እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ (ምሳሌ 8፡22)
የይሖዋ ምስክሮች ምሳሌ 8፡22 ላይ ስለ ጥብብ ያለዉን የይብራይስጥ መጽሓፍ ቅዱስ ቃል “ይሖዋ የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ “ ብሎ ተርጉመዋል፡፡ እንዲሁም እየሱስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡24 ላይ “እያሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ” መባሉን ምክንያት በማድረግ ፤ምሳ 8፡22 እየሱስ መጀመሪያ ስለመፈጠሩ ያወራል ይላሉ፡፡እዚህ ላይ ሁሉም ክርስቲያን ማስተዋል የለበት እየሱስ በእግዚኣብሄር ጥበብ ተመሰለ እንጂ ምሳ8፡22 የሚያወራዉ ስለ አምላክ ጥብብ ነዉ፡፡በምሳ 7፡3 ላይ ጥበብ እህት ተብላለች፡፡እየሱስ ግን ተባዕታዊ ፆታ ነዉ፡፡
ይህ የይሖዋ ምስክሮች አድርጎ ፋጠረገኝ ብለዉ በሁለት ቃላት የተረጎሙት የይብራይስጥ ቃል ኣንድ ቃል ነዉ ይህም “ቀናኒ” የሚባል የይብራይስጥ ቃል ነዉ፡፡ይህ የመጀመሪያዉ የይሆዋ ምስከሮች ትርጉም ስህተት ነዉ፡፡
የፍጥረታት ሁሉበኩር (ቆላ 1፡15-17)
በቆላ 1፡15 ላይ እየሱስን የፍጥረታት ሁሉ በኩር ይለዋል፡፡ይህ ቆላ 1፡15 የይሆዋ ምስክሮች እንደሚሉት እየሱን የመጀመሪየዉ ፍጥረት ማለቱ ነዉን? በኩር ማለትስ ምን ማለት ነዉ?ይህ በኩር ተብሎ የተተረጎመዉ የግሪክ ቃል ፕሮቶኮስ( prototokos) የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛዉ ፈርስት ቦርን (Firstborn) ነዉ፡፡መጀመሪያ የተፈጠረ (First created) ለማለት የግሪኩ ቃል ፕሮቶክቲሲሰ (protoktisis) ነዉ፡፡ታዲያ ይህ ቆላ 1፡15 እየሱስን መጀመሪያ የተፈጠረ ለማለት ከፈለገ ለምን ፕሮቶክቲሲሰ/ First created አላለም?
የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ (ራዕ 3፡14)
ይህም የመጽሓፍ ቀዱስ ክፍል የይሖዋ ምስክሮች
ክርስቶስ የመጀመሪያው የአምላክ ፍጡር ነው ለሚለው አስተምሮኣቸው የኒጠቀሙት ጥቅስ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment