Pages

Wednesday, August 26, 2015

ይሆዋ (ጅሆቫ) ስለሚለዉ የእግዚኣብሄር ስም

እግዚኣብሔር የባህሪዉ መገለጫ የሆኑ የተለያዩ ስሞች ኣሉት፡፡ከእነዚህም ስሞች ዉስጥ ኣንዱ መጀማሪያ  በዘፍጥረት 2፡4 ላይ ይገኛል፡፡ይህንንም የእግዚኣብሔር ስም ቴትራግራማቶን( Tetragrammaton) ብለዉ ብዙዎች ይጠሩታል፡፡በግሪክ ቴትራ (Tetra) ማለት አራት ሲሆን ግራማ(gramma) ማለት ደግሞ ፊደል ማለት ነዉ፡፡ስለዚህ ቴትራግራማቶን ማለት አላት ፊደላት ማለት ነዉ፡፡ነገር ግን ቴትራግራማቶን የሚለዉ ቃል መጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ እንዳሌለ ማስተዋል ኣለብን፡፡ቴትራግራማቶን ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይህ የእግዚኣብሔር ስም በመሰራታዊዉ የኣይሁድ መጽሓፍ(ብሉይ ኪዳን) ዉስጥ አናባቢ ባሌላቸዉ አራት የአይሁድ ፊደላት ስለተጻፉና ማንበብ ስለማይቻል ነዉ፡፡
የእግዚኣብሔር ስም በመሰራታዊዉ የኣይሁድ መጽሓፍ(ብሉይ ኪዳን) ዉስጥ እንዳለዉ፣
በጥንቱ አጻጻፍ   በዘመናዊዉ አጻጻፍሁለቱም በእንግሊዝኛ ሲጻፉ YHWH(YHVH) ይሆናሉ፡፡ Aid-To-Bible-Understanding 1971.p882

ይህ የእግዚኣብሔር ስም በዚህ አጻጻፍ (ቴትራግራማቶን)በብሉይ ኪዳን ዉስጥ በብዛትእንዳለ ምንም የሚያወላዳ ነገር አይደለም፡፡
ነገር ግን ይህ የእግዚኣብሔር ስም መነበብ እንዲችል አዶናይ ከሚለዉ የእግዚኣብሔር ሌላ መጠሪያ አናባቢ ፊደላት ተወስደዉ ያህዌይ ተብሎ እንዲነበብ ተደርጓል፡፡የህዌይ ከሚለዉ ደግሞ ላቲናዊዉ ጀሆቫህ ተፈጠረ፡፡ይህ የእግዚኣብሔር ስም መምህጻረ ቃል ጃ(Ja/Jah) ወይም ያ(Ya/Yah) ተብሎም ይጠራል፡፡ይህም ሀሌሎያ (ሀሌሎጃ) የሚለዉ ውስጥ የገኛል፡፡  እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን በመሰራታዊዉ የአይሁድ መጽሓፍ ላይ ያለዉ የእግዚኣብሔር ስም ንባብ ድምጽ ስለማይታወቅ ዛሬ የምንጠቀማቸዉ ያህዌይ እና ጀሆቫህ የምንላቸዉ ስዉ ሰራሽ(መጽሓግ ቅዱሳዊ ያልሆኑ) ናቸዉ፡፡ይህ ማለት መጠቀማችን ስህተት ነዉ ማለት ሳይሆን ….
ይህም የእግዚኣብሔር ስም ትርጉም ዘጸኣት 3፡14 ላይ ያለዉን ያለና የነበረ(I AM THAT I AM) እንደሆነ ሊቃዉንት ይስማማሉ፡፡
የይሖዋ ምስክሮችም ይህ የእድዚኣብሔር ስም ትርጉም በ ዘጸኣት3፡14 ላይ ያለዉ አንደሆነ ያምናሉ(NWT 2013 ) ምንም እንኳን ዘጸኣት3፡14 ን በትክክል ባይተረጉሙም፡፡ ይይሆዋ ምስክሮች መሰረታዊዉ የብሉይ ኪዳን (Orignal Hebrew Scripture)ዉስጥ ያለዉን  የእግዚኣብሔር ስም መንበብ እነደማይቻል ያምናሉ፡፡ Reasoning p. 194-196 online lib
ይህ የእግዚኣብሄር ስም(ቴትራግራማቶን) በእብራዊያን(ብሉይ ኪዳን) መጽሓፍ ቅዱስ፡-
ይህ የእግዚኣብሄር ስም(ቴትራግራማቶን) በእብራዊያን(ብሉይ ኪዳን) መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ 6,961 ጊዜ ይጋኛል [2]፡፡በእርግጥ ይህ የእግዚዛብሔር ስም በመሰራታዊዉ የእብራዊያን(ብሉይ ኪዳን) መጽሓፍ ቅዱስ(original language text of the Hebrew Scriptures) ዉስጥ መኖሩ ምንም የሚያከራክር አይደለም፡፡

ይህ የእግዚኣብሄር ስም(ቴትራግራማቶን) በሴፕታጊነተ 70( Septuagint (LXX) መጽሓፍ ቅዱስ፡-
እዚህ ላይ በሴፕታጊነተ ( Septuagint) እና መሰራታዊዉን አዲስ ኪዳን ግሪክ መጽሓፍ ቅዱስ ማምታታት የለብንም፡፡ሴፕታጊነተ 70( Septuagint)በ280 ከክርስቶስ ልደት በፊት በቅኝ ግዛት ሳቢያ የግሪክ ቋንቋ ብቻ ለሚናገሩ አይሁዳዊያን  ከመሰራታዊዉ እብራዊያን(ብሉይ ኪዳን) (originallanguage text of the Hebrew Scriptures)መጽሓፍ ቅዱስ የተተረጎመ የብሉይ ኪዳን የግሪክ ቋንቋ የብሎይ ኪዳን መጽሓፍ ቅዱስ ነዉ፡፡ስለዚህ በሴፕታጊነተ ( Septuagint) ኣንደኛ ትርዱም ነዉ ሁለተኛ ብሉይ ኪዳን ነዉ፡፡
ይህ የእግዚኣብሄር ስም(ቴትራግራማቶን) ብሉይ ኪዳን እንደመሆኑ መጠን በሴፕታጊንት ( Septuagint) መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥም ይጋኛል [3]፡፡ ይህንንም ማስራጃ በፎቶ የይሖዋ ምስክሮች በመጽሓፎቻቸዉ አስቀምጠዋል[4,5,6]፡፡

ዋናዉ ጥያቄያችን  ይህ የእግዚኣብሄር ስም(ቴትራግራማቶን) በመሰራታዊዉ የግሪክ አዲስ ኪዳን(the original Christian Scriptures) ዉስጥ መኖር ኣለመኖር ነዉ፡፡በፎቶ የይሖዋ ምስክሮች ለማስራጃነት ያስቀመወጡዋቸዉ ሁሉም የብሉይ ኪዳን (originallanguage text of the Hebrew Scriptures)) ስለሆኑ ለአዲስ ኪዳን ማስራጃ አይሆኑም፡፡


ይህ የእግዚኣብሄር ስም(ቴትራግራማቶን) በመሰራታዊዉ የግሪክ አዲስ ኪዳን(the original Christian Scriptures)መጽሓፍ ቅዱስ፡-
የይሆዋ ምስክሮች የመጽሓፍ ቅዱስ ትርዱማቸዉ ኣንዱ አላማ የእግዚኣብሔርን ስም ማንሰራራት( restoring Jehovah's name) ነዉ በማለት በአዲስ ኪዳን ትርዱማቸዉ ዉስጥ 237 ጊዜ ይሖዋ(ጆሆቫ) ብለዉ ጽፏል[7]፡፡223ቱን κύριος ( Kyrios,ጌታ)  የሚለዉን የግሪክ ቃል ጆሆቫ በሚለዉ በመተካት፣13ቱን Θεὸς(Theos፣እግዚኣብሔር) የሚለዉን የግሪክ ቃል ጆሆቫ በሚለዉ በመተካት፣ኣንዱን ደግሞ (he,እሱ) የሚለዉን የግሪክ ቃል ጆሆቫ በሚለዉ በመተካት ነዉ፡፡
የይሖዋ ምስክሮች ለትርጉማቸዉ የተጠቀሙት መጽሓፍ ቅዱስ  መሰራታዊዉ የኮየኒ ግሪክ ጽሑፍ(The original koine Greek text) እና በታዋቂ የግሪክ ምሁራን የተጻፈ እንደሆነ ገልጻዋል[9]፡፡ የኮየኒ ግሪክ ቋንቋ በሓዋሪያት ዘመን ይነገር የነበረ እና ሓዲስ ኪዳን የተጻፈበት የግሪክ ቋንቋ ነዉ፡፡


ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ያለዉ የእግዚኣብሄር ስም(ቴትራግራማቶን) በዚህ መሰራታዊዉ(በሓዋሪያት የተጻፈ) የኮየኒ ግሪክ መጽሓፍ ቅዱስ(The original koine Greek text) ዉስጥ ኣንድም ቦታ ተጽፎ አይገኝም፡፡ይህንንም ማንም ሰዉ የይሖዋ ምስክሮችን መጽሓፍ(KIT 1969) ከዚህ በማዉረድ ማየት ይችላል፡፡ 

No comments:

Post a Comment