Pages

Friday, August 28, 2015

ዘካሪያስ 12፡10

የብሉይ ኪዳን መጽሓፍ ቅዱስ በጀመሪያ የተጻፈው በይብራይስጥ ቋንቋ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ አዲስ ኪዳን ደግሞ መጀመሪ የተጻፈው ኮይኔ በሚበለው የግሪክ  ቋንቋ ነው፡፡ይህ የግሪክ ቋንቋ በሓዋሪት ዘመን  በእስረኤል አካበባቢ እሰከ ግብጽ እና ሶሪያ ወዘተ እንደ ብሄራዊ ቋንቋ ይነገር ነበር፡፡በሌሎች ቋንቋዎች ያሉት መጽሓፍ ቅዱሶች ሁሉም ከእነዚህ የተተረጎሙ ናቸው፡፡ ከቃንቋ ባህሪ እና ከተርጓሚውም ድክመቶች የተነሳ ትርጉሞች ስለ አምላክ ቃል ሙሉ በሙሉ ትክክል ይተረጉማሉ ማለት አይደለም፡፡ በእርግጥ አንዳንዶቹ ለግል ፍላጎታቸው ሆን ብለው እንደ ፈለጋቸው ይተረጉማሉ ሌሊች ደግሞ ከዚህ ውጪ መሆነ ችግር (ለምሳሌ ካህሎት ማነስ ….) ትክክለኛውን ትርጉም ሳያስተላልፉ ይቀራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በየጊዜው ትርጉሞች እየተሸሻሉ ይሰራሉ፡፡የሆነሆኖ ግን አንዳንዴ በድንገትም ይሁን ሆን ብሎ የአምላክን ቃል ከመሰረታዊው መጽሓፍ ቅዱስ መመልከት ጥሩ ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት የግሪክ ቋንቋ የቃል በቃል ትርጉሙ ለአማኞቹ የሰራው በዚሁ ምክንያት እንደነበር ገልጾአል፡፡ በዚህ ጦማር ውስጥ የይሖዋ ምስክሮች ትርጉም ስህተት መሆኑን ለመጠቆም ለማስረጃነት የምጠቀመው ይሄንኑ መጽሓፋቸውን ነው፡፡
ከላይ ባነሳነው ሀሳብ መሰረት ተ.ዘካ 12፡10ን እንመለከታለን፡፡ ይህ ትንቢተ ዘካሪስ ጎኑን የተወጋው ማን እንደሆነ ይነግረናል፡፡
1፤ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። …. 10፤ በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።  ት.ዘካ 12፡1፣10 (1962 ትርጉም)
የምድርን መሠረት የጣለውና+ የሰውን መንፈስ* በውስጡ የሠራው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦…“በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የሞገስንና የምልጃን መንፈስ አፈሳለሁ፤ እነሱም የወጉትን ያዩታል+ ለአንድያ ልጅም እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኩር ልጅ እንደሚለቀሰው ያለ መራራ ለቅሶም ያለቅሱለታል። ት.ዘካ 12፡1፣10 (አአት ፤የይሖዋ ምስክሮች ትርጉም፡

ከላይ ከሁለቱመረ ትርጉሞች እንደምንመለከተው ተናጋሪው እግዚአብሄር (ይሖዋ) ሲሆን የተወጋው ግን ሌላ ነው፡፡ እስቲ ይህን የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል ከመሰረታዊው የይብራይስጥ መጽሓፍ ቅዱስ የቃል በቃል ትርጉም እንመልከት፡፡ የይብራይስጥ ቋንቋ ከቀኝ ወደ ግራ እንደሚነበብ ያስተውሉ፡፡

ከይብራይስጡ መሰረታዊ መጽሓፍ ቅዱስ ስንመለከት ተናጋሪው እግዚአብሄር (ይሖዋ) ሲሆን የተወጋው  አንድ መሆናቸውን እንመለከታለን፡፡እናም በአጭሩ ያህዌይ (ይሖዋ) እግዚአብሄር እኔን የወጉኝን ይመለከታሉ ይላል፡፡
 said the LORD (Yahewe), which stretches forth the heavens, and lays the foundation of the earth, and forms the spirit of man within him….And I will pour upon the house of David, and upon the inhabitants of Jerusalem, the Spirit of grace and of supplications: and they shall look upon me whom they have pierced, KJV
ሌሎች የእንግሊዝኛ ትርጉሞች በትክክል በዚሁ መልክ መተርጎማቸውን ከዚህ ድር ገጽ ይመልከቱ፡፡ የእብራዊያን የቃል በቃል ትርጉምም ከዚሁ ድረገጽ የተወሰደ ነው፡፡
በአዲስ ኪዳን እንደምንረዳው እና ማስረጃ ማጣቀስ የማያስፈልገን ግልጽ ነገር ስለ እኛ የተወጋው ክርስቶስ ነው፡፡ ዘካ 12፡10 ደግሞ ይህ የተወጋው ያህዌ (ይሆዋ ) መሆኑን ይገልጽልናል፡፡ ያህዌ የወጉኝን እኔን ያዩኛል ይላልና፡፡ ያህዌ ማለት ያለ እና የነበረ (ዘጸኣት3፡14) የሚልትርጉም ሲሆን እኔ እግዚአብሄር አልለወጥም (ት.ሚልክያስ 3፡6) የሚለው የአምለክ የባህሪ ስም ነው፡፡ እየሱስም የማይለወጥ መሆኑን አዲስ ኪዳን እየሱስ ትናንትም፣ዛሬም ወደፊትም ያው ነው (ዕብ 13፡8) በማለት ያህዌ መሆኑን (ዮሓ 8፡58) ይገልጻል፡፡
በእርግጥ የይሖዋ ምስክሮች እንደትርጉማቸው፣የተወጋው ያህዌ አይደለም ይላሉ፡፡ አንዳንዶች የይሖዋ ምስክሮች ሆን ብለው የክርስቶስን አምላክነት (ያህዌነት) ለመደበቅ ያረጉት ነው ይላሉ፡፡ኦረቶዶክሶች ግን የተወጋው ያህዌ መሆኑን ያምናሉ፡፡ እናም የኦርቶዶክሶች ትርጉም ምናልባትም ባለማስተዋል የተደረገ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ከእምነቱ ጋር አይሄድም፡፡
በአማርኛ እንህ ቢተረጉም ትክክለኛ ምልዕክቱን ይይዛል፡፡

1፤ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ ይላል። …. 10፤ በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እኔም (upon me) ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።  ት.ዘካ 12፡1፣10 (1962 ትርጉም)

No comments:

Post a Comment