Pages

Tuesday, October 10, 2017

የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት እየሱስን አታላይ ይለዋል



† ከታላቁ #አስተማሪ #ተማር፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት እየሱስን አታላይ ይለዋል፡፡መጽሐፍ ቅዱስስ ምን ይለዋል? ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። 1ኛ ቆሮ 16፡22
የይሖዋ #ምስክሮች ድርጅት በ2016 ከታላቁ አስተማሪ ተማር በሚል 256 ገጾች ያሉት አንድ መጽሐፍ አሳትሞአል፡፡ ይህም ታላቅ አስተማሪ የተባለው እየሱስ ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ ታላቅ አስተመሪ ምንድን ነው የምንማረው? ለመሆኑ እየሱስ በየይሖዋ ምስክሮች አስተምሮ መሰረት ታላቅ አስተማሪ ነው?
በአርግጥ አንድ የይሖዋ ምስክር እኛ እየሱስ ምንም ሐጢአት እንዳልሰራ ነው የምናምነው ብሎ አንድ ጽሑፋቸውን ሊያሳያችሁ ይችላል፡፡ ይህ አይሆንም የሚል እምለት የለኝም፡፡ የይሖዋ ምስክሮች አስተምሮ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ስለሆነ እየሱስ ሃጢኣት ሰርቶኣል የሚል እና በተቃራኒው ድገሞ እየሱስ ሃጢአት አልሰራም የሚል ከየይሖዋ ምስክሮች ጽሁፎች መግኘት ቀላል ነው፡፡ እየሱስ ሃጢኣት አልሰራም ለሚለው ማስረጃ ማቅረብ በጣም ቀላል እና ብዙ ሰዎችም ያለግርታ የሚያምኑት ነገር ነው፡፡ ነገር ግን እየሱስ ሃጢኣትን ሰርቶኣል የሚለው ለብዙ ክርስቲኖች አጅግ ግር የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የይሖዋ ምስክሮችን ጽሁፎች እና አስተምሮ ላነበበ ሰው የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት እየሱስ ሐጢአት ሰርቶኣል ብሎ እንደሚያምን መረዳት ምንም አያስችግረውም፡፡
1. እየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ስለመነሳቱ መንፈስ ሥጋ የለውም እኔ ግን አለኝ በማለት መንፈስ ለመሰላቸው በማስረጃ እንዲህ ገልጾእል፡፡
<< እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።›› ሉቃ 24፡39፡፡ ይህን የክርስቶስን ምስክርነት በተመለከተ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት እንዲህ ይላል፡፡ እየሱስ እንዲህ ያለው በሥጋ ስለተነሳ አይደለም፣ ነገር ግን የተነሳው በመንፈስ ሆኖ ሳለ ከሞቱ በፊት በሥጋ እና በአጥንት ያውቁት የነበሩት እንዲያምኑ ነው ይላል፡፡ በሌላ አገላለጽ እየሱስ በሥጋ ተነሳሁ ያለው በእውነት በሥጋ ስለተነሳ ሳይሆን ደቀመዛሙርቱን ለማሳመን ነው ይላሉ፡፡ (እነዚህን የይሖዋ ምስክሮች ጽሁፎችን ማንበብ ይቻላ፡-“Make Sure of all Things, Hold Fast to What is Fine” [1953 edition, p. 314]፣መመራመር ፣ገጽ 334)
ስለዚህ እንደ የይሖዋ ምስክሮች አስተምሮ እየሱስ ሰዎች እንዲያምኑት ብቻ ያለሆነውን ነገር ሆንኩ በማለት ፣በአታላይነት የሐሰት ምስክርነትን ሰጥቶኣለ ማለት ነው፡፡ በሥጋ ነው የተነሳሁት በማለት ዋሽቶአል እንደ የይሖዋ ምስክሮች እምነት፡፡ በአጠቃላይ ክርስቶስ በሐሰት አትመስክር የሚለውን ትዕዛዝ በመጣስ ሐጢኣት ሰርቶኣል፡፡
2. የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቀን እናቱን ‹‹አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ›› ስላላት ጉዳይ ትዕዛዝዋን ስላልተቀበለ (firmly rejected Mary’s direction) ነው በማለት እንዲህ ይገልጻሉ፡፡
"ኢየሱስ ልጅ ሳለ ለእናቱና ለአሳዳጊ አባቱ ይ-ታ-ዘ-ዝ ነበር። በዚህ ጊዜ ግን ሙሉ ሰው ስለ ነበር በማርያም ፈቃድ የማይመራ መሆኑን በደግነትና ጥብቅ በሆነ አነጋገር ገልጾላታል ። እርሷም እርማቱን በትሕትና ተቀብላለች።" መመራመር፣ገጽ 260፡፡
እንዲውም በመጠበቂያ ግንብ፣2000፣ሴፕቴምበር፣15፣ገጽ 11 ላይ ትዕዛዝዋን ያልተቀበለበትን ምክንያት 30 አመት የሞለው በማለት እንዲህ ይገልጻሉ ይገልጻሉ፡፡
‹‹ኢየሱስ “አንቺ ሴት፣ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?” ሲል የሰጠው መልስ ለቀረበው ማሳሰቢያ ወይም ሐሳብ ተ-ቃ-ው-ሞ ለመግለጽ የሚያገለግል በድሮ ዘመን የሚሠራበት የአጠያየቅ ዘይቤ ነው። ኢየሱስ ማርያም ያቀረበችውን ሐሳብ የተቃወመው ለምንድን ነው? አሁን 30 ዓመቱ ነው። >>
ከእነዚህ የይሖዋ ምስክሮች ሐሳብ የምንረዳው እየሱስ ለእናቱ አለመታዘዙን ወይም የእናቱን ትዕዛዝ መቃወሙን ነው፡፡ በሌላ መንገድ ክርስቶስ ለእናቱ ያይታዘዝ እና አናቱን የሚገስጽ አመጸኛ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እናትህን አክብር የሚለውን ትዕዛዝ በመጣስ ሐጢኣት ሰርቶኣል ማለት ነው፡፡
መጽሀፍ ቅዱስስ ስለ ክርስቶስ ምን ይላል፡-
በመጽሐፍ ቅዱስ ለሚያምኑት መጽሓፍ ቅዱስ እንኳን እየሱስን ዋሾ ፣አታለይ እና ሀጢአተኛ ሊለው ይቅርን ፤ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ (1ኛ ጴጥ 2፡22) ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ (ዕብ 4፡15) በማለት ምን ሃጢኣት እንዳሌለበት ይነግረናል፡፡ እግዚኣብሄር አብም የምወደውን ልጄን ስሙ ያለው ተንኮለኛውን አታላይ ልጅ አይደለም፡፡ መጽሓፍ ቅዱስ ሀሰተኛ እና አታላይ ማን እንደሆነ እና እውነትን የሚናገር ምን እንደሆነ እንዲህ ይገልጻል፡፡
‹‹እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። እኔ [እየሱስ] ግን እውነትን የምናገር ስለ ሆንሁ አታምኑኝም።›› ዮሐ 8፡44-45
አረማዊው ጲላጦስ እንኳን የክርስቶስን ንጽህና ሲመሰክር እኛ በመጽሐፍ ቅዱስ እናምናለን የምንለው ግን ክርስቶስን ተንኮለኛ መድረግ በጣም ከባድ ክህደት ነው፡፡
ጲላጦስም ደግሞ ወደ ውጭ ወጥቶ። እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ እንዳላገኘሁበት ዮሐ 19፡4
ተንኮለኛ (ውሸታም) ካረግነው በኋላ ከእሱ ተማሩ ማለት እኛም ተንኮለኛ(ውሸተኛ) እንሁን ማለት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እንደ የይሖዋ ምስክሮች እምነት ክርስቶስ እንኳን እኛን ሊያድነን ይቅርና ራሱ አዳኝ የሚፈልግ ሃጢኣተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ክርስቶስን ሃጢኣተኛ ካልን እኛ ዛሬም አልዳንም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ በእሱ ቁስል ተፈዋስን ይላል፡፡ ከታላቁ አስተማሪ ተማር፡፡ባለፉት ጽሁፎቼ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት እንደሚዋሽ እና አማኞቹም እንዲዋሹ እንደሚያበረታታ ገልጼ ነበር፡፡
አይሁዶች እኛ ህግ አላን ይላሉ፡-
ክርስቶንም ሊገድሉት የፈለጉት በህጋቸው መሰረት ነው፡፡ ሁሌም በክርስቶስ ላይ ጥፋት ሲፈልጉ ነበር፡፡ በአይሁድ ህግ ከሚያስገድሉት ህጎች ውስጥ ለቤተሰቡ አመጸኛ የሆነ ልጅ፣ ከእግዚኣብሄር ጋር እኩል ነኝ በማለት እግዚኣብሄርን መስደብ እና ዝሙት ናቸው (ዘዳ 12፡18-21፣ዘሌዋ 24፡10-23፤ዘዳ 22፡24)፡፡ ለዚያውም በድንጋይ የሚያስወግሩ ናቸው፡፡ ዝሙት ሰራች የተባለችውን ሴት ወደ እየሱስ ሲያመጥዋት እኛ ህግ አለን በህጋችን መሰረት መወገር አለባት ማለታቸውም ለዚህ ነው፡፡
አይሁድ ክርስቶስ ላይ በተደጋጋሚ ድንጋይ ሲያነሱ የነበረው እግዚአብሄር ነኝ በማለቱ ነበር፡፡ የህም ህጋቸው በዘሌዋ 24፡10-23 ላይ ያለው ነው፡፡ ይህንንም ሲደርጉ ክርስቶስ መልካም ሥራ እንደሚሰራ በመመስከር ጭምር ነው፡፡
‹‹ አይሁድም መልሰው። እኛ ሕግ አለን፥ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባዋል፥ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና አሉት።››ዮሐ 19፡7
‹‹ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።›› ዮሐ 5፡18፡፡
‹‹ አይሁድም። ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።›› ዮሐ 10፡33
ከዚህ ውጪ አንድም ጊዜ አይሁዶች እየሱስን ህጋቸውን ጠቅሰው ሲከሱት አንመለከትም፡፡ ክርስቶስ ለእናቱ የማይታዘዝ ሆኖ ቢሆን ኖሮ በዘዳ 12፡18-21 መሰረት በከሰሱት ነበር፡፡
መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና፡-
ለእኛ ለምናምን እየሱስ ሃጢኣተኛ አይደለም፡፡ አላታለለንም፡፡ አታላይ እና ውሸታም ዲያቢሎስ ነው፡፡ክርስቶስ በሥጋ ተነሳሁ ሲለን እንድናምነው እያታለለን አይደለም፡፡ እውነትም በሥጋ ነው የተነሳው፡፡ ገና ከመሞቱ በፊት የለበሰውን ሥጋ ይዞ እንደሚነሳ እንዲህ ገልጾአል፡፡
‹‹ ኢየሱስም መልሶ። ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።…፤ እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር›› ዮሐ 5፡19-21፡፡
‹‹ …ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ። ዮሐ 2፡19-22
ይህን ብሎ የጠራው ከመሞቱ በፊት የለበሰውን ሥጋ ነበር፡፡ እንደ ተናገረው የለበሰውን ሥጋ ይዞ መነሳቱን ማቴዎስ እንዲህ ገልጾታል፡፡
‹‹ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።›› ማቴ 28፡6
ስለዚህ እየሱስ በመንፈስ አይደለም በሥጋ ነው የተነሳሁት መንፈስ ሥጋ የለውም እኔ ግን አለኝ ሲል ሊያታልለን ሰይሆን እውነቱን እየነገረን ነው፡፡ እኛም እንደ ደቀመዛሙርቱ መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል እናምናለን፡፡
‹‹እኔ [እየሱስ] ግን እውነትን የምናገር ስለ ሆንሁ አታምኑኝም።›› ዮሐ 8፡45
‹አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን ኣለኝ፡-
ክርስቶስ ‹‹አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምነ ኣለኝ ›› ሲልም እናቱን ትዕዛዝ አለመቀበሉ ሳይሆን ከአንቺ ጋር ምን ጥል (ጸብ) አለኝ በማለት እስዋን የሚያሰቀይምበት ምንም ጸብ እንዳሌለው እየገለጸላት ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ አይሁዶችም በከሰሱት ነበር እንዲሁም ክርስቶስ ትዕዛዝዋን ባልፈጸመ ነበር፡፡ ወይም እየሱስም የሚቃወመውን ነገር እየፈጸመ ነው ማት ነው፡፡ ማሪያምም እሱ ይህን ካለ በኋላ ወዲያው ጋኖቹን ሙሉ ማለትዋ ሀሳብዋን ስላልተቃወመ ነው፡፡ ስለዚህ እየሱስ እናትህን አክብር የሚለውንም ትዕዛዝ አልጣሰም፡፡ 30 አመት ስለሞላውም በእናቱ ላይ አላመጸም፡፡ ሰይጣንን ክርስቶስ በገሰጸ ጊዜ ሰይጣን የእግዚኣብሄር ልጅ ሆን ከአንተ ጋር ምን አለን ልታጠፋን መጣህን ብሎታል፡፡ በመቀጠልም ሰይጣን የእየሱስን ትዕዛዝ መፈጸሙን እንመለከታለን፡፡ ሰይጣን እየሱስን እንዲህ ሲል ለአንተ የማንታዘዝበት ምክንያ የለንም ማለቱ ነው እንጂ የእየሱስን ትዕዛዝ መቃወሙ አልነበረም፡፡
እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ (1ኛ ጴጥ 2፡22)


53 Comments
Comments

Redeate Shewakena Betam teru gelach tsehuf new enamesegenalen selam! Min albat welajochachehu yemiluachehun atesmu eyesusem alsemam 30 amet honot kadege behuala eyalu sewochen wedenesu derejet lememelmel eyetetekemubet yehonal yehene. Betam tibebegnoch nachew eko. Seytan ke eyesus gar yeneberew negeger eyesus le mariam kalat gar kal be kal temesasay mehonu netebu yemayashama endehone beglts yasayal! Enamesegenalen wendemachen!
Show more reactionsReplySeptember 29 at 2:30pm
Manage
Marta Mar · Friends with Dorka Jw and 5 others
Hhhhhhhh yanta fetra selehona aygrmanem lelas yemtcamer yelahem?
Show more reactionsReplySeptember 29 at 8:33pm
Manage
Kidist Getachew · 13 mutual friends
አምላክ አትዋሽ በሀሰት አትመስክር ይላል። አንተ ደሞ ትዛዙን እየተላለፍክ ነው ይቅር ይበልክ
Show more reactionsReplySeptember 29 at 9:50pm
Manage
Habtamu Mulugeta
Habtamu Mulugeta ዋው ምርጥ ገለፃ ፡አንተ/አንቺ አራ እሔን ያክል ውሸታምና አሥመሣይ ናችው ማለቴ የኦርቶክስ ተዋእዶ ቤተ ክርስቲያን?እስቲ ያልበላሕን ለምን ታካለህ ልክ እንደ እርጎ ዝብ ለነገሩ ዝንብ ናችው እኮ ሊያውም ተናካሽ ዝንብ ፡ እስቲ ዝም በል
Show more reactionsSeptember 29 at 9:55pm
Manage
Selam Selam እኔ ማስረጃ ጠቅሼ እንደጻፍኩ እናንተም እንዲሁ አርጉ፡፡ ካልሆነ ግን በስሜታዊነት ከመሳደብ ባለፈ ምንም ነገር ማለት አለማቻላችሁን ያመለክታል፡፡ ከጠቀስኳቸው ውስጥ ውሸት የምትሉትን ጥቀሱ፡፡
Show more reactionsReply
1
September 30 at 10:09am
Manage
Selam Selam ድርጅታችሁ (የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት) እየሱስ << እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ ›› ያለው በሥጋ ስለተነሳ አይደለም፣ ነገር ግን የተነሳው በመንፈስ ሆኖ ሳለ ከሞቱ በፊት በሥጋ እና በአጥንት ያውቁት የነበሩት እንዲያምኑ ነው ማለቱ ውሸት ነው? ይህ ውሸት ከሆነ እናንተ ከድርጅታችሁ ተለይታችሁ እየሱስ በሥ...See More
Show more reactionsReply
1
September 30 at 10:09am
Manage
Mesi Odaa
Mesi Odaa koment mitsetewm Antew nek?kkkkkkkkk
Show more reactionsReplySeptember 30 at 3:53pm
Manage
Selam Selam መልስ ነው የሰጠሁት፡፡ በኮሜንት የጻፍኩት ለአንባቢ እንዲመች ነው፡፡ ነገር ግን ይሄ ትልቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ከዚህ የሚሻለው አንድ ጠቃሚ ነገር ብትናገሪ ነው፡፡
Show more reactionsReplySeptember 30 at 7:52pm
Manage
Selam Selam ስለዚህ ከስሜታዊነት በጸዳ መልኩ በማስረጃ ሀሳባችሁን አቅርቡ፣ካልሆነ ግን አንባቢው ይታዘባችኋል፡፡ ካለማስረጃ ሐሰት ብቻ ማለት ሐሳቡን ሐሰት አያረገውም፡፡ ይልቁንም የቀረበውን ሐሳብ እውነትነት ያጠናክራል፡፡
በተረፈ እየሱስን እጅግ ስለምወደው እሱ ያልሆነውን ሆነ ብለው ሐሰተኛ እና አታላይ ሲያረጉት ያሳክከኛል፤ዝም ማለትም አልችልም፡፡

Show more reactionsReply
1
September 30 at 10:09am
Manage
Kidist Getachew · 13 mutual friends
What a joke I'm out this is Wasting time with Beli people
Show more reactionsReply
1
September 30 at 10:33am
Manage
Selam Selam Kidist Getachew This the only way you have to exit. The Jew blindly opposed Jesus because they had nothing truthful to say against him. Respectfully, this fb is intended for Amharic readers and speakers.I know you are capable of this.I would like to encourage you to write in Amharic. I also want you to stay in the discussion.
Show more reactionsReplySeptember 30 at 10:45am
Manage
Selam Selam የምሥራቹ ቃል ለምን ከጓደኝነቱ ብሎክ አደረገኝ ? የይሖዋን ህዝቦች ስለሚሳደብ ነው ይላል፡፡ ይህ ሐሰት ነው፡፡ ባይሆን ኖሮ በማስረጃ የተሳደብኩትን ባሳየ ነበር፡፡ እውነታው እውነት በእጁ ስለሌለ እና መወያየት ስለማይችል ነው፡፡ ማን እየተሳደበ እንደሆነ ማንም ሰው የዚህን ፌስቡክ ጽሑፎች ከነአስተያየታቸው በማንበብ መረዳት ይችላል፡፡ ይሖዋ ምስክሮች ውይይትን መቋቋም ሲቅታቸው የሚተቀሙት ዘዴ አንዱ ብሎክ ማድርግ ነው፡፡ ግንባር ቀደሙ ተባረክ ደምስ ነው፡፡ መጀመሪ መወያየት ጀመርን እየከበደው ሲመጣ ብሎክ አደረገኝ፡፡ ስሱን ተከትላው አሁንም ብዙዎቹ ይህን አርገዋል፡፡ አሳፋሪው ነገር የምሥራቹ ቃል የተባለውም ይሁን ተባረክ ደምስ እኔን ብሎክ ካደረጉ በኋላ እኔ መልስ በማለሰጥበት ሁኔታ ለመመለስ መሞከራቸው ነው፡፡ Kidist Getachewu ብትሆንም የምሥራቹ ቃል በሚባለው ሰው የምትመራ ስለሆነች ይህን ማድረግዋ አይቀርም፡፡ ቢያንስ መልስ ከመስጠት ትቆጠባለች፡፡ ምናልባት በራስዋ አዕምሮ መመራት ከጀመረች መልካም ውይይት ሊኖረን ይችላል፡፡
Show more reactionsReply
1
September 30 at 11:17am


  Show more reactionsReplySeptember 30 at 11:18am
Selam Selam የይሖዋ ምስክር ለሆነው የምሥራቹ ቃል ለተባለው የተሰጠ መልስ፡፡ ይህ ሰው ብሎክ ስላደረገኝ መልሱን መስጠት የምችለው እዚህ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ሰው ብሎክ እንደሚደርግኝ አውቅ ነበር፡፡
የምሥራቹ ቃል የተባለው ይህ ሰው በSeptember 21 2017at 10:07pm ስለስላሴ የተወሳሰበ የስላሴ ትምህርት በሚል ርዕስ ስር ስለ ስላሴ ጽፎ ነበር፡፡ በዚህም ጽሁፉ አብ ከወልድ ይበልጣል የሚለውን የመጽሐ...See More

Show more reactionsReply
1
September 30 at 12:27pm
Manage
Redeate Shewakena Yemidenk new! Kelelaw ye kerestena haymanot lemeleyet ena enesu yemifetruten ye amlak mesel lemagzef ye kerestos sem be Christianu hiwot lay yemichawetewen mina betam masanes neberebachew. Yehe teks (ke melaekt yetegnawem lej alemebal) metshaf kidus lay denget sewoch eyesus melak new belew endaysetu yetetsafe eskimesel deres ye eyesusen melak alemehon gelts argotal.
Manage
Selam Selam be metsihaf kidus lemiyamin melsu ale. Sile qalu amlak yetemesegene yihun.
Manage
Selam Selam ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ [የእየሱስ] ነው፤ዮሐ 16፡15
Show more reactionsReply
1
September 30 at 12:41pm
Manage
Redeate Shewakena Sewen yemimeraw mereja mehon alebet. Tenkara anegager be tenkara mekneyat medegef alebet tamagnenet endinorew (weshetam...) Lenezih tsehufocheh melash yemihon beki neger medrek lay sikerb lemayet hulem gugut lay nen yehenen tomar yemeneketatel sewoch. Bekebadu mizan yemidefu temehertochen new eyeyen yalenew enezih tsehufoch lay. Enamesegenalen wendemachen selam!
Show more reactionsReply
1
September 30 at 1:07pm
Manage
Ribka JW Rita · Friends with Redet Man Jw and 47 others
bibel mejemriya meremer aderg seme lematfat medregew tegel ayesakam bezu atelfa

Show more reactionsReplyOctober 1 at 9:19pm
እኛ የይሖዋ ምስክሮች መጽሃፍ ቅዱስን መሰረት አርገን ነው የምናምነው። የውልህ ሰላም ሉቃስ 2439 ላይ "እና ራሰ መሆኔን እድታውቁ እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ ደግሞም ዳሳችሁ እዩ መንፈስ በኔ ላይ እደምታዩት ስጋና አጥንት የለዉምና።" ነው የሚለው ስለዚህ እኛ የይሖዋ ምስክሮች እየሱስ የተነሳው በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ነው ብለን ነውየምናምነው።በ1 ጴጥ 318 ላይም "............. በስጋ ሞተ በመንፈስ ግን ህያው ሆነ''ነው የሚለው። ስለዚህ እንተ ያልከው ሃሳብ ከእዉነት ይራቀ ነው። ለላው ደግሞ ዩሐ 23,4 ላይ "በቃና በተደረገው የሰርግ ድግስ ላይ የወይን ጠጅ ባለቀ ጊዜ የእየሱስ እናት:- የወይን ጠጅ አኮ የላቸውም አለችው። እየሱስም:- አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዘዬ ገና አልደረሰም አላት።'' ስለዚህ እየሱስ ፍጹም ስለነበረ በማሪያም ፈቃድ የማይመራ መሆኑን በደግነትና ጥብቅ በሆነ መንገድ መግለጽ ስለፈለገ ነው። ይህም ለናቱ ታዛዥ አለመሆኑን አያሳይም? ምክንያቱም ዮሐ26-9 ላይ ብትመለከተው ስድስት ጋኖችን በዉሃ አንዲሞሉ ካረገ በሗላ ወደ ወይን ጠጅ አንደቀየራቸው ይገልጻል። ይህ ደግሞ ማርያምን አንደታዘዛት ይገልጻል።አንግዲያው የውልህ ወድሜ መሰረተ ቢስ በሆኑ የተጣመሙ ቃላት የይሖዋ ምስክሮችን አስታለሁ ብለህ አታስብ፣አትርፉ ከንቱ ድካም ነው። አኛ የይሖዋ ምስክሮች ደግሞ የምን መራው ሁሉን ቻይ፣ የጽንፈአለም ፈጣሪ፣ሉአላዊው ጌታ በሆነው ይሖዋ ነው። አንኳን ተራ ሰው ይቅርና ሰይጣንም ሊያስተን ኣይችልም። ምክንያቱም ይሖዋ ምስክሮቹ ስለሆንን በመንፈስ ቅዱስ ሃይሉ ይረዳናል።
Reply
1
እና ደግሞ እየሱስ "አንች ሴት ካንቺ ጋር ምን አልኝ?" ሲል የናቱን ትዛዝ ለመቀበል ሳይሆን ካንቺ ጋር ምን ጥል(ጸብ) አለኝ በማለት እሷን የሚያስቀይምበት ምን ጸብ አደለኤለው እየገለጸላት ነው። ብለህ የተረጎምከው ከእውነት ይራቀ ነው። ምክንያቱም ማሪያም የተየቀችው የወይን ጠጁ አያለቀ ሲሀድ "የወይን ጥጁ እልቆባቸዋል ብላ ነው። ስለዚህ ከጥል ወይም ከጸብ ምንም ይሚያገናኘው ነገር አደሌለ ግልፅ ነው። ከዚህ ይልቅ ቀደም ሲል እዳልኩት እና በጉዳዩም ላይ እየሱስና ማሪያም ስለማይመለከታቸው ነው። ግን እየሱስ ጉዳዩ ባይመለከታቸውም አናቱን ማሪያምን ታዟታል።
እና ደግሞ እየሱስ "አንች ሴት ካንቺ ጋር ምን አልኝ?" ሲል የናቱን ትዛዝ ላለመቀበል ሳይሆን ካንቺ ጋር ምን ጥል(ጸብ) አለኝ በማለት እሷን የሚያስቀይምበት ምን ጸብ አደለኤለው እየገለጸላት ነው። ብለህ የተረጎምከው ከእውነት ይራቀ ነው። ምክንያቱም ማሪያም የተየቀችው የወይን ጠጁ አያለቀ ሲሀድ "የወይን ጥጁ እልቆባቸዋል ብላ ነው። ስለዚህ ከጥል ወይም ከጸብ ምንም ይሚያገናኘው ነገር አደሌለ ግልፅ ነው። ከዚህ ይልቅ ቀደም ሲል እዳልኩት እና በጉዳዩም ላይ እየሱስና ማሪያም ስለማይመለከታቸው ነው። ግን እየሱስ ጉዳዩ ባይመለከታቸውም አናቱን ማሪያምን ታዟታል።
Selam Selam Nahom Seid ሰሞኑን ትንሽ የሥራ ውጥረት ኖሮብኝ ነው ውይይቱን በቅርቡ እንቀጥላለን፡፡ አንተም እንደማትጠፋ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
Habtemariam Ch Tiru new
Selam Selam Nahom Seid ‹‹እኛ የይሖዋ ምስክሮች መጽሃፍ ቅዱስን መሰረት አርገን ነው የምናምነው።›› ማለትህ መልካም፡፡ ነገር ግን ከቃል ባለፈ በተግባር ማመን ኣለብን፡፡ ድርጅትህ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምን ከሆን ለምን በመጽሐፍ ቅዱስ ያሌሉት ቃለት ይጨምራል? ከብዙዎቹ በጥቂቱ ቆላ 116-20፤ፊልጵ 29 እና 1 ቆሮ 1527፡፡ማስረጃ ዎቹን ከሚቀጥሉት ስዕሎች ተመልከት፡፡ ለምን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያዛቸውን ነገሮች አይፈጽምም? አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸልዩ ይላል እናንተግን አታደርጉም፤ እናንተ ደግሞ እግር ተጣጠቡ ይላል እንተግን አታደርጉም እንዲሁም ማንም ሰው የአለምን ፍጻሜ ቀን ( የአርማጌዶንን ቀን) አያውቅም ይላል ድርጅታችሁ ግን 1914 እና 1975 አርማጌዶን ይፈጸማል ብሎ ነበር ነገር ግን ሰይሆን ቀረ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ቢያም ኖሮ እንዲሁም አምላክን ቃል የሚያምን ቢሆን ኖሮ ድርጅታችሁ የአለምን ፍጻሜ ትንቢትን ባልተነበያም፤ሐሰተኛ ነብይም ባልሆነ ነበር፡፡ እንግዲህ በትክክል ድርጅትህ በመጽሐፍ ቅዱስ ማመን ኣለማመኑን በተጨማሪ መርምር፡፡
Selam Selam Nahom Seid በፊልጲስዩስ 29 ላይ ሌላ የሚለውን ቃል ከየት አመጣችሁ?
  


Selam Selam Nahom Seid በቆላስይስ 116,17,20 ላይ ያሉትን ሌሎች የሚሉትን ቃላት ከየት አመጣችሁ?





Selam Selam Nahom Seid 1 ቆሮንቶስ 1527 ላይ ያለውን አምልከ የሚለውን ቃል ከየት አመጣችሁት?





Selam Selam Nahom Seid ታዲያ ድርጅታችሁ ታማኝ ነው?
Selam Selam Nahom Seid ‹‹ስለዚህ እኛ የይሖዋ ምስክሮች እየሱስ የተነሳው በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ነው ብለን ነው የምናምነው።›› ላልከው ይሄን እኔም ብዬኣለሁ፡፡
እየሱስ እናንተ እንደምታስተምሩት የተነሳው በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ከሆነ ለምን መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውም እኔ ግን አለኝ ተመልከቱ ለምን ኣለ ? በመንፈስ ከሆነ የተነሳው ለምን መንፈስ አይደለሁም አለ ለደቀመዛሙርቱ ? ያለሆነውን ነገር ለምን ሆንኩ ይላል?
ድርጅታችሁ ይህን ሲመልስ ደቀመዛሙርቱ እንዲያምኑት ነው ይላል፡፡ ስለዚህ እንደድርጅታችሁትምህርት እንዲያምኑት ሲል እየሱስ ያለሆነውን ሆንኩ ብሎኣል ማለት ነው፡፡ ደቀመዛሙርቱን አታሎኣቸዋል፣ዋሽቶኣቸዋል፡፡ ስለዚህ እንደ ድርጅታችሁ ትምህርት እየሱስ በሐሰት መስክሮኣል፡፡ ሐጢኣት ሰርቶኣል፡፡ አንተ ግን ድርጅትህ በሚለው የማታምን ከሆነ መልካም፡፡ ካልሆነ ግን እውነታው ይህ ነው፡፡
እየሱስ ይህን መልስ የሰጠው እንዲሁ አይደለም መንፈስ ነው ብለው ለተጠራጠሩት መንፈስ ኣለመሆኑን ሲያረጋግጥላቸው ነው፡፡
እየሱስ መንፈስ ስጋና አጥንት የለውም እኔ ግን ኣለኝ ስለማለቱ የአማርኛው ትርጉም ግር ካለህ የራሳችሁን የእንግሊዝኛ ትርጉም ቀጥሎ አያይዤልሃለሁ፡፡
Selam Selam Nahom Seid NWT 2013 Luk 2439



Selam Selam Nahom Seid እየሱስ እንዴት ነው የተነሳው? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና ›› ማቴ 286፡፡ ምን ነበር የተናገረው? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ ኢየሱስም መልሶ። ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።›› ዮሐ 219፡፡ ይህን ቤተመቅደስ ሲል ምን ማለቱ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር ›› ቁጥር 21፡፡ ሰውነቱ እንደሚል አስተውል፡፡ ታዲያ ደቀመዛሙርቱ ከሙታን ከተነሳ በኋላ በዚህ መልኩ (ከመሞቱ በፊት የለበሰውን ሥጋ ይዞ) እንደተነሳ አመኑ? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ›› ቁጥር 22፡፡ እኛም ክርስቲኖች እንዲሁ እናምናለን፡፡
Selam Selam Nahom Seid <<በስጋ ሞተ በመንፈስ ግን ህያው ሆነ ›› 1 ጴጥ 318::ይህን በመጥቀስ እየሱስ የተነሳው በመንፈስ ብቻ ነው ብለሃል፡፡ ከላይ ግን እንደ ተረዳነው እየሱስ የተነሳው ከመሞቱ በፊት የለበሰውን ሥጋ ይዞ ነው፡፡ ታዲያ <<በስጋ ሞተ በመንፈስ ግን ህያው ሆነ ›› ሲል ምን ማለቱ ነው? ይህን ለመመለስ እየሡስ ምንድን ነው የሚለውን መመለስ ተገቢ ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት በብዛት እየሱስ ማን እንደሆነ እንጂ ምን እንደሆነ በተገቢው አያስተምርም፡፡ ስለዚህ አማኞቹም ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መረዳት ይቸገራሉ፡፡ የእየሱስ ምንነት ማለት ባህሪው ማለት ነው፡፡ ፈረስ ምንድን ነው የሚለውን ካላወቅን ፈረስን ከሌሎች እንስሶች መለየት አንችልም፡፡
Selam Selam Nahom Seid እየሱስ ሰው ነው፡፡እንዲሁም እየሱስ እግዚኣብሄር (አምላክ) ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ብሎ ይጠረዋል (ማር 838)፡፡ የሰው ልጅ ማለት ሰው ማለት ነው፡፡ ሰው መንፈስ ሳይሆን የሚጨበጥ መሆኑን ሥጋ በማለት ይገልጻል፡፡ ‹‹ ቃልም ሥጋ ሆነ፤›› ዮሐ 114፡፡
እየሱስ እግዚኣብሄር (አምላክ) ነው፡፡ ‹‹ቃልም እግዚኣብሄር ነበር›› ዮሐ 11 ፡፡ ቶማስም ‹‹ ጌታዬ አምላኬ›› ብሎ ጠራው፡፡(Said to Him the God of me and the Lord of me>>) ፡፡ዮሐ 2028 እግዚኣብሄር ሥጋ አይደለም መንፈስ ነው፡፡ዮሐ 424፡፡ ስለዚህ እየሱስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነበር፡፡ በሰውነቱ ሥጋ ነው በአምላክነቱ መንፈስ ነው፡፡1 ጢሞ 220፡፡ እንዴት ነው ሰውም (ሥጋም) አምላክም ( መንፈስም) የሆነው፡፡ ሁለቱን በማዋሀድ (ሁለቱን ያዋሐደ ኤፌ 214) ፡፡ በሚታየው ሥጋው (ሰውነቱ) ውስጥ የማይታየው መንፈስ (አምላክነቱ) ነበር፡፡ ነገር ግን አይን የሚያየው ሥጋን ብቻ ነው፡፡ መንፈስ በተዋህዶ በሥጋው ቢኖርም፣መንፈስ በእምነት እንጂ በአይን አይታይምና አምላክ መሆኑን ያመኑት መጽሐፍ ቅዱስን እና የእሱን ቃል ያመኑት ብቻ ናቸው፡፡ አይሁዶችም ሰው ብቻ ነው እግዚኣብሄር አይደለም ብለው በአይን ያዩትን ብቻ ስላመኑ ሊገድሉት ፈለጉ ገደሉትም፡፡ ‹‹ ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤ ›› 1 ቆሮ 28፡፡
Selam Selam Nahom Seid ለምን ሥጋ ለበሰ ? ሞትን ማጥፋት፣አምላክ የማይሞት ሥላሆነ ለሞት ተገቢውን ዋጋ ለመክፈል፤ የማይሞተው አምላክ (እሱ በእግዚኣብሄር መልክ ሲኖር ሳለ) የሰውን ሥጋ ለብሶ በሰው መልክ ሆነ፡፡ ሰው የማያድን ሆኖ ሳለ፤እሱ በሞቱ እንደ ሰው ሞቶ እንደ አምላክነቱ አዳነን፡፡
ስለዚህ እየሱስ <<በስጋ (በሰውነቱ) ሞተ በመንፈስ (በአምላክነቱ) ግን ህያው ሆነ ››1 ጴጥ 318 <<በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤›› ቁጥር 19፡፡
እየሱስ በሞተበት በሦስቱ ቀናት ውስጥ በሥጋ ሞተ እንጂ በአምላክነቱ (በመንፈስ) አልሞተም፡፡ ለዚህ ነው እኔ ራሴ እራሴን አስነሳዋለሁ ያለው፡፡ዮሐ 219
Selam Selam Nahom Seid ‹‹እየሱስም:- አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዘዬ ገና አልደረሰም አላት።'' … ይህም ለናቱ ታዛዥ አለመሆኑን አያሳይም?›› ማለትህን ሰስታውስ፡፡ ይህ ብቻ ፣በመሃል የተቆረጠውን ሀሳብ ሳይጨምር፤ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ድርጅታችሁ ይህን ይላል፡፡
"ኢየሱስ ልጅ ሳለ ለእናቱና ለአሳዳጊ አባቱ --- ነበር። በዚህ ጊዜ ግን ሙሉ ሰው ስለ ነበር በማርያም ፈቃድ የማይመራ መሆኑን በደግነትና ጥብቅ በሆነ አነጋገር ገልጾላታል እርሷም እርማቱን በትሕትና ተቀብላለች።" መመራመር፣ገጽ 260፡፡ አስተውል ‹‹ ልጅ ሳለ ለእናቱና ለአሳዳጊ አባቱ --- ነበር›› ይላል፡፡ ከዚም ይህን በመቃወም ‹‹ በዚህ ጊዜ ግን (አፍራሽ ቃል መሆኑን አስተውል) ሙሉ ሰው ስለ ነበር በማርያም ፈቃድ የማይመራ ›› ይለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ድርጅታችሁ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ኢየሱስአንቺ ሴት፣ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?” ሲል የሰጠው መልስ ለቀረበው ማሳሰቢያ ወይም ሐሳብ --- ለመግለጽ የሚያገለግል በድሮ ዘመን የሚሠራበት የአጠያየቅ ዘይቤ ነው። ኢየሱስ ማርያም ያቀረበችውን ሐሳብ ----- ለምንድን ነው? አሁን 30 ዓመቱ ነው። >>በመጠበቂያ ግንብ፣2000፣ሴፕቴምበር፣15፣ገጽ 11፡፡ በእንግሊዝኛውም rejected ይላል፡፡ ይህ ማለት accepted የሚለው ተቃራኒ ነው፡፡ የተቃወመበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን እናቱን ተቃውሞኣል፤እንዲሁም አልታዘዛትም፡፡ እየሱስ እናቱንም ተቃወመ ካልን እሱ ራሱ የሚቃወመውን የሚፈጽም ነው ማለት ነው፡፡ ከዚህም በላይ የእናንተ አስተምሮ እርስ በራሱ ይቃረናል፡፡
Selam Selam Nahom Seid ‹‹ የናቱን ትዛዝ ---- --- ካንቺ ጋር ምን ጥል(ጸብ) አለኝ በማለት እሷን የሚያስቀይምበት ምን ጸብ አደለኤለው እየገለጸላት ነው›› ብለሃል ላልከው ተሳስተሃል(ሐሰት ነው)፡፡
እኔ ያልኩት ‹‹እናቱን ትዕዛዝ ----- --- ከአንቺ ጋር ምን ጥል (ጸብ) አለኝ በማለት እስዋን የሚያሰቀይምበት ምንም ጸብ እንዳሌለው እየገለጸላት ነው፡፡›› እኔ ያል...See More
Selam አሁንም እደግምልሃለሁ እኛ የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፍ ቅዱስን መሰረት አርገን ነው የምናምነው። ከቃልም አርፈን በተግባር የምንፈጽም ሰዎች ነን። እኛ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላትን አልጨመርንም። እነዚህ የተቀስካቸው ጥቅሶችም ማስረጃ ሊሆኑህ አይችሉም። አንድ ልታውቀው የሚገባ ጉዳይ አለ አዲስ አለም ትርጉም(New world Translation) መጽሓፍ ቅዱስ ሲተረጎም መሰረት ያደረገው የእብራይስጡን R,Kittel's Biblia Hebraica(HBK)ን፣ በግሪከኛው ደግሞ West cott and Hert ትርጉሞችን መሰረት አርጎ ነው። ኢትዮጲያ ውስጥ የምንተቀምበት መጽሃፍ ቅዱስ ደግሞ የተተረጎመው King James Version መሰረት አርጎ ነው። ስለዚህ አዲስ አለም ትርጉም R,Kittel's Biblia Hebraica እና West cott and Hert መተርጎሙ ነጥቡ ይበልጥ ግልጽ እንዲሆን አድርጓል።
Reply15 hrs
Selam ፊሊጲስዮስ 29 ሌላ የሚለውን ቃል ከየት አመጣችሁት ላልከው ጥያቄ አዲስ አለም ትርጉም እንዲህ ይላል " በዚህም ምክኒያት አምላክ የላቀ ቦታ በመስ ከፍ ከፍ አደረገው፤ እንዲሁም ከለላ ከማንኛውም ስም በላይ የሆነ ስም በደግነት ሰጠው። ይላል King James Version መሰረት አርጎ የተተረጎመው አዲስ አለም ትርጉም(1993 የታተመው) ላይ እና 1954 መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ጥቅሱ አንዲህ ይላል "ስለዚህ አግዚአብሀር እጂግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ሰጠው። ይላል እንግዲያው ልብ በል አዲስ አለም ትርጉሙ ላይ ከሌላ ከማንኛውም ስም በላይ የሚል ቃል አለ። በአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ ደግሞ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነ ስም የሚል ቃል አለ። ስለዚህ አስተዉል ከስምም ሁሉ እና ከሌላ ከምንኛውም ስም በላይ የሆነ ስም የሚሉት ቃላቶች ምንም የሚጋጭ ነገር የላቸውም። ሁለቱም ሃሳባቸው አንድ ነው። እንዲያውም ከሌላ ከማንኛውም ስም በላይየሚለው ቃል የበለጠ ሃሳቡንግልጽ ያደርገዋል። ምክንያቱም ከስምም ሁሉ በላይ ማለት ከሌላ ከማንኛውም ስም በላይ ማለት ነው።
Reply15 hrs
Selam 116,17,20 ሌሎች የሚሉትን ቃላት ከየት አመጣችሁት ላልከው ጥቅሱ አዲስ አለም ትርጉም "ምክንያቱም በሰማያትና በምድር ያሉ ሌሎች ነገሮችህ ሁሉ....................፣ሌሎች ነገሮች የተፈተሩት.......፣ቁጥር 17 ላይ. ...ከሌሎች ነገሮች ሁሉ...፣ሌሎች ነገሮች.......... ቁጥር 20. .............ሌሎቹን ነገሮች..........." ይላል በአዲ...See More
Reply14 hrs
Selam 1 ቆሮ 1527 ላይ ያለውን አምላክ የሚለውን ቃል ከየት አመጣችሁት ላልከው ደግሞ ጥቅሱ ነዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ "ሁሉን ነገር ከእግሩ ስር አስገዝቶለታል ተብሎለታልና" ይላል። ታዲያ ሁሉን ነገር ከእግሩ ስር ያስገዛለት ማን ነው? አምላክ አደሆነ ግልጽ ነው። ለዚህ ነው በአዲስ አለም ትርጉም ላይ አምላክ" ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዝቶለታልና የሚለው። ይህ ደግሞ ነጥቡን ይበልጥ ግልጽ አደረገው እንጂ የጥቅሱን ሃሳብ አለወተውም።
Reply14 hrs
Selam ዮሓ 219-21 እየሱስ "ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱ እነም በሶስት ቀን መልሼ አነሳዋለሁ" ብሎ መለሰላቸው። አይሁዳውያኑም " ይህን ቤተ መቅደስ ለመስራት 46 አመት ፈጅቷል፤ታድያ አንተ አዴት 3ቀን መልሰህ ታነሳዋለህ? አሉት በተ መቅደስ ሲል ግን ስለገዛ ሰውነቱ መናገሩ ነበር። እዚህ ላይ እየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እየነገራቸው ያለው እኮ 3ኛው ቀን እደሚነሳ ነው እንጅ ሲነሳ የለበሰውን ስጋ ይዞ እደሚነሳ እየነገራቸው አይደለም። ለተጨማሪ መረጃም ማቴ1621 ላይ ያለዉን ሃሳብ ማየት ትችላለህ። ጥቅሱ ላይ እየሱስ 3ኛው ቀን እደሚነሳ ነውእንጅ የነገራቸው የለበሰውን ስጋ ይዞ እደሚነሳ አልነገራቸውም። እና ደቀ መዛሙርቱ ያመኑት የለበሰውን ስጋ ይዞ አደተነሳ ሳይሆን 3ኛው ቀን እደሚነሳ የተነገርውን ቃል ነው ያመኑት። የተነገረውም ቃል ማቴ1621ነው። ለላው አሁንምእደግምልሃለው 1 ጴጥ318 "በስጋ ሞተ በመንፈስ ግን ህያው ሆነ" ስለሚል እየሱስ የተነሳው በመንፈስ ነው ብለን እናምናለን። ደግሞ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት በብዛት እየሱስ ማን አደሆነ እንጅ ምን እደሆነ በተገቢው መንገድ አያስተምርም ያልከው ከእውንውት በጣም የራቀ ነው። ምክንያቱም ስለ እየሱስ በሚናገሩ በማንግናውም ጽሁፎቻችን ላይ ብታይ ስለምንነቱ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች ተገልጸዋል። ለምሳለ ትክክለኛው የመጽሕፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው በሚለው መጽሓፋችን ምእራፍ 4 ላይ እየሱስ ማነው በሚለው ርእስ ውስጥ 3 ዋና ዋና ነጥቦች ተብራርተዋል። እየሱስ የተሰተው ልዩ ሚና ምን እደሆነ፣የመጣው ከየት እደሆነ እና ምን አይነት ሰው እደነበረ ያብራራል። አንድ ያልገባህ ነገር አለ በማንነት ዉስጥ ምንነት እዳለ ማወክ አለብህ። ሌላው 1 ጴጥ 318 ከጠከስክ በሗላ በስጋ(በሰውነቱ) በመንፈስ(በአምላክነቱ) ግን ህያው ሆነ ብለህ ተርጉመሀዋል በስጋ (በሰውነቱ) ያልከው ልክ ነህ። ምክንያቱም በሰዉነቱ ሞቷል። በመንፈስ(አምላክነቱ) ያልከው ግን ከእውነት የራቀ ነው። በጣም ጠሳስተሃል። መጀመርያ መንፈስ ምን ማለት ነው? መንፈስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ህያዋን ፍጡራንን ሁሉ የሚያንቀሳቀሰውን በአይን የማይታየውን ሓይል ያመለክታል። ከዚህም በተጨማሪ መንፈስ መላእክትንም ይጨምራል ይሖዋም መንፈስ ነው። እዲያውም ኦርቶዶክሶች ነፍስንና መፈስን አንድ አይነት ትርጉም አዳላቸው አና ልዩነት እደሌላቸው ነው የምታምኑት። በናንተ አባባል ነፍስና መንፈስ ምንም ልዩነት ከሌላቸው ለምንድን ነው ኢሳ 5312 አተለይ 1954 ትርጉም ላይ "ስለዚህ እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፣ከሓያላንም ጋር ምርኮን ይካፈላል፣ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰቷልና፣ከአመጸኞችም ጋር ተቆጥሯል፣እሱ ግን የብዙ ሰውዎችን ሓጢያት ተሸከመ፣ ስለ አመጸኞችም ማለደ" ይላል። ስለዚህ እናንተ ደግሞ ነፍስና መንፈስ ልዩነት እደሌላቸው ታምናላችሁ ጥቅሱ ላይ ግን " ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰቷልና" ይላል። ስለዚህ ባንተ አስተሳሰብ መንፈስ የሚለውን ኣምላክነቱ ብለሃል። ታዲያ ነፍስና መንፈስን ምንም የሚያለያያቸው ነገር ከሌለ ባንተ አተረጓጎም እየሱስ ባምላክነቱ ሞቷል ማለት ነው። መንፈስ(አምላክነቱ)ብለህ መተርጎምህ ገርሞኛል። ሌላው እየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ስጋዊ መልክ ይዞ መታየቱ እውነት ነው።ምክንያቱም ዘፍ 191-3ላይ 2መለአክት ለሎጥ እደተገለጡለትና ምግብም ጭምር እደሰጣቸውና እንደበሉ ይገልጻል። ደቀመዛሙርቱ በተለያዩ ጊዜያት ወዲያው እዳዩት እየሱስ መሆኑን ሊያውቁ ያልቻሉት ለምንድን ነው? (ሉቃስ 24 15-32፣ዮሓ 2014-16) ከስምንት ቀን በኋላስ እደገና ለደቀመዛሙርቱ በተገለጠበት ጊዜ በሮቹ ተቆልፈው ሳሉ በድንገት በመካከላቸው አዴት ሊገኝ ቻለ? (ዮሓ 2026,27) ስለዚህ እየሱስ ስጋዊ አካል ሳይሆን መንፈሳዊ አካል ይዞ ነው የተነሳው።
Reply11 hrs
Selam Selam Nahom Seid ‹‹አሁንም እደግምልሃለሁ እኛ የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፍ ቅዱስን መሰረት አርገን ነው የምናምነው። ከቃልም አርፈን በተግባር የምንፈጽም ሰዎች ነን።›› ላልከው መደጋግም ነገርን እውነት አያደርገውም፡፡ እኔ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት እንደማታምኑ በማስረጃ ነው ያስቀመጥኩት፡፡ አንባቢው ማስረጃውን ተመልክቶ እውነቱን ይረዳል፡፡ ‹‹በግሪከኛው ደግሞ West cott and Hert ትርጉሞችን መሰረት አርጎ ነው።›› ላልከው እኔም ያቀረብኩት የግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ይሄው ነው፡፡ የእናንተ ድርጅት ለዚህ West cott and Hert የግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ የቃል በቃል ትርጉም ከእያንዳንዱ ቃላት ሥር በመስጠት kingdom interlinear translation (KIT) በማለት የራሱ አርጎታል፡፡ ከላይ የሰጠሁህ ማስረጃ የግሪኩ ቃላት West cott and Hert ሲሆኑ ከሥር ያሉት የእንግሊዝኛ ትርጉሞች የራሳችሁ ድርጅት ነው፡፡ ትርጉማችሁ ስህተት መሆኑን የሚነግረንም የገዛ መጽሐፋችሁ ነው፡፡ እንዲያውም ድርጅታችሁ በአዲስ ኪዳን አንድም ቦታ የማይገኘውን ይሖዋ የሚለውን ቃል 200 ጊዜ በላይ በገዛ ፍቃዱ በመጨመር በመጽሐፍ ቅዱስ አለማመኑን አስመስክሮኣል፡፡ማመን ያለማመን የግለሰብ ነው፡፡
Reply49 mins
Selam Selam Nahom Seid በፊሊጲስዮስ 29 ሌላ የሚለውን እና ‹‹ [ቆላስይስ] 116,17,20 ሌሎች የሚሉትን ቃላት በገዛ ፍቃዳችሁ የጨመራችሁ መሆኑን King James Version እና 1954 መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥም እነዚህ ጥማሪ ቃላት አለመኖራቸውን ተጨማሪ ማስረጃ ሰጥተሀናል፡፡ ነገር ግን ቃላቱ ቢጨመሩም ባይጨመሩም ምንም የትርጉም ለውጥ የላቸውም ብለሃል፡፡ ይህ ሐሰት ነው፡፡ እንደሚከተለው እመልሳሉ፡፡
Reply40 mins
Selam Selam Nahom Seid በፊሊጲስዮስ 29 ‹‹ከስምም ሁሉ [በላይ] እና ከሌላ ከምንኛውም ስም በላይ….ሁለቱም ሃሳባቸው አንድ ነው ›› ላልከው ሐሰት ነው፡፡ ከሥምም ሁሉ በላይ የሆነ የአምላክ ሥም ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይሄንን ሥም ነው የእየሱስ የሚለው፡፡ እናንተ ግን እየሱስ አምላክ አይደለም ብላችሁ ስለምታምኑ ከሌላ የሚለውን ቃል ጨማራችሁ፡፡ ይህ ነው እውነቱ፡፡ ‹‹እንዲያውም ከሌላ ከማንኛውም ስም በላይየሚለው ቃል የበለጠ ሃሳቡንግልጽ ያደርገዋል።›› ላልከው፤ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስን ሐሰብ ሳይሆን ግልጽ የሚያደርገው የእናንተን እምነት ነው፡፡ ለእኛ በመጽሐፍ ቅዱስ ለምናምን ምንም ሳንጨምር ሐሳቡ ግልጽ ነው፡፡
Reply39 mins
Selam Selam Nahom Seid ቆላስይስ 116, 17, 20 :- ‹‹እንግዲያው ሌሎች ነገሮች እና ሁሉ ነገር የሚሉት ቃላት አይጋጩም።›› ላልከው ሁለቱ የትርጉም ልዩነት ኣላቸው፡፡ ድርጅታችሁን ሌሎች የሚለውን እንዲጨምር ያደረገው ምንድን ነው?
ቆላስይስ 116, 17, 20 እየሱስን ‹‹በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልናሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። …. ከሁሉ በፊት ነው›› ይለዋል፡፡ መጽሐፍ ቅስ እየሱስን ‹‹በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል›› ሲል እሱ ፍጡር ኣለመሆኑን እየነገረን ነው፡፡ ምክንያቱም እየሱስ ሁሉን ፍጥረታት ከፈጠረ ፍጥረታት በእሱ የተፈጠሩት ናቸው ማለት ነው፡፡ ሁሉም ፍጥረታት በእሱ ነው የተፈጠሩት፡፡ እሱ ፈጣሪ ነው እንጂ ፍጡር አይደለም፡፡
እንደ የይሖዋ ምስክሮች እምነት ግን እየሱስ የመጀመሪያው ፍጡር ነው ካልን፤ ቆላስይስ 116 (በግሪኩ እና ሌሎች ትርጉሞች) ግን እየሱስ ሁሉንም ፍጥረታት ፈጥሮኣል ይላል፡፡ ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮችን እምነት ከትክክለኛው የቆላስይስ 116 ሐሰብ ጋር ስናወዳድረው እየሱስ ሁሉን ፍጥረታት እንደመፍጠሩ ራሱንም ፈጥሮኣል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን አይችልም ራሱ ሳይኖር ራሱን አይፈጥርም፡፡ ስለዚህ እምነታቸው ከቆላስይስ 116 17, 20 ጋር ስለሚጋጭ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከመምጣት ይልቅ እንደ ፍላጎታቸው ሌሎች የሚለውን ጨመሩ፡፡ ይህ ነው ሐቁ፡፡
Reply38 mins
Selam Selam Nahom Seid ከፍጥረት ሁሉ በኩር ነው - <<ቁጥር 15ላይ "አሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው ከፍጥረት ሁሉ በኩር ነው።" ይላል ስለዚህ ኢየሱስ የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ነው።>> ላልከው ይህ ድርጅታችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ አያምንም ለሚለው ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግሪኩ ከፍጥረታት አይልም የፍጥረታት ነው የሚለው፡፡ ድርጅታችሁ እየሱስ የፍጥረታት በኩር ነው ምክንያቱም እሱ መጀመሪ ተፈጠረ ይለወል፡፡ የራሳችሁን መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተህ ተመልከት፡፡በቆላስይስ 115 ላይ የፍጥረት ሁሉ በኩር ካለው በኋላ በቁጥር 16 ምክንያቱም ብሎ ምን ይላል?
የበኩርና ትርጉም እን አየሱስ ለምን በኩር እንደተባለ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሰጠሁትን የቀድሞ መልስ ከዚህ ተመልከት፡፡
https://www.facebook.com/permalink.php...
https://www.facebook.com/permalink.php...
Reply37 mins
Selam Selam Nahom Seid 1 ቆሮ 1527 :- የይሖ ምስክሮች ትርጉም አምላክ የሚለውን ቃል በገዛ ፍቃዱ መጨመሩ ‹‹ነጥቡን ይበልጥ ግልጽ አደረገው እንጂ የጥቅሱን ሃሳብ አለወተውም። ›› ያልከው ፍጹም ሐሰት ነው፡፡ ድርጅታችሁ ሆን ብሎ ሐሳቡን እንደሚቀይረው ተረድቶ ነው ያረገው፡፡
በቁጥር 27 በግሪኩ ያለው ቃል አምላክ ሰይሆን የወንድ ተውላጠ ስም እሱ (he) ነው፡፡ ምናልባት ይህ የወንድ ተውላጠ ስም ለአምላክ ነው ብለህ በእርግጠኝነት ታምን ይሆናል፡፡ በመሆኑም አምላክ በሚለው መተካቱ ትክክል ነው ልትል ትችላለህ፡፡ የግሪክን ቋንቋ በትንሹ ብታየው ግን ለዚህ ዋስትና የለህም፡፡ በግሪክ ቋንቋ ስዋስዋዊ ጾታ ነገሩ ጾጻ ጋር ዝምድና የለውም፡፡ ለምሳሌ በግሪክ ቋንቋ ሞት ጾታው ተባዕት (Masculine) ነው፡፡ ስለዚ ተውላጠ ስሙም ተባዕት (Masculine) ነው፡፡ Strong's Concordance http://biblehub.com/greek/2288.htm
‹‹ [እሱ]ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና/ ምክንያቱም [እሱ]ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአል/ For (because) he hath put all things under his feet. ›› የዚህ አይነት አረፍተነገር subordinate clause ይባላል፡፡ የዚህ አይነት አረፍተነገር በራሱ አይቆምም፤የአንድ አረፍተነገር ግማሽ ነው፡፡ https://www.thoughtco.com/subordinat@e-clause-grammar...
ይህ በቁጥር 27 ያለው አረፍተነገር የአንድ አረፍተነገር የምክንያት ክፍል ነው፡፡ ምክንያቱም / For /because የሚሉት ቃላት የአረፍተነገሩን የምክንያት ክፍል ከውጤቱ ጋር ያያይዛሉ፡፡ ታዲያ በቁጥር 27 ምክንያቱን ካወቅን ውጤቱ (የአረፍተነገሩ ግማሽ) የት ነው ያለው፡፡ As, because and since all introduce subordinate clauses. They connect the result of something with its reason.
እስቲ ከቁጥር 26 እንጀምር፡፡
26 የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤27 [ምክንያቱም] ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና።The last enemy that shall be destroyed is death. For (because) he hath put all things under his feet. ››
ስለዚህ ውጤቱ የሞት መሻር የዚህ ምክንያቱ ሁሉን ከእግሩ በታች መግዛቱ ነው፡፡ ስለዚህ ገዚ የተባለው ሞት ነው፡፡ ሞት ሁሉን መግዛቱን በቁጥር 22 ‹‹ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ›› በማለት ይናገራል፡፡
ስለዚህ 1 ቆሮ 1526-28 ገዚ ሞት ሲሆን ተገዚ ደግሞ እኛ እና እየሱስ (ልጁ) ነው፡፡ የእኛን ለብዙ ዘመናት ለሞት መገዛት (መሞት) ልጁ ለሞት በመገዛት( በመሞት) እኛን ከሞት ማባቡን ይናገራል፡፡ ለዚህም ተጨማሪ ማረጋገጫ በቁጥር 29 ‹‹እንዲያማ ካልሆነ›› በማለት የገዚ ተገዢው ታሪክ ሰው ከሞት የዳነበት መሆኑን ይገልጻል፡፡
ድርጅታችሁ ግን የሌለውን አምላክ የሚለውን ቃል በመጨመር በቁር 29 ካለው ሐሳብ ጋር የሚጋጭ አድርጎታል፡፡ የእናንተን እምነት (አብ ገዚ ወልድ ተገዚ) የሚለውን ከወሰድን እና ከቁጥረ 29 ጋር ‹‹እንዲያማ ካልሆነ›› በሚለው ስናያይዘው ሰው ከሞት የዳነው እየሱስ ለአብ በገዛቱ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ቤዛውን ከንቱ ያረጋ፡፡ ይህ ቢሆን ኖሮ እየሱስ ሳይሞት በመገዛት ብቻ ሞትን ባጠፋ ነበር፡፡ ስለዚህ ድርጅታችሁ የጨመረው ቃል መጽሐፍ ቅዲስን ከማፋለሱም በላይ ትርጉሙን ይቀይራል፡፡
Reply27 mins
Selam Selam Nahom Seid ‹‹ዮሓ 219-21 እየሱስ "…ግን ስለገዛ ሰውነቱ መናገሩ ነበር። …. ሲነሳ የለበሰውን ስጋ ይዞ እደሚነሳ እየነገራቸው አይደለም።እና ደቀ መዛሙርቱ ያመኑት የለበሰውን ስጋ ይዞ አደተነሳ ሳይሆን 3ኛው ቀን እደሚነሳ የተነገርውን ቃል ነው ያመኑት›› ላልከው መልሱ ግልጽ ነው፡፡ አስቀድሜም መልሼነበር፡፡ ሰውነቱ የሚለውን ቃል አጽንኦት ሰጥቼው ነበር፡፡ ስለገዛ ሰውነቱ ማለት የለበሰው ስጋ ማለት ነው፡፡ ሰውነት ማት የሰው ከካል ማለት ነው፡፡ የራሱን ሰውነት አካል (ሥጋ) ማለት ነው፡፡ እየሱስ ከተነሳብ በኋላ ከሞቱ በፊት እንደነበረው የሰው ልጅ ተብሎኣል፣ሚመጣም በዚኅ መልኩ ና፡፡ የሰው ልጅ ማለት ሰው ማለት ነው፡፡ ይህም ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡ ደቀመዛሙርቱም ያመኑት በሥጋ መነሳቱን ነው፡፡
‹‹ኢየሱስም። እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።›› ማር 1462 ፤ማቴ 2531
የተነሳው መልኣክ (መንፈስ) ሆኖ ቢሆን መጽሐፍ አይዋሽምና የሰው ልጅ ይልም ነበር፡፡ እንግዲያው እናንተ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አታምኑም ማለት ነው፡፡
Reply10 mins
Selam Selam Nahom Seid እየሱስ ከሞተ በኋላ የታየው ልክ በዘፍ 191-3 ላይ ሁለቱ መላዕክት እንደታዩት ነው ላልከው የተሳሳተ ማመሳሰል ነው፡፡ እየሱስ በሥጋ (የሰውን ሥጋ) ለብሶ ኖሮኣል፣የሰው ልጅም ተብሎኣል፤የተወለደውም ከሰው ከማሪያም ነው፡፡ እናም ሰው ነበረ፡፡ ሁለተኘ ከመሞቱ በፊት በሥጋ እንደሚነሳ ተባግሮኣል፡፡ ሦስተኛ ከተነሳ በኋላ መንፈስ ለመሰላቸው እና ለተጠራጠሩት መንፈስ ኣለመሆኑን በማስረጃ ገልጾኣል መስክሮኣል፡፡ ከዚያም በኋላ የሰው ልጅ ይመጣል ተብሎ መነገሩ በሥጋ መነሳቱን ያሳያል፡፡
Reply10 mins
Selam Selam Nahom Seid ‹‹አንድ ያልገባህ ነገር አለ በማንነት ዉስጥ ምንነት እዳለ ማወክ አለብህ።›› ላልከው ይህ ግልጽ ነው፡፡ የእየሱስ ምንነት ማለት ባህሪው ማለት ነው፡፡ ስለ ባህሪ እና አካል ከዚህ ብታነብ እና አዚያው አስተያየት ብትሰጠኝ፡፡ http://besilasieamagn.blogspot.com/2015/09/11john-11_53.html http://besilasieamagn.blogspot.com/2015/09/blog-post_61.html
Reply10 mins
Selam Selam Nahom Seid ‹‹ደቀመዛሙርቱ በተለያዩ ጊዜያት ወዲያው እዳዩት እየሱስ መሆኑን ሊያውቁ ያልቻሉት ለምንድን ነው?....በሮቹ ተቆልፈው ሳሉ በድንገት በመካከላቸው አዴት ሊገኝ ቻለ?..ስለዚህ እየሱስ ስጋዊ አካል ሳይሆን መንፈሳዊ አካል ይዞ ነው የተነሳው›› ብለሃል፡፡

እየሱስ ከመሞቱ በፊት ያለውን ይሄን ታሪክ እንመልከት፡፡

‹‹ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነሱ መጣ። ደቀ መዛሙርቱ በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ደንግጠውምትሃት ነው!” አሉ። በፍርሃት ተውጠውም ጮኹ። ሆኖም ኢየሱስ ወዲያውኑአይዟችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩአላቸው። ጴጥሮስም መልሶጌታ ሆይ፣ አንተ ከሆንክ በውኃው ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝአለው። እሱም!” አለው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ከጀልባው ላይ ወርዶ በውኃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ። ሆኖም አውሎ ነፋሱን ሲያይ ፈራ። መስጠም ሲጀምርምጌታ ሆይ፣ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። ወዲያው ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውናአንተ እምነት የጎደለህ! ለምን ተጠራጠርክ?” አለው።+ ጀልባው ላይ ከወጡ በኋላ አውሎ ነፋሱ ጸጥ አለ። ከዚያም በጀልባው ውስጥ ያሉትአንተ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነህብለው ሰገዱለት።>> ማቴ 1425-33

ምትሃት ብለው በአማርኛ የተተረጎመውን ቃል ብዙዎቹ የእንግሊዝኛ ተርጓሚዎች Gost ብለው ሲተረጉሙ NWT ደግሞ apparition ብሎታል፡፡ ዞሮ ዞሮ ትርጉሞ አንድ ነው፡፡ https://www.collinsdictionary.com/dict.../english/apparition
ስለዚህ እየሱስ በውኃ ላይ እየተራመደ ሲመጣ መንፈስ ነው የመሰላቸው፡፡ ቶሎ ሉለዩትም አልቻሉም፡፡ እሱነቱን የተጠራጠረው ጴጥሮስ እንዲውምጌታ ሆይ፣ አንተ ከሆንክ›› በማለት እሱነቱን ለማረጋገጥ ጠየቀው፡፡በኋላም አመነ፡፡ እየሱስ ሰው የማይችለውነ ነገር አደረገ፡፡ ተኣምር፡፡ ስለዚህ እየሱስ በውኃ ላይ ሲራመድ መንፈስ ነው ብለው ደቀመዛሙርቱ ሊያውቁት ስላልቻሉ እየሱስ መንፈስ ነበር? ሰው ማድረግ ያልቻለውን ስላደረገ እሱ መንፈስ ነበር ማለት ነው? በሉቃ 2437-41 ላይም እየሱስ እየሱስ ተመሳሳይ ነገር ነው ያረገው፡፡

በሁለቱም ቦታ መንፈስ መሰላቸው፤ደነገጡ፤እየሱስም አትፍሩ ኣላቸው፤እኔው ራሴ ነኝ በማለት በማስረጃ የሰቡት ነገር ስህተት እንደሆነ ነገራቸው፡፡እነሱም አመኑ፡፡

37 ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። 38 እርሱም። ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል? 39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው። 40 ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። 41 እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ። በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው። ሉቃ 2437-41
በሮቹ ተቆልፈው ሳሉ በድንገት በመካከላቸው መገኘቱም ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም፡፡ እሱ ብዙ በሰው የማይቻሉ ተኣምራት አድርጎኣል፡፡ በውሃ ላይ መሄዱ ከብዙዎቹ አንዱ ነው፡፡ እሱ ከሰው ልማድ ውጪ ያለ አባት የተወለደ ነው፡፡
ስለዚህ እየሱስ እንደተናገረው በሥጋ ነው የተነሳው፡፡ የተነሳውም በራሱ ነው፡፡ እኔ ሥጋ አለኝ መንፈስ ግን የለውም የለውም እውነት ነው፡፡
እሱ የሰው ልጅ ሰው የእግዚኣብሄር ልጅ እግዚኣብሄር ነው፡፡ ሰው ሥጋ ነው እግዚኣብሄር መንፈስ ነው፡፡ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን አልሞተም፡፡
Reply10 mins
Selam Selam Nahom Seid ‹‹እዲያውም ኦርቶዶክሶች ነፍስንና መፈስን አንድ አይነት ትርጉም አዳላቸው አና ልዩነት እደሌላቸው ነው የምታምኑት።›› ያልከው ሐሰት ነው፡፡ ማስረጃ ብታስቀምጥ ጥሩ ነው፡፡ ‹‹1 ጴጥ 318 ከጠከስክ በሗላ በስጋ (በሰውነቱ) በመንፈስ (በአምላክነቱ) ግን ህያው ሆነ ብለህ ተርጉመሀዋል›› ስላልከኝ ነገር እኔ ትርጉም አይደለም የሰጠሁት ማብራሪያ ነው፡፡ ‹‹በስጋ (በሰውነቱ) ያልከው ልክ ነህ። ምክንያቱም በሰዉነቱ ሞቷል። በመንፈስ (አምላክነቱ) ያልከው ግን ከእውነት የራቀ ነው። ›› ላልከው ማመን የግለሰብ ነው፡፡ ቃልም አምላክ ነበር። ዮሐ 11 አምላክ መንፈስ ነው፤ ዮሐ 424 (አአት) ማብራሪያውን ተመልሰህ አንብበው፡፡ እየሱስ በሥጋው ሞቶ ሳለ ህያው ስለሆነ ነው ራሱን ያስነሳው፡፡ https://www.facebook.com/permalink.php...
Reply8 mins


No comments:

Post a Comment