‘People
should examine all the evidence by examining both sides of a matter.’ Awake, 22
October 1973, p.6).
ከላይ እንደምናየዉ
የይሆዋ ምስክሮች መጽሔት የሆነዉ ፣የኦክቶበር/22/ገጽ 6 ንቁ መጽሔት ሰዎች(የይሆዋ ምስክሮችን ጨምሮ) ኣንድን ጉዳይ መረጃ
በመጠቀም ግራ ቀኙን እንዲመረምሩ ያበረታታል፡፡
በጽሓፍ ቅዱስም
ይሄንኑ ያሳስባል፡፡
·
“የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ በመንፈስ
የተነገረን ቃል* ሁሉ
አትመኑ፤+ ከዚህ
ይልቅ በመንፈስ የተነገሩት ቃላት* ከአምላክ
የመነጩ መሆን አለመሆናቸውን መርምሩ፤+ ብዙ
ሐሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+”1 ዮሐንስ 4:1
(አአት)
·
“ሁሉንም ነገር መርምሩ፤+ መልካም
የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ። 22 ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ራቁ።+1” ተሰሎንቄ 5:21(አአት)
የዚህም ጦማር
አላማ ይሄዉ ነዉ፡፡ የይሆዋ ምስክሮችን እምነታቸዉን ለማስቀየር ወይም ሌላዉ ክርስትያን በየይሆዋ ምስክሮች
ላይ ጥላቻ እንዲኖረዉ ለማድረግ አይደለም፡፡የይሆዋ ምስክሮችን አስተምሮ እዉነታዎችን በማስረጃ በማቅረብ የይሆዋ ምስክሮችም
ይሁኑ ሌሎች ክርስትያኖች አዉነታዉን እንዲረዱ መርዳት ነዉ፡፡
የይሆዋ ምስክሮች በሀይማኖታቸዉ ዉስጥ ብዙ መስዋእትነትን
የሚከፈሉ ናቸዉ፡፡ብዙ ጊዜ እየዞሩ ከኣገር ኣገር በራሳቸዉ ወጪ ተቸጋግረዉ ያገለግላሉ፡፡በእምነቱ ዉስጥ እያሉ እንኳን ሰዉ በመሆናቸዉ
በሚሰሩት ኣንዳንድ ስህተቶች ከቤተሰቡቻቸዉ፣ከዎዳጆቻቸዉ፣ከሚወዱዋቸዉ
መንፈሳዊ ጓደኞቻቸዉ የመገለልን እና የብቸኝነትን መስዋዕትነት ይከፈላሉ፡፡የዚህም ጦማር ኣንዱ አላማ የይሆዋ ምስክሮች
ይህን ሁሉ መስዋእትነት የሚከፈሉለትን ሀይማኖታቸዉን በማስረጃ እንዲማረምሩ እና ሳይረፍድ በወጣትነታቸዉ ዘመን መንገዳቸዉን እንዲያዩ
መርዳት ነዉ፡፡ ጦማሩም በተቻለዉ መጠን በአብዛገኛዉ የይሆዋ ምስክሮችን ጽሁፎችን ፣መጽሓፍ ቅዱስን እና ሌሎች
ጽሁፎችን በማስረጃነት በመጠቀም ሚዛናዊ ማስረጃ ይሰጣል፡፡
No comments:
Post a Comment