Pages

Monday, October 3, 2016

መንፈስ ቅዱስ

የይሖዋ ምስክሮች መንፈስ ቅዱስ ዝርዉ ሀይል (መንፈስ ቅዱስ በሥራ ላይ ያለ የአምላክ ኃይል ) ነዉ ይላሉ፡፡ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች መንፈስ ቅዱስ አካላዊ አይደለም በማለት የክህደት ትምህርትን ያስተምራሉ፡፡ ምንም እንኳን የይሖዋ ማስክሮች ይህን ሀሳባቸዉን በተለያዩ መጽሃፎቻቸዉ  (ለምሳሌ ፡በስላሴ ማመን ይገባሃልን ፣መጠበቂያ ግንብ 2009፣ጥቅምት 1፣ገጽ 4-5) ቢገልጹም፣የይሖዋ ምስክር ነኝ በሚል የግል የፌስቡክ ገጽ1 እና ገጽ2 እና  በድርጅቱ ድረገጽ ላይ  እንዲሁ ይገኛል(መስከረም 242009 .. የተጎበኘ)፡፡

ይህ ጽሁፍ በተገለጹት የፌስ ቡክ እና የድርጅቱ ድረ ገጽ ላይ ለተቀመጡት የየይሐሖወዋ መምሰስከክረሮቸች ሀሳቦች መልስ ይሰጣል፡፡ለዚህ መልስ ከመስጠቴ በፊት አካል ማለት ምን ማለት እንደሆነ በጥቂቱ ላብራራ፡፡

አካል ማለት የራሱ ባህሪ ያለዉ፣ንቃታ ህሊና ያለዉ፣ኣንተ ብለን ልናወራዉ የምንችላዉ እንደ ሰዉ፣እንደ እገዚኣብሄር (ለጊዜዉ  አብ እና ወልድ)፣የራሱ የሆነ ማንነት ያለዉ ማለታችን ነዉ፡፡ ለምሳሌ የመንግስት አካላት ማለት በኣንድ መንግስት ስር ያሉ ስልጣን ያላቸዉ ሰዎች ማለታችን ነዉ፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ አካል የራሱ የሆነ ማንነት ኣለዉ፡፡ አካል ስንል የሰዉነት ክፍል (ክፍልፋይ) ማለታችን አይደለም፡፡ ስለ አካል የዚህን ያህል ከተናገርኩ ወደ መልሶቹ ልሂድ፡፡ በተከታታይ ክፈሎች በመከፋፈል የይሖዋ ምስክሮች ስለ መንፈስ ቅዱስ ለሚያተምሩት የክህደት ትምህርቶች መልስ እንሰጣለን፡፡ክፍል ሁለትን ያንብቡ! 

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
መንፈስ ምንድን ነዉ የሚለዉ ርዕሳቸዉ ስር ‹‹በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መንፈስ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ሩአህ ሲሆን የግሪክኛው ቃል ደግሞ ንዩማ ነው።›› ካሉ በኋላ እነዚህ ቃላት የተለያዩ ትርጉሞች እንዳሉት ከመጽሃፍ ቅዱስ በመጥቀስ ይገላጻሉ፡፡ ከእናዚህም ዉስጥ ኣንዱ መንፈሳዊ አካላት (አምላክና መላእክት)—1 ነገሥት 22:21፤ ዮሐንስ 4:24እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ትርጉም በቀጠል ይህን ሀሳብ እናገኛለን፡፡
‹‹ሁሉንም የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ፤ ሁሉም በሰው ዓይን ሊታዩ ባይችሉም የሚያሳድሩትን ውጤት ግን መመልከት እንችላለን። በተመሳሳይም የአምላክ መንፈስ “ልክ እንደ ነፋስ ሁሉ የማይታይና የማይዳሰስ እንዲሁም ኃይል ያለው ነው።”—አን ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኒው ቴስታመንት ዎርድስ http://www.menfak.no/bibel/vines.html››

 መልስ ፡-
የይሖዋ ምስክሮች እንደሚሉት የይብራይስጡ ሩሃ ወይም የግሪኩ ኒዉማ ትርጎሞች ኣንዱ መንፈሳዊ አካላት ማለት ነዉ፡፡ልክ ነዉ፡፡ ኣብ መንፈሰዊ አካል ፣መላዕክትም …፡፡ስለዚህ የይብራይስጡ ሩሃ ወይም የግሪኩ ኒዉማ ትርጉም መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንዳል ሆነ አይናገርም ማለት ነዉ፡፡
እዚህ ላይ አን ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኒው ቴስታመንት ዎርድስ (An Expository Dictionary of New Testament Words) የሚባለዉን መዝገበ ቃላት ለማስረጃነት መጠቀማቸዉን እናስተዉል፡፡ምናልባት ይህን ዲክሽነሪ መጥቀሳቸዉ ይህ ዲክሺነሪ (መዝገበ ቃል) የይሖዋ ምስክሮችን ሀሳብ የሚደግፍ ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ መዝገበ ቃላት የግሪኩ ንዩማ (መንፈስ) አካላዊዉን መንፈስ ቅዱስ እንደሚያመለክት ይገልጻል፡፡ እናም መነፈስ ቅዱስ ልክ እንደ ነፋስ ሁሉ የማይታይና የማይዳሰስ እንዲሁም ኃይል ያለው  ሆኖ ሳለ አካላዊ ነዉ ይላል፡፡ እግዚኣብሄርስ መንፈስ አይደለምን; እናም ይ መዝገበ ቃል የይሖዋ ምስክሮችን  የንዩማ (መንፈስ) ትርጉም እየተቃወመ እንደሚደግፋቸዉ ኣርገዉ ማቅረባቸዉ እዉነታዉን ለመደበቅ እና ሰዎችን ለማታለል ነዉ፡፡ ማታለል መዋሸት የሰይጣን ስራ  ነዉ፡፡

መንፈስ ቅዱስ አካላዊ (Personality of the Holy Spirit) መሆኑን ከ አን ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኒውማ ቴስታመንት ዎርድስ መዝገበ ቃላት የተቀነጨበ፡፡
the Personality of the Holy Spirit, e.g., John 14:26, where He is …The Personality of the Spirit is emphasized at the expense of strict grammatical procedure in John 14:26; 15:26; 16:8,13,14, … "He," is used of Him in the masculine, …. The rendering "itself" in Rom. 8:16,26, due to the Greek gender, is corrected to "Himself" in the RV…The subject of the "Holy Spirit" in the NT may be considered as to His Divine attributes; His distinct Personality in the Godhead;
ሙሉዉን የመዝገበ ቃላቱን ሀሳብ http://www.menfak.no/bibelprog/vines.pl?word=spirit

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
መንፈስ ቅዱስ አይደለም የሚለዉ ርዕሳቸዉ ስር መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የአምላክእጅ፣’ ‘ጣትወይምእስትንፋስተደርጎ መገለጹ አካል እንዳልሆነ ይጠቁማል። (ዘፀአት 15:8, 10) የአንድ የእጅ ባለሙያ እጆች ከአንጎሉ ወይም ከሰውነቱ ተነጥለው ብቻቸውን እንደማይሠሩ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም መንቀሳቀስ የሚችለው በአምላክ አመራር ብቻ ነው።  ይላሉ፡፡

መልስ፡-
ጣት አካል ነዉ፡፡
ጣት መባሉ ኣንድነታቸዉንን እና የኣንዱ ኣለመኖር ለሌላዉ ጉድለት መሆኑን፡፡ሁላችንም እንደምናዉቀዉ እየሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ ተብሎኣል፡፡ጥበብ ግን አካላዊ አይደለም፡፡ የእግዚኣብሄር ጥበብ ዘላለማዊ እና ሁሌም አብራዉ እንደ ነበረች ሁሉ፣እየሱስ እንዲህ መባሉ ዘላለማዊነቱን እና ሁሌም አብረዉ መኖራቸዉን ይገልጻል፡፡መንፈስ ቅዱስ የእግዚኣብሄር እጅ እና እስትንፋስ መባሉ፣የእግዚኣብሄር እጅ እና እስትንፋስ ዘላላመዊ እና ሁሌም አብረዉት የነበር ስለ ሆኑ፣መንፈስ ቅዱስም በዚህ መጠራቱ ዘላለማዊነቱን እና ሁሌም አብረዉ መኖራቸዉን ይገልጻል፡፡እዚህ ላይ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ነዉ (አካል) ነዉ ስንል እንደ እጅ ከሰዉነታችን ኣንድ ኣካል እንደሆነ ማለታችን አይደለም፡፡ ነገር ግን እንደ ኣብ እና ወልድ የራሱ የሆነ አካል ኣለዉ ማለታችን ነዉ፡፡
  
የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
(ሉቃስ 11:13) መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን መንፈስ ከውኃ ጋር የሚያነጻጽረው ሲሆን እንደ እምነትና እውቀት ካሉ ነገሮች ጋር ተያይዞ የተጠቀሰበት ጊዜም አለ። እነዚህ ሁሉ ንጽጽሮች መንፈስ ቅዱስ አካል እንዳልሆነ ይጠቁማሉ።ኢሳይያስ 44:3 የሐዋርያት ሥራ 6:5 2 ቆሮንቶስ 6:6

መልስ፡-
መንፈስ ቅዱስ ከውኃ ጋር በመነጻጻሩ አካል የለዉም ካልን ኣብ እና ወልድ ከመንፈስ ቅዱስ (በየይሆዋ ምስክሮች ሀሳብ መሰረት) ጋር መነጻጸራቸዉ አካል የለቻዉም ያስብላል፡፡ምክንያቱም ኣብ እና ወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በኣንድ ስም ተጠርተዋል ማቴዎስ 28:19፡፡ እዚህ ጋር የይሖዋ ምስክሮች የራሳቸዉን አስተምሮ እየተቃወሙ ነዉ፡፡ ሞት አካላዊ እና ህይወት የሌለዉ ነዉ፡፡በእየሱስ መጠመቅ በሞት ከመጠመቅ ጋር ሲነጻጸር እንመለከታለን፡፡ስለዚህ በየይሖዋ ምስክሮች አነጋገር መሰረት እየሱስም አካላዊ አይደለም ማለት ነዉ፡፡ነገር ግን አካላዊ ነዉ ብለዉ ያምናሉ፡፡
Or do YOU not know that all of us who were baptized into Christ Jesus were baptized into his death? (NWT)
ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? ሮሜ 6፡3 (1962)
ወይስ ክርስቶስ ኢየሱስ ዉስጥ የተጠመቅን ሁላችን እሱሰ ሞት ዉስጥ እንደተጠመቅን አታዉቁም ሮሜ 6፡3 (የይሖዋ ምስክሮች መጽሃፍ ቅዱስ)
ስለዚህ ይህ የይሖዋ ምስክሮች ሀሳብ ከመጽኃፍ ቅዱ እና ከራሳቸዉም አስተምሮ ጋር ከመጋጨቱም በላይ መንፈስ ቅዱስን አካላዊ አይደለም አያስብልም፡፡ ከላይ የይሖዋ ምስክሮች የጠቀስዋቸዉ ሁሉ ስለ ምሰፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያወሩ ናቸዉ፡፡ በክፍል 6 ማብራሪያዉን ይነልከቱ፡፡ የሰዉ ልጅ አካላዊ መሆኑን የይሖዋ ምስክሮች ያምናሉ፡፡ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ዉስጥ የተጠመቅን ማለታቸዉን አስተዉሉ፡፡

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
የአብ ስም ይሖዋ፣ የወልድ ስም ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጿል፤ ይሁንና መንፈስ ቅዱስ ስም እንዳለው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የትም ቦታ አልተጠቀሰም።

መልስ፡-
ኣንድ ሀጻን እንደ ተወለደ ስም የለዉም፡፡ ስለዚህ ይህ ሕጻን አካላዊ አይደለም ማለት ነዉ ወይም  ሰዉ ሰዉ (አካላዊ ) የሚሆነዉ ስም ሲወጣለት ብቻ ነዉ እንደ የይሖዋ ምስክሮች ፡፡አስገራሚ ነዉ፡፡   የምንናገረዉን ነገር ቆም ብለን ማሰብ ኣለብን፡፡እዉነታን ለመካድ ስንል ሌላዉን እዉነታ እንክዳለን፡፡የኣንድ ክርስቲያን ዋናዉ ቁብነገር መንፈስ ቅዱስን ማወቅ ነዉ እንጂ ስሙ አይደለም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ስም የመንፈስ ቅዱስ ነዉ፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ኣንድ መንፈስ ቅዱስ ነዉ ያለን፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ስንል ማንን እንደምንጠራ ግልጽ ነዉ፡፡ የሖዋ (በተሸለ አጠራር ፣ያህዌይ) የሚለዉ የእግዚኣብሄር ስም ባህሪዉን (ዘላለማዊነቱን)የሚገልጽ ስም ነዉ፡፡ስለዚህ ያህዌይ የግል ስም ሳይሆን የባህሪ ስም ነዉ፡፡ትርጉሙም ያለ እና የነበረ ማለት ነዉ፡፡ እየሱስ (ዕብራ 13፡8፣ ኢሳ 9፡6) እና መንፈስ ቅዱስም ዘላለማዊ ስለሆኑ ያህዌይ ናቸዉ፡፡ነገር ግን ይህ ነገር መሰናክል የሚሆን ከሆነ፤መንፈስ ቅዱስ በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ በተለያዩ ስሞች ተጠርቶኣል፡፡ ፔራቅሊጦስ (ዮሓ 14፡16፣16፡7)፣የእዉነት መንፈስ(ሮሜ 8፡2) ወዘተ፡፡

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
(ኢሳይያስ 42:8 NW ሉቃስ 1:31) ሰማዕት የሆነው ክርስቲያኑ እስጢፋኖስ በሰማይ ላይ ያለውን ሁኔታ ተአምራዊ በሆነ መንገድ በራእይ በተመለከተበት ወቅት ሁለት እንጂ ሦስት አካላትን አላየም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትኩር ብሎ ወደ ሰማይ ሲመለከት የአምላክን ክብር እንዲሁም ኢየሱስ በአምላክ ቀኝ ቆሞ አየ።” (የሐዋርያት ሥራ 7:55)

መልስ፡-
መንፈስ ቅዱስን ኣየሁ እንዳላለዉ ሁሉ አላየሁም አላለም፡፡
የይሖዋ ምስክሮች በገዛ ፈቃዳቸዉ አላየም ይላሉ፡፡ በመጽሃፍ ቅዱስ ቢያምኑ ኖሮ ይህን ባላሉ፡፡መጽሃፍ ቅዱስ አላየም አይልም፡፡ ስለመንፈስ ቅዱስም አላወራም፡፡ ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ሀሰት ተናግረዋል፡፡

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
 “መንፈስ ቅዱስአካል ያለው ከመሆኑም በላይ የሥላሴ ክፍል ነው በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ 1 ዮሐንስ 5:7, 8 ላይ ያለው ሐሳብ ይህን ያሳያ ሚለዉ የተሳሳተ እምነት ነዉ፡፡
1879 ትርጉም ላይ 1 ዮሐንስ 5:7, 8 የሚከተለውን ሐሳብ ይዟል፦በሰማይ የሚመሰክሩ ሦስት ናቸውና እርሳቸውም አብ ቃልም መንፈስ ቅዱስም። . . . ሦስትም አንድም ናቸው።ይሁንና ተመራማሪዎች ሐዋርያው ዮሐንስ ይህን ሐሳብ እንዳልተናገረ ደርሰውበታል፤ በመሆኑም ሐሳቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አይደለም። ፕሮፌሰር ብሩስ ማኒንግ ሜትስገር እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦እነዚህ ቃላት ውሸት በመሆናቸው የአዲስ ኪዳን ክፍል ሊሆኑ አይገባም።”— ቴክስቹዋል ኮሜንታሪ ኦን ግሪክ ኒው ቴስታመንት
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መንፈስ ቅዱስ፣ አካል ያለው ነገር የሚያደርጋቸውን ነገሮች እንዳከናወነ ተደርጎ መገለጹ አካል እንዳለው ያሳያል ሚለዉ የተሳሳተ እምነት ነዉ፡፡

መልስ፡-
በመጀመሪያ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ የስላሴ ክፍል ነዉ ብለዉ አያምኑም፡፡ ስላሴ አይከፈልም፣ክፍልፋይ የለዉም፡፡ይህ የይሖዋ ምስክሮች ምስኪኖችን ለማታለል እና ግራ ለማጋባት የሚጠቀመዉ ዘዴ ነዉ፡፡ወይም ድርድቲ ስላሴ ማላት ምን እንደሆነ አያዉቅም፡፡ እኛ የምናምነዉ በንፈስ ቅዱስ የስላሴ አንዱ አካል (person) ብለን ነዉ፡፡ ስለ ኣንደኛ ዮሓ 5 በተመለከተ ደግሞ፤የመንፈስ ቅዱስ አካላዊነት እና አምላክነት በዚህ የመጽኃፍ ቅዱስ አንቀጽ ላይ ብቻ  የተመሰረተ አይደለም፡፡ ይህ የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ቢኖርም ባይኖርም በክርስቲያናዊ ትምህርት ላይ ለዉጥ የለዉም፡፡
እስቲ ለማንኛዉም ተጨመረ የተባለዉን ክፍል ትተን ከ1962ቱ ትርጉም ይህን 1 ዮሐንስ 5 አንመልከት፡፡
መቁጥር 6 ላይ እንዲህ ይላል፡፡
‹‹በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።››
እየሱ በዉሃ እና በደም መጣ ይላል፡፡ይህም እየሱስ ሰዉ ሆኖ መምጣቱን መግለጹነዉ፡፡ይህ ሁላችንም የምንስማማበት ነዉ፡፡እየሱስ በመስቀል ላይ ሲሞትም የፈሰሰዉ ዉሃ እና ደም ነበር፡፡
በቁጥር 7 ደግሞ እንዲህ ይላል፡፡
‹‹ መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።››
የሚመሰክረዉ መንፈስ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ምስክርነቱም እዉነት ነዉ፡፡
ቀጥሎ በቁጥ 8 ላይ እንዲህ ይላል፡፡
‹‹ የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ። ››
የሚመሰክሩት እነማን እንደሆኑ ይገልጻል፡፡ የሶስቱም ግን እንደሚስማማ እንዲሁ፡፡
መቁጥር 9 ደግሞ በቁጥር 7 ‹‹መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው፡፡›› የተባለዉ ውስጥ መንፈስ የተባለዉ እግዚኣብሄር መባሉን እናስተዉላለን፡፡
9፤ የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።
ስለዚህ መንፈስ ተብሎ የተጠራዉ እግዚኣብሄር ነዉ፡፡በመሆኑም የውኃውን እና  ደሙን ምስክርነት የሰዉ ምስክርነት ሲል መንፈሱን ምስክርነት ግን የእግዚኣብሄር ምስክርነት ይላዋል፡፡ የይሖዋ ምስክሮችም እንዲህ ብለዉ ጽፈዋል፡-
‹‹17 The Messiah would be pierced, but his bones would not be broken. Inhabitants of Jerusalem would “look to the One whom they pierced through.” (Zech. 12:10) And Psalm 34:20 states: “[God] is guarding all the bones of that one; not one of them has been broken.” Confirming these points, the apostle John wrote: “One of the soldiers jabbed his [Jesus’] side with a spear, and immediately blood and water came out. And he that has seen it [John] has borne witness, and his witness is true . . . These things took place in order for the scripture to be fulfilled: ‘Not a bone of his will be crushed.’ And, again, a different scripture says: ‘They will look to the One whom they pierced.’”—John 19:33-37.›› WT,2011,8/15,p16-17

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው ነገር የሚያደርጋቸውን ነገሮች እንዳደረገ ተደርጎ የተገለጸበት ጊዜ አለ፤ ይሁንና ይህ በራሱ መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አካል እንዳለው አያሳይም። ጥበብ፣ ሞትና ኃጢአትም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አካል ያለው ነገር የሚያደርገውን ነገር እንዳከናወኑ ተደርገው ተገልጸዋል። (ምሳሌ 1:20 ሮም 5:17, 21) ለምሳሌ ያህል፣ ጥበብሥራእንደምትሠራ እናልጆችእንዳሏት ተገልጿል፤ ኃጢአት ደግሞ እንደሚያታልል፣ እንደሚገድልና የመጎምጀት ፍላጎት እንደሚፈጥር ተደርጎ ተገልጿል።ማቴዎስ 11:19 ሉቃስ 7:35 ሮም 7:8, 11

መልስ፡-
ጥበብ፣ ሞትና ኃጢአት ሚባሉ (የሆኑ) አካላት ኣሉን? በፍጹም፡፡ነገር ግን መንፈስ የሆኑ አካላት ኣሉ፡፡ ኣዎን ፡፡እግዚኣብሄር መንፈስ ነዉ፣ሰይጣን መንፈስ ነዉ…ስለዚህ መንፈስ ቅዲስም መንፈስ ነዉ፡፡ (ከመጽሃፍ ቅዱስ ወይም…)

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
በተመሳሳይም ሐዋርያው ዮሐንስ እንደጻፈው ኢየሱስ፣ መንፈስ ቅዱስንረዳትብሎ የጠራው ከመሆኑም ሌላ ይህ ረዳት አሳማኝ ማስረጃ የሚያቀርብ፣ የሚመራ፣ የሚናገር፣ የሚሰማ፣ የሚያሳውቅ፣ የሚያከብርና የሚወስድ ወይም የሚቀበል እንደሆነም ተናግሯል።

መልስ፡-
እዉነት ነዉ፡፡ ‹‹አሳማኝ ማስረጃ የሚያቀርብ፣ የሚመራ፣ የሚናገር፣ የሚሰማ፣ የሚያሳውቅ፣ የሚያከብርና የሚወስድ ወይም የሚቀበል››  የሚያመዛዝን  ንቃተ ህሊና ያለዉ አካል የሚያደርጋቸዉ ነገሮች ናቸዉ፡፡ ለዚህ ነዉ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ነዉ የምንለዉ፡፡

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
(ዮሐንስ 16:7-15) ዮሐንስ በሌላ ጥቅስ ላይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር የተጠቀመው ንዩማ የሚለው ግሪክኛ ቃል ፆታ አመልካች የሌለውና ለግዑዝ ነገር የሚያገለግል ቃል መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው።ዮሐንስ 14:16, 17

መልስ፡-
ይህ ነገር ምንም ትኩረት የሚስብ ነገር የለዉም፡፡ ይህ የግሪክ ቋንቋን ስዋስዉ ኣለማወቅቃቸዉን ይገልጻል፡፡ በግሪክ ትንሽ ልጅ ተዉላጠስም ጾታ አልባ (‹‹ፆታ አመልካች የሌለውና ለግዑዝ ነገር የሚያገለግል ቃል ››) ነዉ፡፡ስለዚህ እንደ የይሖዋ ምስክሮች ሀሳብ ትንሽ ልጅ አካላዊ አይደለም ማለት ነዉ፡፡ የአምላክን ጥልቅ ሚስጢር ኣዉቃለሁ የሚለዉ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት ይህን ኣለማወቁ ይገርማል፡፡አሳፋሪም ነዉ፡፡ዝም ብሎ ነዉ ማለት ነዉ የሚያወራዉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በግሪክ ቋንቋ ጾታ አልባ በሆነዉ ተዉላጠስም መጠራቱ የቋንቋው ስዋስዉ ስለሆነ ነዉ እንጂ አካላዊ ስላልሆነ አይደለም፡፡ለበለጠ መረጃ ከላይ የይሖዋ ምስክሮች የጠቀሱትን መዝገበ ቃላት ያንብቡ፡፡http://www.menfak.no/bibelprog/vines.pl?word=spirit ፣ለዋቢነት የጠቀሱት መጽሃፍ ወይ ሙሉዉን አላነበቡም ወይም ሆን ብለዉ ትተዉ ነዉ፡፡
በተጨማሪ በግሪክ ሞት ጾታዉ ወንድ ነዉ (http://biblehub.com/greek/2288.htm )፡፡
በተጨማሪም የይሖዋ ምስክሮች በዮሓ16፡13-15 ስለ መንፈስ ቅዱስ በወንድ ጾታ (he) ብለዉ እንደተረጎሙ ማየት ይቻላል፡፡

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
ሰው የሚጠመቀው በመንፈስ ቅዱስ ስም መሆኑ መንፈስ ቅዱስ አካል እንደሆነ ያሳያል ሚለዉ የተሳሳተ እምነት ነዉ፡፡
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥስምየሚለው ቃል ሥልጣንን ወይም ቦታን ለማመልከት የተሠራበት ጊዜ አለ። (ዘዳግም 18:5,19-22 አስቴር 8:10) ለምሳሌ ያህል፣በሕግ ስምየሚል የተለመደ አባባል አለ፤ ይህ አባባል ሕግ አንድ ዓይነት አካል እንደሆነ የሚጠቁም አይደለም። አንድ ሰውበመንፈስ ቅዱስ ስምመጠመቁ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ፈቃድ እንዲፈጸም በማድረግ በኩል ያለው ሥልጣንና ድርሻ አምኖ መቀበሉን የሚያሳይ ነው።ማቴዎስ 28:19

መልስ፡-
መህግ ስም የሚለዉ መጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ አላየሁም፡፡በእርግጥ የይሖዋ ምስክሮች ‹የተለመደ አባባል› ይሉታል (እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግ (ልማድ) ቆላ 2፡8) ፡፡ ስም የሚለዉ ሥልጣንና ድርሻን ሳይሆን ይበልጥ ስልጣንን ያሳያል (nsight, Volume 2 p. 1019-1020) ፡፡ በህግ ስም ስንልም እንዲሁ ነዉ፡፡ስለዚህ ስም ስልጣንን ያሳያል የሚለዉን እንያዝ ፡፡
ማቴዎስ 28:19
‹‹በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥››
እንደ የይሖዋ ምስክሮች አስተሳሰብ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ካልሆነ፣ኣብ እና ወልድ ከእርሱ ጋር ስለተነጻጸሩ (ለዚያዉም በስልጣን)፣ኣብ እና ወልድ አካላዊ አይደሉም ማለት ነዉ ፡፡ ወይም ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ከሆኑት ጋር ስለተጠራ እሱም አካላዊ ነዉ ማለት ነዉ፡፡ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ አካላዊ አይደለም ከሚሉባቸዉ ውስጥ ኣንዱ አካላዊ ካልሆኑት ከዉሃ …ጋር መጠራቱ (መነጻጸሩ) ነዉ (ይህን ይመልከቱ)፡፡
በጠጨማሪም ስሞች ሳይሆን ስም እንደሚል እናስተዉል፡፡ስለዚህ ሶስቱም ኣንድ ስልጣን (ስም) እንዳላቸዉ ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም ስልጣን ንቃተ ህሊናን የሚጠይቅ ነገር መሆኑን እናስተዉል፡፡የግኡዝ ነገር ባህሪ አይደለም፡፡ ለዚህ ነዉ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ነዉ የሚሉት፡፡

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
የኢየሱስ ሐዋርያትና ሌሎች የጥንት ክርስቲያኖች፣ መንፈስ ቅዱስ አካል እንደሆነ ያምኑ ነበር የሚለዉ የተሳሳተ እምነት ነዉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ታሪክ ይህን ሐሳብ አይደግፍም። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ መለኮታዊ አካል እንደሆነ . . . የሚገልጸው ሐሳብ የመጣው 381 .. ከተካሄደው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ በኋላ ነው።ይህም የሆነው የመጨረሻው ሐዋርያ ከሞተ 250 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ ነው።

መልስ፡-
ሀሰት፡፡በ381 . በመንፈስ ቅዱስ ላይ ለተነሳዉ ክህደት መልስ የተሰጠበት ነዉ እንጂ መለኮታዊ አካል እንዳለዉ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተምሮዉ የተጀመረበት አይደለም፡፡ይህ ታሪክን ካለማወቅ ወይም ሰዎችን ሆን ብሎ ለማሳሳት ታሪክን የማዛበት ስራ ነዉ፡፡
ከ381 ዓ.ም በፊት ቅዱስ ራሱን የቻለ መለኮታዊ አካል እንደሆነ እና እንደ ኣብ አምላክ (እግዚኣብሄር) ይታመን እንደ ነበረ ኣንተ ከጠቀስከዉ አመት ከ161 አመት በፊት የሞተዉ ተርቱሊያን ፣ሶስት አካላት፣ኣብ ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ ከማለቱም በላይ፣መንፈስ ቅዱስም እንደ ኣብ እና ወልድ ሁሉ፣በባህሪዉ አምላክ መሆኑን ይገልጻል፡፡ስለሴ የሚለዉንምቃል እዚሁ እናገኛለን፡፡መጽሃፍ ቅዱስም ቢሆን የመንፈስ ቅዱስን አካላዊነት ይደግፋል፡፡ በክፍል ስድስት ማስረጃ ኣለ፡፡

ከ381 ዓ.ም በፊት ስለ መንፈስ ቅዱስ አካላዊነት ያስተማሩ አባቶች፡፡
1.      ከ145-220 የኖረዉ ተርቱሊያን
በሶስተነት ኣንድነት ፣… ሶስት አካላት (Persons).. አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ፡፡ ይህም በአካል ሶስት ሲሆኑ በመለኮት ኣንድ ናቸዉ የምንለዉን ማለት ነዉ፡፡

The Unity into a Trinity,…the three Persons'-- the Father, the Son, and the Holy Ghost: Tertullian, who lived 145 – 220 A.D. ante-nicea,Volume 3 LatinChristianity, AGAINST PRAXEAS, ,p598
2.       ከ35-108 የኖራዉ ኢግናቲየስ ሉኣላዊ በማለት ይጠረዋል፡፤
and the apostles receive from God, through Jesus Christ, one and the same Holy Spirit, who is good, and sovereign, and true, and the Author of [saving] knowledge.” (Ignatius of Antioch who lived 35 –108 A.D) The Ante-Nicene Fathers, Volume I: The Apostolic Fathers with Justin Martyr and Irenaeus (A. Roberts, J. Donaldson & A. C. Coxe, Ed.) (p82).
3.     ከ100-165 የኖረዉ ጀስቲን ደግሞ
‹‹እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ፣ከአባቱ አካል ወይም ከራሱ አካል፣…›› በማለት መንፈስ ቅዱስ አካል እንዳለዉ ይናገራል፡፡

“And the Holy Spirit, either from the person of His Father, or from His own person, answers them, ‘The Lord of hosts, He is this King of glory.” (Justin Martyr 100 – 165 AD) The Ante-Nicene Fathers, Volume I: The Apostolic Fathers with Justin Martyr and Irenaeus  (p213)

4.     ከ175 – 185 በጸፈዉ ጽሁፉ ዉስጥ የሊዮኑ ኢረናዩስ ኣብ መልድ እና መንፈስ ቅዱስን ሶስቱ ሰላዮች በማለት በበጎ ይጠራቸዋል፡፡
“the three spies, who were spying out all the land, and hid them at her home; [which three were] doubtless [a type of] the Father and the Son, together with the Holy Spirit.  (Irenaeus of Lyons 175-185 AD)  The Ante-Nicene Fathers, Volume I: The Apostolic Fathers with Justin Martyr and Irenaeus (492)

ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች የጥንት አባቶች መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንደሆነ 381 .ም በፊት አያምኑም የሚሉት  አይን ያወጣ ሀሰት ነዉ፡፡

የይሆዋ ምሰክሮች ሀሳብ፡-
ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑበማለት የጻፈው ሐዋርያው ጳውሎስ ነበር። (ኤፌሶን 4:30) አንዳንዶች እነዚህ ቃላት መንፈስ ቅዱስ አካል መሆኑን እንደሚጠቁሙ ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂበታማኝና ልባም መጋቢበሚዘጋጁ ጽሑፎች ላይ የጥንት ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን አካል እንደሆነ ወይም ከልዑሉ አምላክ ጋር እኩል የሆነ የሥላሴ ክፍል አድርገው ይመለከቱት እንዳልነበር የሚያሳይ ቅዱስ ጽሑፋዊና ታሪካዊ ማስረጃ በተደጋጋሚ ወጥቷል።* (ሉቃስ 12:42 1954 ትርጉም) በመሆኑም ጳውሎስ ከላይ ያለውን የተናገረው መንፈስ ቅዱስን እንደ አንድ አካል አድርጎ በመመልከት አልነበረም።
መንፈስ ቅዱስ በዓይን የማይታይ የአምላክ ኃይል ነው። (ዘፍጥረት 1:2) ዮሐንስ በውኃ እንዳጠመቀ ሁሉ ኢየሱስበመንፈስ ቅዱስእንደሚያጠምቅ ተነግሮለት ነበር። (ሉቃስ 3:16) 33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ 120 ገደማ የሚሆኑ ደቀ መዛሙርትበመንፈስ ቅዱስ የተሞሉሲሆን አንድ አካል መጥቶ በውስጣቸው እንዳልገባ የታወቀ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 1:5, 82:4, 33)

 መልስ፡-
የይሖዋ ምስክሮች ‹ታማኝ እና ልባም› ብለዉ ድርጅታቸዉን ስለመጥራታቸዉ እና ለዚህም (ሉቃስ 12:42 ስለመጥቀሳቸዉ በማስረጃ መጨረሻ ላይ እንመለከታለን፡፡ በቅድሚያ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያነሱትን መልስ እንስጥበት፡፡ በመጀመሪያ መንፈስ ቅዱስ ስንል የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ (ስጦታ) እና አካላዊዉ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነዉ፡፡ አካላዊ መንፈስ ቅዱስ (የስላሴ አካል) የሆነዉ ኣንድ ሲሆን ስጦታዉ (ጸጋዉ) ግን ብዙ ነዉ፡፡
“የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤” 1ኛ ቆሮ 12፡4:: እዚሁ የመጽሃፍ ቅዱ ክፍል(ከቁጥር 8 እስከ 10) ዉስጥ እነዚህ ልዩ ልዩ የተባሉት የመንፈስ ቅዱስ ጻጋ ጥበብን መናገር፣እውቀትን መናገር፣እምነት፣የመፈወስ ስጦ፣ትንቢትን መናገር፣መናፍስትን መለየት፣ልሳን መናገር፣መተርጎም መሆናቸዉን የናገራል፡፡ “ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።” ቁጥር 11፡፡
የይሖዋ ምስክሮች ከላይ በቁንጽል የጠቀሱት መዝገበቃላትም በግሪክ መጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ አካላዊዉ መንፈስ ቅዱስ በሚሆንበት ጊዜ በአብዛኛዉ ከፊቱ አመላካች (definite article) ይኖራል በማለት እዚያዉ የይሖዋ ምስከሮች የጠቀሱት ገጽ ላይ ጽፈዋል፡፡ነገር ግን የይሖዋ ምስክሮች ይህን እዉነት ስለማይፈልጉት ቆረጠዉታል፡፡
As a general rule the article is present where the subject of the teaching is the Personality of the Holy Spirit, e.g., John 14:26, where He is spoken of in distinction from the Father and the Son. See also 15:26 and cp. Luke 3:22. http://www.menfak.no/bibelprog/vines.pl?word=spirit በተጨማሪም ለተመሳሳይ ሀሳብ The Doctrine of the Greek Article› Thomas Fanshaw Middleton፣ገፅ125-126 ያንብቡ፡፡

ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት፣መጠመቅ ወዘተ በተጠቀሰበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን ሲያመለክት የስላሴ አካል የሆነዉን፣ ንቃተ ህሊና ያለዉ አካላዊ መንፈስ ቅዲስን ሲያመለክት ላምሳሌ፣ሰብኣዊ ስሜቶች (ማስተማር፣ማዘን፣በምራት፣…) የሚፈጽመዉ፣ በጥምቀት በኣብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሲል ወዘተ አካላዊ መንፈስ ቅዱስ ማለቱ ነዉ፡፡
ስለዚህ ከሁለቱ መጽሃፎች እንደምንረዳዉ፡-
1.      ከግሪኩ ኒዉማ ፊት አመልካች ቃል (definite article) ከሌላ (πνεύματος(of spirit),/ πνεύματι(spirit) ἁγίῳ(holy) ) መንፈስ ቅዱስ ማለት ጸጋዉ ነዉ
2.     ከግሪኩ ኒዉማ ፊት አመልካች ቃል (definite article) ካላ (τὸ(the) ἅγιον(holy) πνεῦμα(spirit) , τὸ(the) πνεῦμα(spirit) …)መንፈስ ቅዱስ ማለት አካላዊዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ
(ለማስረጃነት የተጠቀምኳቸዉ ሁሉም የግሪክ እንግሊዝኛ ቃል በቃል መጽሃፍ ቅዱስ ትርጎሞች ድርጅቱ ራሱ ካሳተመዉ መጽሃፍ የተወሰዱ ናቸዉ (KIT 1985))
መንፈስ ቅዱስ ሲል የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ መሆኑን የሚያመለክቱ ክፈሎች ፡-
የይሖዋ ምስክሮች ከላይ የተቀሱት (ሉቃስ 3:16 , የሐዋርያት ሥራ 1:5, 2:4) በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ እና መሞላት ማለት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እና ስጦታ ማለት ነዉ፡፡
 Ἰωάνης(John) μὲν(indeed) ἐβάπτισεν(baptized) (to water,) ὑμεῖς(YOU) δὲ(but) ἐν(in) πνεύματι(spirit) ሥራ 1:5
 ἐπλήσθησαν(they became filled) πάντες(all) πνεύματος(of spirit) (holy,) καὶ(and) ἤρξαντο(they started) λαλεῖν(to be speaking) ἑτέραις(to different) γλώσσαις(tongues) καθὼς(according as) τὸ(the) πνεῦμα(spirit) ἐδίδου(was giving) ἀποφθέγγεσθαι(to be uttering) αὐτοῖς ሥራ2:4
 ὑμᾶς(YOU) βαπτίσει(will baptize) ἐν(in) πνεύματι(spirit) ἀγίῳ(holy) καὶ(and) πυρίሉቃስ 3:16
በአጠቃላይ የይሖዋ ምስክሮች ብዙ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ አይደለም ለሚለዉ የሚጠቅሷቸዉ ጥቅሶች፤በመንፈስ ቅዱስ ስለመሞላትን በወይን ጠጅ ፣በጥበብ ከሞላት፣ በእምነት ከመሞላት፣ በደስታ ከሞሞላት፣በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት ፥ፍቅር፥ በእውነት ቃል ከመሞላት ጋር አወዳድሮ የገለጸበት (ኤፌ 5፡18፣የሓዋ 6፡3፣የሓዋ 11፡24፣የሓዋ 13፡52፣ የሐዋ 6:5  2ኛ ቆሮ 6፡6) ሁሉም ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ (መንፈስ) ሲሉ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ማለታቸዉ ነዉ፡፡ በማቴ 3፡11 እና ማርቆ 1፡8 ላይ በመንፈስ ቅዱስ፣በዉሃ እና በእሳት መጠመቅ ሲል የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ማለቱ ነዉ፡፡
ከግሪኩ ኒዉማ ፊት የግሪኩ አመልካች ቃል (definite article) ከግሪኩ ኒዉማ ፊት አላመኖሩን ያስተዉሉ፡፡
 μὴ(not) μεθύσκεσθε(be YOU being made drunk) (to wine,) ἐν(in) (which) ἐστὶν(is) (unsaving course,) ἀλλὰ(but) πληροῦσθε(be YOU being filled) ἐν(in) πνεύματι ኤፌ 5፡18
 πλήρεις(full) πνεύματος(of spirit) καὶ(and) (of wisdom,) οὓς(whom) καταστήσομεν(we will appoint)  የሓዋ 6፡3
 πλήρη(full) πίστεως(of faith) καὶ(and) πνεύματος(of spirit) ἁγίου የሓዋ 6፡5
 ἦν(he was) ἀνὴρ(male person) ἀγαθὸς(good) καὶ(and) πλήρης(full) πνεύματος(of spirit) ἁγίου(holy) καὶ(and) πίστεως. ፣የሓዋ 11፡24
 χαρᾶς(of joy) καὶ(and) πνεύματος(of spirit) ἁγίουየሓዋ 13፡52
 (purity,) ἐν(in) (knowledge,) ἐν(in) (longness of spirit,) ἐν(in) (kindness,) ἐν(in) πνεύματι(spirit) (holy,) ἐν(in) ἀγάπῃ(love) (unhypocritical,)2ኛ ቆሮ 6፡6
 γ(I) μὲν(indeed) ὑμᾶς(YOU) βαπτίζω(I baptize) ἐν(in) ὕδατι(water) εἰς(into) μετάνοιαν·(repentance;) (the (one) δὲ(but) ὀπίσω(behind) μου(me) ἐρχόμενος(coming) ἰσχυρότερός(stronger) μου(of me) (is,) οὗ(of whom) οὐκ(not) εἰμὶ(I am) ἱκανὸς(fit) τὰ(the) ὑποδήματα(sandals) βαστάσαι·(to carry off;) αὐτὸς(he) ὑμᾶς(YOU) βαπτίσει(will baptize) ἐν(in) πνεύματι(spirit) ἁγίῳ(holy) καὶ(and)πυρί·(fire)በማቴ 3፡11
 γ(I) ἐβάπτισα(baptized) ὑμᾶς(YOU) (to water,) αὐτὸς(he) δὲ(but) βαπτίσει(will baptize) ὑμᾶς(YOU) πνεύματι(to spirit) ἁγίῳማርቆ 1፡8
አካለዊዉን መንፈስ ቅዱስ የሚመለክቱ ክፍሎች፡-
መስደብ የምንችለዉ ግኡዝ ያልሆነ ፣አካለዊ የሆነና ንቃተህሊና ያለዉን ነገር ብቻ ነዉ፡፡ ትልቁ እና ስርየት የሌለዉ ሃጢኣት መንፈስ ቅዱን መስደብ ነዉ (ማቴ 12፡32፣ማር 3፡29፣ሉቃ 12፡10) ፡፡ይህ መንፈስ ቅዱስ ግኡዝ ያልሆነ ፣አካለዊ የሆነና ንቃተህሊና ያለዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ እንጂ ጻጋዉ አይደለም፡፡ ይህም በኤፊሶን 4፡30 አታሳዝኑት የተባለዉ፣አካላዊዉን መንፈስ ቅዱስ ነዉ፡፡በማቲዮስ ወንጌል 28፡19 ላይ ስለ ጥምቀት ከአካላዊዉ ኣብ እና ወልድ ጋር የተጠራዉ ግኡዝ ያልሆነ ፣አካለዊ የሆነና ንቃተህሊና ያለዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ እንጂ ጻጋዉ አይደለም ፡፡የሉቃስ ወንጌል 12፡12 እና ዮሓንስ ወንጌል 14፡26 ላይ የስተማረዉ ግኡዝ ያልሆነ ፣አካለዊ የሆነና ንቃተህሊና ያለዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ እንጂ ጻጋዉ አይደለም ፡፡በሃዋሪያት ስራ 2፡38 ላይ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ሲል መንስ ቅዱስ አካላዊዉ ሲሆን ስጦታ የተባለዉ ግን ጸጋዉ ነዉ፡፡

ከግሪኩ ኒዉማ ፊት የግሪኩ አመልካች ቃል (definite article) መኖሩን ያስተዉሉ፡፡
 δ’(but) ἂν(likely) εἴπῃ(might speak) κατὰ(down on) τοῦ(the) πνεύματος(spirit) τοῦ(of the) (holy,)  ማቴ 12፡32

 βλασφημήσῃ(should blaspheme) εἰς(into) τὸ(the) πνεῦμα(spirit) τὸ(the) ἅγιον, ፣ማር 3፡29

 εἰς(into) τὸ(the) ἅγιον(holy) πνεῦμα(spirit) βλασφημήσαντι(having blasphemed) οὐκ(not) ἀφεθήσεται. ፣ሉቃ 12፡10

 μὴ(not) λυπεῖτε(be YOU saddening) τὸ(the) πνεῦμα(spirit) τὸ(the) ἅγιον(holy) τοῦ(of the) θεοῦ, ኤፊሶን 4፡30
πτίζοντες(baptizing) αὐτοὺς(them [persons]) εἰς(into) τὸ(the) ὄνομα(name) τοῦ(of the) πατρὸς(Father) καὶ(and) τοῦ(of the) υἱοῦ(Son) καὶ(and) τοῦ(of the) ἁγίου(holy) (spirit,)ማቲ 28፡19
12 τ(the) γὰρ(for) ἅγιον(holy) πνεῦμα(spirit) διδάξει(will teach) ὑμᾶς(YOU)  ፡፡ሉቃ 12፡12
 τ(the)πνεμα(spirit) τ(the) γιον(holy) (which) πέμψει(will send) (the) πατρ(Father) ν(in) τ(the) νόματί(name) (of me,) κενος(that (one) μς(YOU) διδάξει(will teach) πάντα(all (things) κα(and) πομνήσει(will remind)  ዮሓ 14፡26
 λήμψεσθε(YOU will receive) τὴν(the) δωρεὰν(free gift) τοῦ(of the) ἁγίου(holy) πνεύματος·(spirit;)  ስራ 2፡38

በሥራ 2፡4 ላይ የተሞሉት በመንፈስ ቅዱስ (በጸጋዉ) መሆኑን የሚገልጸዉ አንቀጽ ከፊቱ አርቲክል የሌለዉ (πνεύματος(spirit)) ሲሆን ይህን ጸጋ የሰጠዉ አካላዊዉ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ደግሞ ዴፍኒት አርቲክል በማስቀመጥ (τὸ(the) πνεῦμα(spirit)) ያመለክታል፡፡ ስለዚህ በኣንድ ቁጥር ዉስጥ ሁለቱንም ትርጉሞች አናገኛለን፡፡
 ἐπλήσθησαν(they became filled) πάντες(all) πνεύματος(of spirit) (holy,) καὶ(and) ἤρξαντο(they started) λαλεῖν(to be speaking) ἑτέραις(to different) γλώσσαις(tongues) καθὼς(according as) τὸ(the) πνεῦμα(spirit) ἐδίδου(was giving) ἀποφθέγγεσθαι(to be uttering) αὐτοῖς ሥራ2:4
በ1ኛ ቆሮ 12፡4 (የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤) ፤11 (ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።) የሚሉት ዉስጥ አንዱ መንፈስ የሚለዉ አካላዊዉን መንፈስ ቅዱስ (τὸ(the) πνεῦμα(spirit)) ነዉ፡፡ እንዲሁም በቁጥር 7 መንፈስ ቅዱስ መግለጥ (manifestation) የሚለዉ ዉስጥ መግለጥ ማለት የመንፈስ ቅዱስ መገለጫዎች (ጸጋ) ሲሆን መንፈስ ቅዱስ የተባለዉ አካላዊዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ፡፡ በቁጥር 13 በመንፈስ ተጠምቀናል እና ጠጥተናል ጠሚለዉ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ (πνεύματι(spirit)) ነዉ፡፡
4 Διαιρέσεις(Varieties) δ(but) χαρισμάτων(of gracious gifts) (are,) τ(the) δ(but) ατ(very) πνεμα·(spirit;) 
11 πάντα(all) δὲ(but) ταῦτα(these (things) ἐνεργεῖ(is working within) τὸ(the) ἓν(one) καὶ(and) τὸ(the) αὐτὸ(very) (spirit,) διαιροῦν(variegating) ἰδίᾳ(to own [space]) ἑκάστῳ(to each (one) καθὼς(according as) βούλεται.
7 κάστ(To each (one) δὲ(but) δίδοται(is being given) (the) φανέρωσις(manifestation) τοῦ(of the) πνεύματος(spirit)
 13 
κα(and) γὰρ(for) ἐν(in) ἑνὶ(one) πνεύματι(spirit) ἡμεῖς(we) πάντες(all) εἰς(into) ἓν(one) σῶμα(body) (we were baptized,) εἴτε(whether) Ἰουδαῖοι(Jews) εἴτε(or) (Greeks,) εἴτε(whether) δοῦλοι(slaves) εἴτε(or) (free (ones) καὶ(and) πάντες(all (ones) ἓν(one) πνεῦμα(spirit) ἐποτίσθημεν

በሥራ 2፡33 ላይ ‹‹የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል›› የሚለዉ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚለዉ ቃል አካላዊዉን (τοῦ(of the) πνεύματος(spirit) ) ነው፡፡
33 τ(To the) δεξιᾷ(right [hand]) οὖν(therefore) τοῦ(of the) θεοῦ(God) ὑψωθεὶς(having been put on high) τήν(the) τε(and) ἐπαγγελίαν(promise) τοῦ(of the) πνεύματος(spirit) τοῦ(the) ἁγίου(holy) 

ይህን የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል የይሖዋ ምስክሮች እንዲህ ተርጉመዋል ፡፡ ቃል የተገባለትን ቅዱስ ምንፈስ ( the promised holy spirit) ፡፡ ይህም ፍጹም ስህተት ነዉ፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ራሳቸዉ ካሳተሙት የቃል በቃል ትርጉም ስናስተዉል  ἐπαγγελίαν(promise) τοῦ(of the) πνεύματος(spirit) τοῦ(the) ἁγίου(holy) (‹‹የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል) ይላል፡፡ የተስፋ ቃሉን የሰጠዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ራሱ ተስፋዉ አይደለም፡፡ ሰለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ሆን ብለዉ በዚህ መልኩ የተሳሳተ ትርጉም ሰጥተዉታል፡፡
በ1962ቱ የአማርኛ ትርጉም እና በኪንግ ጀምስ እንግሊዝኛ ላይ ‹‹የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል እና the promise of the Holy Ghost በማለት በትክክል ተተርጉሞኣል፡፡

ስለዚህ ከላይ እንደተመለከትነዉ የይሖዋ ምስክሮች ስለ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያወራዉን የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል በመጥቀስ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ አይደለም ማለታቸዉ ስህተት መሆኑን ነዉ፡፡ ስለዚህ ስለ ምንፈስ ቅዱስ ስናወራ ሁለቱን ለይተን ማወቅ ኣለብን፡፡ (ኆኅተ ጥበብ ፣ብርሃኑ ጎበና)

በእርግጥ የይሖዋ ምስክሮች ታማኝ እና ልባም ነዉን?
1.      የጠቀሱት መዝገበቃላት መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንደ ሆነ በግልጽ ጽፎ ሳለ በተቃራኒዉ ማቅረባቸዉ ታማኝ ኣለመሆናቸዉን ያሳያል፡፡እንዲሁም ልብ ብለዉ ሀሳቡን ኣለማቅረባቸዉ ልባም ኣለሞናቸዉን ይገልጻል፡፡
2.     በግሪክ መንፈስ ቅዱስ በግኡዝ ተዉላጠ ስም መጻፉን እንደ ማስረጃ ማቅረባቸዉ ልባም ኣለመሆናቸዉን እና ግሪክን ኣለማወቃቸዉን ያሳያል፡፡እናም ድርጅቱ እምነት የሚጣልበት አይደለም ማለት ነዉ፡፡በተጨማሪም የጠቀሱት መዝገበቃላት ይህን በግልጽ ጽፎ ሳለ ልብ ኣለማለታቸዉ፣ጥራዝ ነጠቅ ጥቅስ ለማወዛገብ እና ሙሁራን ይደግፉናል ለማለት እንደሚጠቀሙ ያሳያል፡፡
3.     የጥንት ክርስቲያኖች ምንፈስ ቅዱስ አካላዊ አይደለም ብለዉ ያምኑ ነበር በማለት ሀሰት ተናግሮኣል፡፡
4.     በተጨማሪም የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት በ1914 እና በ1975 አለም ታልፋለች በማለት ያልተፈጸመ (ሀሰተኛ) ትንቢት መናገራቸዉ ሀሰተኛ እና እምነት የማይጣልባቸዉ ያረጋቸዋል፡፡

ምንም እንኳን ጅርጅቱ ‘በታማኝና ልባም መጋቢ‘ ነኝ በማለት መጽሃፍ ቅዱስን ቢጠቅስም ተግባሩ ከዚህ በተቃራኒ ነዉ፡፡ ስለዚህ ይህ ድርጅት ታማኝ እና ልባም አይደለም፡፡ ማንም ሰዉ ተነስቶ መጽሃፍ ቅዱስን ጠቅሶ  ‘ታማኝና ልባም መጋቢ‘ ነኝ ሊል ይችላል፡፡ ተግባሩ ግን እዉነታዉን ያሳያል፡፡

የይሖዋ ምስክሮች እንደሚሉት የይብራይስጡ ሩሃ ወይም የግሪኩ ኒዉማ ትርጎሞች ኣንዱ መንፈሳዊ አካላት ማለት ነዉ፡፡ልክ ነዉ፡፡ ኣብ መንፈሰዊ አካል ፣መላዕክትም …፡፡ስለዚህ የይብራይስጡ ሩሃ ወይም የግሪኩ ኒዉማ ትርጉም መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንዳል ሆነ አይናገርም ማለት ነዉ፡፡ነገር ግን በተናገሩት ተቃራኒ የይሆዋ ምስክሮች ከግል ሀይማኖታዊ አመለካከታቸዉ በመነሳት፣የግሪኩን ኒዉማ እና የይብራይስጡን ሩሃ ( ሁለቱም መንፈስ ማለት ናቸዉ) አንቀሳቃሽ ሀይል በማለት ተርጉመዋል፡፡
 በመሆኑም በግድ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ አይደለም የሚለዉን እምነታቸዉን ወደ መጽሃፍ ቅዱስ ለማስገባት ይሞክራሉ፡፡ እናም ሁሉም ክርስቲያን ይህን ማወቅ ኣለበት፡፡

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደ ኣብ እና እንደ ወልድ አካላዊ ነዉ፡፡
ስለመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ምንነት የበለጠ ለመረዳት በብርሃኑ ጎበና የተዘጋጀዉን ኆኅተ ጥበብ ያንብቡ፡፡

No comments:

Post a Comment