Pages

Wednesday, April 20, 2016

እየሱስ የፍጥረታት በኩር (ቆላ 1፡15-17)

    የፍጥረታት በኩር ማለት ምን ማለት ነዉ?
      በቆላ 1፡15 ላይ እየሱስን የፍጥረታት ሁሉ በኩር ይለዋል፡፡ይህ ቆላ 1፡15 የይሆዋ ምስክሮች እንደሚሉት እየሱን የመጀመሪየዉ ፍጥረት ማለቱ ነዉን? በኩር ማለትስ ምን ማለት ነዉ?ይህ በኩር ተብሎ የተተረጎመዉ የግሪክ ቃል ፕሮቶኮስ( prototokos) የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛዉ ፈርስት ቦርን (Firstborn) ነዉ፡፡መጀመሪያ የተፈጠረ (First created) ለማለት የግሪኩ ቃል ፕሮቶክቲሲሰ (protoktisis)  ነዉ፡፡ታዲያ ይህ ቆላ 1፡15 እየሱስን መጀመሪያ የተፈጠረ ለማለት ከፈለገ ለምን ፕሮቶክቲሲሰ/ First created አላለም?

      ብኩርና ሁለት ትርጉም ኣለዉ፡፡ኣንደኛዉ ቀድሞ የተወለደ ማለት ነዉ፡፡ሁለተኛዉ ስልጣን አለቅነት ነዉ፡፡የመጀመሪያዉ ብኩርና (ቀድሞ መወለድ) ለሌላ ወገን ሊተላለፍ አይችልም፡፡የሁለተኛዉ ብኩርን (የበላይነት/ስልጣን) ለሌላ ወገን ሊተላለፍ ይችላል፡፡ብኩርና ስልጣን ስለመሆኑ የያዕቆብን እና የኤሳዉን ታሪክ ማየት ይቻላል፡፡31፤ ያዕቆብም። በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው። 32፤ ዔሳውም። እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ፤ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት? አለ ። 33፤ ያዕቆብም። እስኪ በመጀመሪያ ማልልኝ አለው። ማለለትም፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ። ዘፍ 25፡31-33 ታዲያ ያዕቆብ ከኤሳዉ በእድሜ በለጠ?በፍጹም፡፡ነገር ግን በስልጣን በለጠ፡፡


      ታዲያ እየሱ ለምን የፍጥረታት በኩር ተባለ? በአማርኛ ምክንያትን ስለሆነ ወይም ኣልና ብለን ስንገልጽ በእንግሊዝኛ because/For/Therefore እያልን እንገልጻለን፡፡ግሪኩም hoti ይለዋል፡፡ቆላ 1፡16 እየሱስ ለምን የፍጥረታት ሁሉ በኩር እንደተባለ በዚሁ መልክ ይገልጻል፡፡
        የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና

        For by Him all things were created, both in the heavens and on earth, visible and invisible, whether thrones or dominions or rulers or authorities-- all things have been created through Him and for Him.

        ότι(hoti) for εν in αυτώ him εκτίσθη were created τα πάντα the whole(all),τα the things εν in τοις the ουρανοίς heavens, και and τα the things επί upon της the γης earth–τα the ορατά visible καιand τα the αόρατα unseen; είτε whether θρόνοι thrones, είτε whether κυριότητες lordships, είτε whether αρχαί sovereignties, είτε whether εξουσίαι authorities; ταπάντα the whole(all) δι΄ through αυτού him και and εις in αυτόν him έκτισται have been created

      የፍጥረታት በኩር የተባለዉ ቀድሞ ስለተፈጠረ ቢሆንማ ኖሮ እዚያዉ ሁሉም በእርሱና ለእርሱ ተፈጠሩ ባላለ ነበር፡፡ስለዚህ እየሱስ የፍጥረታት ሁሉ በኩር የተባለዉ በፍጥረታት ላይ ባለዉ ስልጣን ነዉ፡፡ ይህንንም በግልጽ በምክንያት ተጽፎ ከላይ አይተናል፡፡



      የይሖዋ ምስክሮች በዚህ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል በግሪኩ መጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ የሌላ ” ሌሎች” የሚል ቃል ጨምረዋል፡፡ትምህርታቸዉ መጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ ካለ በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ የሌለ እና ትርጉሙን የሚቀይር ቃል ማስገባት ለምን አስፈለገ?












      No comments:

      Post a Comment