሪክ ነበር የተጻፈው፡፡ በወቅቱም በቋንቋው አገልግሎት ስፋት የተነሳ ፣ በሰፊው በአገልግሎት ላይ ይውል የነበረው ጠብሉይ ኪዳን መጽሃፍ ከይብራይስጡ ይልቅ ፣ ትርጉም የሆነው የግሪኩ የሰባዎቹ ልቃውንት መጽሓፍ ነበር፡፡ እነ አርዮስም ሲያነሱ ለነበሩት የክህደት ጥያቄዎች ይጠቀሙ የነበረው ይሄንኑ ትርጉም ነበር፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብዙ አርዮሳዊያን እየሱስ ፍጡር ነው ለማት በብዛት የሚጠቀሙት የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ምሳ 8፡22 ላይ ያለውን ነው፡፡ ‹‹ እግዚኣብሄር የመንገዱ መጀመሪያ ….?››

የትርጉሞች ዳሰሳ፡-


የዚህ ሀይላቃል ቁልፉ ቦታ ከላይ በ… የተውኩት ነው፡፡ በአማርኛ ትርጉሞች ‹‹አደረገኝ 1962 እና1980›› ፤ቀድሞ ይሖዋ ምስክሮች ይጠቀሙት የነበረው መደበኛ ትርጉም ደግሞ ‹‹አድርጎ አመጣኝ›› ሲል የይሖዋ ምስክሮች የራሳቸው ትርጉም ደግሞ ‹‹ አድርጎ ፈጠረኝ ›› ይላል፡፡ የመጀመሪው ትርጉም ከላይ እንደጠቀስኩት የግሪኩ ሰባዎቹ ልቃውንት ትርጉም ነው፡፡ በዚህ ትርጉም ἔκτισέν (ፈጠረኝ ) ተብሎ ነው የተተረጎመው፡፡ ብዙ አርዮሳዊያንም ይህን ትርጉም እየጠቀሱ ነበር የሚከራከሩት፤ አባቶችም ቢሆኑ ይሄንኑ ትርጉም በመጠቀም ነበር መልስ ለመስጠት ይጥሩ የነበረው፡፡ ጥቂት አባቶች ግን ወደ መሰረታዊው የይብራይስጥ ትርጉም ሲሄዱ ነገሩ ለአርዮሳዊያን እንዳሰቡት አልጋ ባልጋ አለመሆኑን ተረዱ፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ቅዱስ ባሲሊዮስ (St.Basil) አንዳንድ ይብራይስጡን መጽሃፍ ያጠኑ ‹‹ ἔκτισέν ሳይሆን  έκτήσατό με መሆን እንዳለበት ደርሰውበታል ፤ ይህ ደግሞ ፍጥረታዊ ነው ብለው ለሚክዱት አርሳዊያን ትልቅ እንቅፋት ነው ›› በማለት የገለጹት፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ባሲሊዮስ ይህን ክፍል ከዘፈ 4፡1 ጋር አመሳክረውታል፡፡

ጥቂት ዳሰሳ ስለ ጥበብ መጽሃፈ ምሳሌ 8፡-


ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል ቃል በቃል እየሱስ ብሎ ወይም የእግዚኣብሄር ልጅ ብሎ አይናገርም፤ ይልቁንስ ጥበብን በሰውኛ ዘይቤ ይገልጻል፡፡ለምሳሌ በምሳ 7፡3 ላይ ጥበብ እህት ተብላለች፡፡እየሱስ ግን ተባዕታዊ ፆታ ነዉ፡፡ ነገር ግን  እየሱስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡24 ላይ “እያሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ” መባሉን ምክንያት በማድረግ ፤ምሳ 8፡22 እየሱስ መጀመሪያ ስለመፈጠሩ ያወራል ይላሉ አርዮሳዊያን፤ምክንያቱም እነሱ እየሱስ ፍጡር ነው የሚል አስቀድሞ በአዕምሮኣቸው አለ፡፡እዚህ ላይ ሁሉም ክርስቲያን ማስተዋል የለበት እየሱስ በእግዚኣብሄር ጥበብ ተመሰለ እንጂ ምሳ8፡22 የሚያወራዉ ስለ አምላክ ጥብብ ነዉ፡፡ የእየሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ መባልን፤ይህን የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል እንዳለ ከተረዳን በኋላ አያይዘን እንመለከታለን፡፡ 

ቀናኒ ትርጉሙ ምንድን ነዉ?


በዚህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል በተለያየ መንገድ የተተረጎመው የይብራይስጥ ቃል ‹‹ቀናኒ›› የሚል ነው፡፡ ቡርኔይ የሚባል ምሁር በዚህ ቃል (ቀናኒ) ትርጉም እና በምሳሌ 8፡22 ትርጉም ላይ ሰፊ ምርምር አድረጓል፡፡ጥናቱንም The Journal of Theological Studies ላይ አሳትሟል፡፡ ይህም ሰዉ (ቡርኔይ) ይህ የአይሁድ ቃል (ቀናኒ) የተለያዩ ትርጉሞች እንዳሉት ከመጽሓፍ ቅዱስ በመጥቀስ ያስረዳል፡፡ከነዚህም ትርጉሞች ዉስጥ መፍጠር (create) እና መዉለድ (beget) የሚሉት ይገኛሉ፡፡ በመዝ 139፡13 አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በለበት ጊዜ ፈጥረሃል ተብሉ የተተረጎመዉ ይሀዉ ቀናኒ የሚለዉ ቃል ነዉ፡፡ በዘፍ 4፡1 ላይ ሄዋን ቀኤልን ስለመዉለድዋ በተናገረች ጊዜ ቀናኒ የሚለዉን ቃል ተጠቅማለች፡፡ አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም። ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ (ቀናይተ) አለች።(ዘፍ 4፡1) የሄዋን የመጀመሪያ ለጅም ስም ቃየን የሚለዉ ከዚህ ቃል ጋር የተያያዘ ነዉ፡፡ ስለዚህ ከላይ እንደምንረዳው ቀናኒ የሚለው የይብራይስጥ ቃል ቢያንስ ፈጠረኝ ወይም ወለደኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ በምሳ 8፡22 ላይ የተኛውን ትርጉም ነው የያዘው?

ምሳ 8፡22 የቀናኒ ትርጉም መዉለድ ነዉ ወይስ መፍጠር ነዉ?


የዚህ መልስ በግል ወይም ሀይማኖታዊ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆን የለበትም ፡፡ ብዙ ትርጉም ያለውን ቃል ትክክለኛ ትርጉሙን ማወቅ የሚቻለው በዙሪያው ካሉት ሀሳቦች ነው፡፡ ለምሳሌ በዘፍ 4፡1 ላይ ይህ ቃል ስለመውለድ ስለመሆነ በዙሪያው ያሉት ቃላት ጸነሰች ወለደች የሚሉት ቃላት ያሳያሉ፡፡ ይህም ምሁር የዚህን ቃል(ቀናኒ) ትርጉም በዚህ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል (ምሳ 8፡22) ዉስጥ ከሁለቱ የተኛዉ እንደሆነ ለመለየት የሚቀጥሉትን አንቀጾች ዉስጥ ያሉትን ፍንጮች ማየት ያስፈልጋል ይላል፡፡ለዚህም በቁጥር 24፣25 ‹‹ሆላልቲ›› የሚሉትን የይብራይስጥ ቃላት ትርጉም የስቀምጣል፡፡ በምሳሌ 8፡24-25 ላይ ያለዉ ሆላልቲ የሚለዉ ቃል ደግሞ ያለጥርጥር  ‹‹መዉለድን›› ይገልጻል ይላል፡፡ ይህን ቃል ከላይ የጠቀስኳቸው ትርጉሞች በሙሉ ‹‹ተወለድኩ›› ብለው ነው የተረጎሙት፤ የይሖዋ ምስክሮችን ጨምሮ፡፡ ቡርኔም እንዲህ በማለት ያብራራል፡-

“in  v - 24, 25 (stage 3) חוֹלָ֑לְתִּי (ሆላልቲ) means ' I was brought forth with travail' (birth),” C:F.BurneyChrist as the Apex of Creation (Prov. viii 22, Col. i 15-18, Rev. iii 14.)” The Journal of Theological Studies page 165 (አማርኛዉ የኔ ነዉ)

በቁጥር 25 (ሆላለቲ የሚለዉ የይብራይስጥ ቃል) ያለጥርጥ መዉለድ ማለት ነዉ ካለ በኋላ፣በዚህ ምክንያት በቁጥር 22 ያለዉ ቀናኒ የሚለዉ የይብራይስጥ ቃል ትርጉም ፈጠረኝ ሳይሆን ወለደኝ ነዉ ይላል፡፡  

“the inference is obvious that the figure described in v. 22 by (stage 1) קָ֭נָנִי (ቀናኒ)is 'beget me' (act of procreation).” ibd: page 165 (አማርኛዉ የኔ ነዉ)

 ነገር ግን ፈጠረኝ ወይም ተመሳሳይ ትርጉም ለዚህ ቃል (ምሳ 8፡22 ቀናኒ) ለመስጠት የመረጡት አካላት ከግል እና ሀይማኖታዊ ፍላጎታቸዉ ዉጪ ምንም ምክንያት ሊኖራቸዉ አይችልም፣ምክንያቱም ይህ ቃል ሁለቱንም (ፈጠረኝም ወይም ወለደኝም) ትርጉሞች ስላሉት ነዉ ፡፡ እንደ አገባቡ ግን ፈጠረኝ የሚለው ትርጉም ድጋፍ የለውም፡፡

ቡርኔይ “in the beginning “የሚለዉም ስህተት ነዉ ይላል፡፡ በአማርኛዉ ደግሞ ‹‹በመንገዱ መጀመሪ››ያ የሚለዉ ስህተት ነዉ ማለቱ ነዉ፡፡ ምክንያቱም “in” የሚለዉን ቃል የሚወክለዉ  (በ) የሚባለዉ የይብራይስጥ ቃል (ዘፍጥርት 1፡1 መጀመሪያ ላይ ያለዉ ማለት ነዉ) በምሳሌ 8፡22 ላይ የለም ይላል፡፡ 

2
Yah·weh   22
יְֽהוָ֗ה   22
Yahweh   22
N‑proper‑ms   22
7069 [e]
qā·nā·nî
קָ֭נָנִי
possessed me
V‑Qal‑Perf‑3ms | 1cs
7225 [e]
rê·šîṯ
רֵאשִׁ֣ית
at the beginning
N‑fsc
 
 

 
 
 1870 [e]
dar·kōw;
דַּרְכּ֑וֹ
of His way
N‑csc | 3ms
6924 [e]
qe·ḏem
קֶ֖דֶם
Before
N‑msc
4659 [e]
mip̄·‘ā·lāw
מִפְעָלָ֣יו
His works
N‑mpc | 3ms














*ይብራይስጥ ከቀኝ ወደ ግራ ነው የሚነበበው፡፡

ስለዚህ እንደ የይብራይስጡ በኩረ ጽሁፍ ምሳ8፡22፣ጥበብ የእግዚኣብሄር ስራ (ፍጥረት) መጀመሪያ ነች፡፡

የመንገዱ መጀመሪያ ማለትስ ምን ማለት ነው


መንገድ የተባለው ፍጠረትታት መሆናቸውን እዚያው ‹‹ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ›› መጀመሪያ ከማለቱም በላይ በተከታታይ የአምላክን ፍጥረታት ይተነትናል፡፡ እናም መንግድ የተባለው ፍጥረታት ናቸው፡፡ እናም ጥበብ ‹‹የእግዚኣብሄር ፍጥረታት መጀመሪያ ›› ተብላለች በዚህ ክፍል፡፡ ማስተዋል ያለብን ጥበብ ‹‹በእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ›› አልተባለችም፡፡ ‹በ› ቅጥያ ትልቅ ትርጉም ይሰጣል፡፡ በፍጥረት መጀመሪያ ማለት ፤ ከፍጥረታት ውስጥ መጀመሪያ ማለት ነው፤ ነገር ግን እንዲህ አልተባለም፡፡ የእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት የእግዚኣብሄር ፍጥረታት ምንጭ ወይም አስገኚ ማለት ነው፡፡ እግዚኣብሄር ሁሉንም ፍጥረታት የፈጠረዉ በጥበቡ እንደሆነ እዚሁ ምሳ 8፡30 ላይ ‹‹ዋና ሠራተኛ ነበርሁ›› ከሚለው እንረዳለን፡፡ ዋና ሰራተኛ ማለት የለጥበብ ምንም ነገር እንዳልተደረገ፤ ወይም አምላክ ሁሉንም የፈጠረው በጥበቡ እንደሆነ መግለጹ ነው፡፡ እንዲሁም በመዝ 104:24 ላይ ‹‹ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ›› በማለት አምላክ ሁሉን ያረገው ወይም የፈጠረው በጥበቡ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በመሆኑም እዚህ (ምሳ 8 ላይ) ጥበብ እንደ እግዚኣብሄር ፍጥረታት ምንጭነት/አስገኚነት ተነገረች እንጂ እንደ የመጀመሪያዋ ፍጥረት አይደለችም፡፡ይህም የአባይ መጀመሪያ/ምንጭ ኢትዮጲያ ነች እንደማለት ነዉ፡፡  በመሆኑም ይህ የይብራይስጥ የቋንቋ ምሁር የዚህ ምሳ 8፡22 ትርጉም እንደሚከተለዉ መሆን ኣለበት ይላል፡፡
“The Lord begat me as the beginning of His way, The antecedent of His works, of old.” ibd: page 168 (አማርኛዉ የኔ ነዉ)

ይህም በአማርኛ እንደሚከተለዉ ሊተረጎም ይችላል፡፡ “ጌታ የመንገዱን መጀመሪያ ወለደኝ፣የቀድሞ ስራዉ መጀመሪያ፡፡”

ስለዚህ ከመሰረታዊው ቋንቋ ነው የተረጎምነው የሚሉት የይሖዋ ምስክሮች ያለምንም ምክንያት በገዛ ፍላጎታቸዉ ፈጠረኝ ብለዉ ተርጉመዋል፡፡ የይብራይስጡ ማሳሌ 8፡22 የጥብብን መፈጠር አያስተምርም፡፡ አዚህ ላይ እያሱስ በጥበብ ተመሰለ እንጂ ጥበብ በእያሱ እንዳልተመሰለ መረዳት ኣለብን፡፡ስለዚህ ምሳሌ 8፡22ትን ስናነብ ጥበብን አስመልክተን ነዉ፡፡እግዚኣብሄር ሁሉንም ነገር የሰራዉ በጥበብ ነዉ፡

የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፡፡


አብዛኞቹ የአማርኛ መጽሃፍ ቅዱስ ትርጉሞች ቀናኒ የሚለዉን የይብራይስጥ ቃል አደረገኝ ብለዉ ትረጎመዋል፡፡ይህ በእርግጥ አደረገኝ ሲል በመዉለድ ይሁን በመፍጠር ግልጽ አይደለም፡፡ነገር ግን እነዚሁ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉሞች በቀጣይ ያሉትን ሆላልቲ የሚሉትን በትክክልም ተወለድኩ ብለዉ ስለሚተረጉሙ ምሳ 8፡22 ስለ ጥብብ መወለድ እንደሆነ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ስለዚህ የሀሳብ ግጭት የለበትም ለማለት ያስችላል፡፡ ይልቁንም በይብራይስጡ ያለውን አይነት ግርታ በውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡

ምሳ 8፡22-25
22፤ እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥  በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ። 23፤ ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ፤ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ።  24፤ ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ ተወለድሁ፥  የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ።  25፤ ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥  ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድሁ

ታዲያ የይሖዋ ምስክሮች ለምን ፈጠለኝ ብለዉ ተረጎሙ?


ትክክለኛዉን ትምህርት የማይታገሱበት ጊዜ ይመጣልና፤ከዚህ ይልቅ ከራሳቸዉ ፍላጎት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ጆሯቸዉን እንዲኮረኩሩላቸዉ በዙሪያቸዉ አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ፡፡2ኛ ጢሞ 4፡3 አአት (የይሆዋ ምስክሮች ትርጉም)

ምሳ 8፡22 እንደ ይሖዋ ምስክሮች ጥበብ ተፈጠርኩ ኣለች ስንል ምን ማለታችን ነዉ?


በመጀመሪያ እዚህ ላይ ምሳሌ 8 የሚያወራው ስለ ጥበብ መሆኑን ማስተዋል ኣለብን፡፡ ይህ ክፍል ሙሉ በሙሉ የሚያወራዉ ስለ ጥበብ በሰዉኛ ዘይቤ ነዉ፡፡ ኣንድም ቦታ እየሱስ ብሉ አይጠራም፡፡ ይህን ስል እየሱስ በእግዚኣብሄር ጥበብ አልተመሰለም ማለቴ አይደልም፡፡ ነገር ግን ስለጥበብ የተባለዉን በትክክል ከተረዳን በኋላ እየሱስ ለምን በእግዚአር ጥበብ እንደተመሰለ ማጥናት ኣለብን፡፡ ስለዚህ እዚህ ጋር (ምሳ 8፡22) ተፈጠረም ተወለደም ስንል በመጀመሪያ ጥበብን ነዉ እንጂ እየሱስን አይደለም፡፡ በእየሱስ ላይ ባለን አስተምሮ ተጽእኖም ይሁን በሌላ፣ጥበብ ተፈጠረች ብለን ሰንተረጉም የሚያስከተለዉን ክህደት እንደሚከተለዉ እናያለን፡፡

እዚህ ምሳ8፡22 ላይ ጥበብ ተፈጥራለች (በእግዚኣብሄር) ካልን፣ጥበብ ያለነበረችበት ጊዜ ነበር ስለሚሆን፣እግዚኣብሄር የጥበብ ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ምሳ8፡22 ላይ ጥበብ ተፈጥራለች ካልን፣ አምላክ በፊት ለዘላለም ጥበብ አልነበረዉም ማለት ነዉ፡፡ ይህም እግዚኣብሄር ከጥበብ አልባነት ወደ ጥበበኛነት ተለወጠ ማለት ነዉ፡፡ እኔ እግዚኣብሄር አልለወጥም እንደሚል አስተዉሉ (ት.ሚልክያስ 3፡6) ፡፡እግዚኣብሄር ደግሞ ሁሉንም ነገር በጥበብ ስለሰራ፣ጥበብ ለመፍጠር ደግሞ ጥበብ ስለሚያስፈልገዉ ራስዋ ጥበብ ልትፈጠር አትችልም፣እገዚኣብሄርም የሌለችዉን ጥበብ ባለቤት መሆን ስለማይችል፣እግዚኣብሄር ጥበበኛ ሳይሆን ይቀር ነበር ማለት ነዉ፡፡ስለዚህ ጥበብ ተፈጠረች ማለት እግዚኣብሄር ጥበበኛ አልነበረም የሚል ክህደት ያስከትላል፡፡ይህንንም ብዙዎች ያስተዋሉት አይመስልም፡፡ ‹‹<<ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ ›› የሚለዉ ይህን ነዉ፡፡

ጥበብ ተወለድኩ ማለትዋ ምን ማለት ነዉ?


እዚህ ምሳ8፡22 ላይ ጥበብ ተወለደች (በእግዚኣብሄር) ካልን፣የጥበብ ዘላለማዊነት ወለድኩሽ ባላት አካል ባህሪ ላይ ይመሰረታል፡፡ ጥበብን ወለድኩሽ ያለዉ አካል ዘላለማዊ ካልሆነ (የተፈጠረ ከሆነ) ከሱ የተወለደችዉም ጥበብ ዘላለማዊ አትሆንም (የተፈጠረች ትሆናለች)፡፡ ነገር ግን ጥበብን ወለድኩሽ ያለዉ አካል ዘላለማዊ ከሆነ (ያልተፈጠረ ከሆነ) ከሱ የተወለደችዉም ጥበብ ዘላለማዊ ትሆናለች (ያልተፈጠረች ትሆናለች)፡፡ስለዚህ በምሳ8፡22 መሰረት ጥብብ ዘላለማዊ እና ያልተፈጠረች ከመሆንዋም በተጨማሪ እግዚኣብሄር እኔ እግዚኣብሄር አልለወጥም ባለዉ መሰረት እግዚኣብሄር ከዘላለም እስከ ዘላለም በባህሪዉ ጥበበኛ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
ለምሳሌ ኣንድ አካል ከሰዉ ተወለድኩ ካለ የሰዉን ባህሪ ይላበሳል ማለት ነዉ፡፡በመሆኑም ወለደኝ ያለዉ ሰዉ ዘላለማዊ ካልሆነ ከሰዉ ተወለድኩ ያለዉም ዘላለማዊ አይሆንም ማት ነዉ፡፡ ስለዚህ ኣንድ አካል ከተፈጠረ ነገር ተወለድኩ ካለ እሱ ራሱ ፍጡር መሆኑን መናገሩን መረዳት ኣለብን ፡፡
ስለዚህ በምሳ8፡22 ላይ ጥብብ ከዘላለማዊዉ አምላክ ተወለድኩ በማለት ዘላለማዊነትዋን ትናገራለች፡፡-እግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ በማለት ደግሞ የፍጥረታት ምንጭ መሆንዋን ትገልጻለች፡፡
ጥበብ የመንገዱ መጀመሪያ ነች እንጂ መንገዱ መጀመሪያ (ፍጥረት) አይደለችም፡፡ስለዚህ ጥበብ በ-እግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ሳትሆን የ-እግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ናት እንደ ምሳ8፡22፡... ሀሳብ፡፡ ጥበብም ከዘላለማዊው አምላክ ተወለድኩ በማለት ዘላለማዊነትዋን ትናገራለች፡፡ይህም እኔ እግዚኣብሄር አልለወጥም እንዳለዉ እግዚኣብሄር ከዘላለም እስከዘላለም በባህሪዉ ጥበበኛ መሄኑን ይገልፃል፡፡ስለዚህ ጥበብ የእግዚኣብሄር የመጀመሪያ ፍጥረት አይደለችም፡፡ይልቁንም የባህሪዉ ነች፡፡

ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይነሳሉ፡፡እነዚህ ሰዎች ጥፋት የሚያስከትል ኑፋቄ በስዉር ያስገባሉ፤ የዋጃቸዉን ጌታ እንኳ ሳይቀር ክደዉበራሳቸዉ ላይ ፈጣን ጥፋት ያመጣሉ፡፡2ኛ ጴጥ 2፡1 አአት

ትልቁ የአዳም ስህተት እንኳን እግዚኣብሄርን (ሁሉን አዋቂ) ለመሆን ተመኘ እንጂ የእግዚኣብሄርን ምንነት (ባህሪ) አልካደም፡፡ ስለዚህ ጥብብ ተፈጠረች ስንል እግዚኣብሄርን እየካድን መሆናችንን መዘንጋት የለብንም፡፡ ልጁን ስንክት አብንም እንክዳለን ፡፡ ይሖዋ ምስክሮች እየሱስን ፍጡር ለማለት ሲሞክሩ ይሆዋ የሚሉትን አምላካቸውን ጥበብ አልባ ብለው ክደውታል፡፡ <<ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።›› (1ኛ ዮሐ 2፡23) የቆጡን ኣወርድ ብላ የብብትዋን ጣለች እንደሚባለዉ የይሖዋ ምስክሮች እየሱስን በመካዳቸዉ ብቸኛ አምላካችን ይሖዋ የሚሉትንም ክደዋል፡፡ይህን አላስተዋሉም፡፡ሁላችንም ይህን ልንነግራቸዉ ይገባል፡፡ ‹‹<<ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ ›› የሚለዉ ይህን ነዉ፡፡


የእግዚኣብሄር ጥበብ እና እየሱስ፡-



እየሱስ ክርስቶስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡24 ላይ “እያሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ” ተብሎኣል፡፡ ከዚህም በጨማሪ እየሱስ በራዕ 3፡14 ላይ ‹‹ የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ›› ተብሎኣል፡፡ ይህን ራዕይ 3፡14ን ትርጉም ደግሞ መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አዲስ ኪዳን የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ ነው፡፡ ይህን ክፍል የተለያዩ ትርጉሞች እንደሚከተለው ተርጉመዋል፤ ‹‹በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው 1962፣1980›› እንዲሁም የይሖዋ ምስክሮች ትርጉም‹‹ ከአምላክ ፍጥረት የመጀመሪያ የሆነው ›› ፡፡ የይሖዋ ምስክሮች እንግሊዝኛው ደግሞ ‹‹the beginning of the creation by God:
›› በማለት ተርጉሞታል፡፡የእንግሊዝኛው ኪንገ ጀምስ ደግሞ ‹‹
the beginning of the creation of God:
›› በማለት ተርጉሞታል፡፡  ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ትርጉም በግሪኩ ቃል በቃል የይሖዋ ምስክሮች ከተጠቀሙት የግሪክ መጽሓፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ነው፡፡

(the) (Amen,) (the) μάρτυς(witness) (the) πιστὸς(faithful) καὶ(and) (the) (true,)   (the) ἀρχὴ(beginning) τῆς(of the) κτίσεως(creation) τοῦ(of the) (God,)

ከግሪኩ እንደምንረዳው ሁሉም ትርጉሞች በትክክል አልተረጎሙትም፡፡ በ1962 እና 1980ው ውስጥ ‹‹በእግዚአብሔርም›› የሚለው ውስጥ በግሪኩ ‹‹›› የሆነው ‹‹በ›› የሚለው ቅጥያ የለም፡፡ ይህ ‹‹በእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ›› የሚለው ፣ እየሱስን ከፍጡር ውስጥ የሚመድብ የሚያወናብድ ትርጉም ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ደግሞ የበለ ግልጽ እንዲሆን ‹‹ከአምላክ ፍጥረት የመጀመሪያ›› ቢተረጉሙም ይህም ስህተት ነው፤ ምክንያም በግሪኩ ‹‹ἀπὸ(from) ›› የሆነው ‹‹ከ›› ቅጥያ የለም፡፡ በእንግሊዝኛውም ይሆዋ ምስክሮች ትርጉም ስህተት ነው ፣በግሪኩ ‹‹ ὑπ’(by) (hypo)›› የሆነው ‹‹ by›› የሚለው ቅጥያ የለም፡፡ ስለዚህ ከግሪኩም እንደምንመለከተው ‹‹የእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ/the beginning of the creation of God›› የሚለው ትክክል ነው፡፡ እናም ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል በምሳ 8፡22 ላይ ጥበብ ‹‹ የእግዚኣብሄር መንገድ (ፍጥረት) መጀመሪያ›› ከተባለችው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም እየሱስ እዚህ ጋር የተባለው የፍጥረታት ምንጭ ነው የተባለው፡፡ ‹‹ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።›› (ዮሐ 1፡1)


ጥብብ ከእግዚኣብሄር ተወለድኩ በማለት ዘላለማዊነትዋን እና የእግዚኣብሄር የባህሪዉ መሆንዋን ትናገራለች፡፡እየሱስ ክርስቶስ የእግዚኣብሄር ኣንድያ ልጅ /ኣንተ ልጄ ነህ መባሉ  ዘላለማዊነቱን እና የባህሪ ልጅነቱን ይናገራል፡፡ዘላለማዊ ካልሆነዉ ሰዉ የሚወለደዉ ዘላለማዊ አይደለም ነገር ግን ዘላለማዊ ከሆነዉ የሚወለደዉ ዘላለማዊ ነዉ፡፡ዘላለማዊ ልደት፡፡

ጥብብ የእግዚኣብሄር መንገድ/ስራ/ፍጥረት መጀመሪያ በመባል ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩት በእግዚኣብሄር ጥበብ መሆኑን ይገልጻል፡፡እየሱስ ክርስቶስም በራዕ 3፡14 የእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ በመባል ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩት በእርሱ መሆኑን ይገልጻል፡፡በተጨማሪም ዮሓ1፡3፣ቆላ 1፡15-16፡፡

ዋቢ ማስረጃዎች

1 , C:F.BurneyChrist as the Apex of Creation (Prov. viii 22, Col. i 15-18, Rev. iii 14.)” The Journal of Theological Studieshttps://digilander.libero.it/domingo7/Burney.pdf
2,ምሳ 8፡22 ቃል በቃል ትርጉም ፣ https://biblehub.com/interlinear/proverbs/8-22.htm

3,የይሖዋ ምስክሮች ግርክ ቃል በቃል ትርጉም ፣KIT https://wol.jw.org/en/wol/b/r1/lp-e/int/E/1985/66/3#s=14&study=discover



ስሉስ ቅዱስ የተመሰገነ ይሁን፡፡


2 comments: