በዘጸኣት 3፡13 ላይ ሙሴ አምላክን ባነጋገረበት ጊዜ ስምህን ቢጠይቁኝ ማን ልበል ሲል አምላክም
אֶֽהְיֶ֑ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֖ה (’eh·yeh ’ă·šer ’eh·yeh) ካለው በኋላ
אֶֽהְיֶ֖ה (’eh·yeh ) ልኮኛል በል ብሎታል፡፡ የህን የይብራይስጥ ቃል ኪንግ ጀምስ የእንግሊዝኛ
ትርጉም የመጀመሪውን I AM THAT I AM ሲለው የሁለተኛውን ደግሞ
I AM በማለት ተርጉሞታል፡፡
<<And
God said unto Moses, I AM THAT I AM:
and he said, Thus shalt thou say unto the children of Israel, I AM hath sent me unto you.>>
KJV
በብዛት በኢንተርኔት ላይ የሚገኘው
የ1962ቱ የአማርኛ ትርጉም ደግሞ
እግዚአብሔርም ሙሴን። <<ያለና የሚኖር>> እኔ ነኝ አለው፤
እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። <<ያለና የሚኖር>>ወደ
እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው። 15፤ እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው።
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ። የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር
(ያህዌ) ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።
የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፍ ቅዱስ
ትርጉም ደግሞ እንዲህ ተርጉሞታል፡፡
‘ስሙ ማን ነው?’+ ብለው
ቢጠይቁኝ ምን ልበላቸው?” አለው። 14 በዚህ
ጊዜ አምላክ ሙሴን “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ”*+አለው።
በመቀጠልም “እስራኤላውያንን ‘“እሆናለሁ” ወደ
እናንተ ልኮኛል’+ በላቸው”
አለው። 15 ከዚያም
አምላክ ሙሴን በድጋሚ እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣+ የይስሐቅ
አምላክና+ የያዕቆብ
አምላክ+ የሆነው
ይሖዋ ወደ እናንተ ልኮኛል።’ ይህ ለዘላለም ስሜ ነው፤+ከትውልድ
እስከ ትውልድ የምታወሰውም በዚህ ነው።
የይሆዋ ምስክሮች ትርጉም አምላክ
የመሆን ባህሪ (የመለወጥ ባህሪ) እንዳለው ያሳያል፡፡ እሆናለሁ
ማለት አምላክ ያልሆነውን ነገር እንደሚሆን ያመለክታል፡፡ ይህንንም ትርጉማቸውን ትክክለኛ የመጽሓፍ ቅዱ ትምህርት በሚለው መጽሓፋቸው
ገጽ 197 ላይ ሰዎች ዶክተር ከመሆን እና ባለጸጋ መሆንን እንደ ምሳሌ በሰውኛ ይሰጣሉ፡፡ ይህ የይሖዋ ምስክሮች ትርጉም እኔ እግዚአብሄር
አልለወጥም (ት.ሚልክያስ 3፡6) የሚለውን የመጽሓፍ ቅዱስ ቃል ይቃወማል፡፡
እንደ ኪንግ ጀምስ እና እንደ
የ1962ቱ ትሩጉሞች፣በግርድፉ አምላክ ያው ድሮ እኔ ያልኩት እኔ ነኝ የሚል ሲሆን ይህም የማይለወጥ ዘላለማዊ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም
ከሌላው የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል ጋር (ት.ሚልክያስ 3፡6) አይቃረንም፡፡
No comments:
Post a Comment