Pages

Friday, August 28, 2015

1925 (የእነአብርሃም ትንሳኤ)

የይሖዋ ምስክሮች አብርሃም፣ይስሃቅ፣ያቆብ እና ሌሎችም የብሉይ ኪዳን ሳዎች  በ1925 ስጋዊ ትንሳኤ እንደሚኖራቸዉ ተንብየዉ ነበር፡፡
የሚከተሉትን ማስረጃዎች ይማልከቱ
” Abraham should enter upon the actual possession of his promised inheritance in the year 1925 .A. D.”  Watch Tower October 15, 1917, page 6157

“አብረሃም ቃል ወደተገባለት ርስቱ በ1925 መግባት ኣለበት” መጠበቂያ ግንብ ኦክቶበር 15፣1917፣ገፅ 6157
 “Some are inclined to become doubtful about 1925; hence they are growing lukewarm. … God will not change his plans. …He has made no mistakes. He will carry them out,” Watch Tower February 1, 1923, page 35

“ኣንዳንዶች ስለ 1925 ይጠራጠራሉ፤እናም ለብ እያሉ ነዉ፡፡…..እግዚኣብሄር እቅዱን አይቀይርም፡፡…ስህተትም አልሰራም፡፡ይፈፅማቸዋልም፡፡”መጠበቂያ ግንብ ፌብሯሪይ 1፣1923፣ገፅ 35

 “Our thought is, that 1925 is definitely settled by the Scriptures,” Watch Tower April 1, 1923, page 106, question and answer

“ሀሳባችን፣1925 በትክክል በመፅሃፍ ቅዱስ የተወሰነ ነዉ፡፡”መጠበቂያ ግንብ ኤፕሪል 1፣1923፣ገፅ 106
“Verily 1925 will show in fact the fulfillment of prophecy, in which year blessings will begin from Abraham.” Watch Tower December 15, 1923, page 376, Rusia

“በእዉነት 1925 የትንቢቱን ፍፃሜ ያሳያል፣በዚህም አመት አብርሃም ቡራኬ ይጀምራል፡፡”መጠበቂያ ግንብ ዲሴምበር 15፣1923፣ገፅ 376
” The year 1925 is a date definitely and clearly marked in the Scriptures, even more clearly than that of 1914;” Watch Tower July 15, 1924, page 211

“1925 በእርግጠኝነትና በግልፅ በመፅሃፍ ቅዱስ የተገለጸ ነዉ፤ከ1914 የበለጠ ግልጽ ነዉ፡፡” መጠበቂያ ግንብ ጁላይ 15፣1924፣ገፅ 211
” Other Scriptures definitely fix the fact that there will be a resurrection of Abraham, Isaac, Jacob and other faithful ones of old, and that these will have the first favor, we may expect
1925 to witness the return of these faithful men of Israel from the condition of death, being
resurrected and fully restored to perfect humanity and made the visible, legal representatives
of the new order of things on earth.” Millions Now Living Will Never Die፣ 1920፣page 88

“ሌሎች መጻህፍት በአርግጠኝነት በ1925 አብርሃም፣ይስሃቅ፣ያቆብ እና ሌሎችም ታማኞች ከሞት በሥጋ ሙሉ በሙሉ ይነሳሉ፣ህጋዊ  የምድር ኣዲሱ ደንብ ተወካይ ይሆናሉ፡፡” Millions Now Living Will Never Die፣ 1920፣page 88
ከላይ እንደምንመለከተዉ የይሖዋ ምስክሮች የእነአብርሃም የ1925 ስጋዊ ትንሳኤ እርግጥ እና በመፅሃፍ ቅዱሳዊ እንዲሁም የእግዚኣብሄር እቅዱ እና እንደሚፈጽመዉ በእርግጠኝነት ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን እርግጠኛ በሆኑበት 1925 እነአብርሃም ሳይነሱ ቀሩ፡፡

ገና 1925 ሳያልቅ እርግጠኛ በሆኑበትን ትንቢታቸዉን እንደሚከተለዉ የመቀየር አዝማሚያ አሳይተዋል (በቅርብ በማለት)፡፡
"it is apparent that there are many peoples now on earth who may confidently hope to see Abraham, Isaac, Jacob and the other prophets back on earth within a few years" The Golden Age, 12 August 1925, page 731
--------
“በግልጽ አሁንም የአብርሃም፣የይስሃቅ፣ያቆብ እና ሌሎች ነብያትን በጥቂት አመታት ዉስጥ ወደ መሬት መመለስ ብዙ ሰዎች በእርግጠኝነት ተስፋ እያረጉ ነዉ፡፡” The Golden Age, 12 August 1925, page 731
የይሖዋ ምስክሮች ፐሬዝዳንት የነበረዉ ራዘርፎርድ ከአመት በኋላ በ1926 በሲዉዘርላንድ ባደረገዉ ስብሰባ ፣እነአብርሃም መጥተዋል ወይ; ተብሎ ለተጠየቅ ጥያቄ እንዲህ ብሎ መልሶዋል
 "it would be foolish to make such an announcement." BETH-SARIM: A Monument to a False Prophet and to False Prophecy ፣by Edmond C. Gruss and Leonard Chretien፣ page 3
መጥተዋል ብሎ መናገር ሞገኝነት ነዉ፡፡ብሎ ኣለመነሳታቸዉን ከተናገረ በኋላ
“we might reasonably expect them to return shortly after 1925,” BETH-SARIM: A Monument to a False Prophet and to False Prophecy ፣by Edmond C. Gruss and Leonard Chretien፣ page 3
ከ1925 በኋላ በቅርብ ትንሳኤያቸዉን እንጠብቃለን፡፡በማለት ጊዜዉ ከ1925 በኋላ በቅርቡ እንደሆነ ተናግሮዋል፡፡
ከላይ የጠቀስኩዋቸዉ  Edmond C. Gruss and Leonard Chretien የሚከተሉትን የይሖዋ ምስክሮች መጽሃፍት ለማስረጃነት ተጠቅመዋል
"New Heavens and New Earth — What Are They?" The Golden Age, 12 August 1925, page 731

"European Conventions," The Watch Tower, 1 July 1926, page 196

ከ1925 በኋላ በቅርቡ ይነሳሉ ኣሉ፡፡
ለእነ አብርሃም በ1929/30 መኖርያ ቤት አሰሩላቸዉ፡፡

ከዚህ በኋላ የይሖዋ ምስክሮች ፐሬዝዳንት የነበረዉ ራዘርፎርድ በቅርቡ ይነሳሉ ላላቸዉ ለእነ አብርሃም በ1929 መኖርያ ቤት አሰራላቸዉ፡፡የቤቱም ስም ቤተ ሳሬም ይባላል፡፡ይህንንም ሀቅ ሳልቬሽን በሚባለዉ መጽሓፋቸዉ ላይ እንዲህ ገልጻዋል፡፡
“At San Diego, California, there is a small piece of land, on which, in the year 1929, there was built a house, which is called and known as Beth-Sarim.” Salvation, Watchtower Bible and Tract Society, by J. F. RUTHERFORD, page 311
በሳንዲኣጎ፣ካሊፎረኒያ በ1929 ቤተ ሳሬም የሚባል ቤት የተሰራበት ትንሽ መሬት ኣለ
“and the purpose of acquiring that property and building the house was that there might be some tangible proof that there are those on earth today who fully believe God and Christ Jesus and in His kingdom, and who believe that the faithful men of old will soon be resurrected by the Lord, be back on earth, and take charge of the visible affairs of earth.” Salvation, Watchtower Bible and Tract Society, by J. F. RUTHERFORD, page 311
የዚህ ንብረት እና የቤት ግንባታ አላማ ዛሬ ምድር ላይ ያሉት ሙሉ በሙሉ እግዚኣብሄርን፣እየሱስ ክርስቶስን እና መንግስቱን የሚያምኑት እና ታማኝ የድሮ ሰዎች በቅርቡ በጌታ ከሞት እንደሚነሱና ወደ መሬት ተመልሰዉ ምድራዊ ኑሮ እንደሚኖሩ ተጨባጭ ማረጋገጫ ስላላቸዉ ነዉ፡፡
“to be used by the president of the Society and his assistants for the present, and thereafter to be for ever at the disposal of the aforementioned princes on the earth.” Salvation, Watchtower Bible and Tract Society, by J. F. RUTHERFORD, page 311
ለጊዜዉ የማህበሩ ፕሬዝዳንት እና ራዳቶቻቸዉ ይጠቀሙና ከዚያ በኃላ እስከ ማጨረሻዉ ከላይ ለጠቀስናቸዉ ልዑላን[እነ አብርሃም] ይሰጣል፡፡
“and if and when the princes do return and some of them occupy the property, such will be a confirmation of the faith and hope that induced the building of Beth-Sarim.” Salvation, Watchtower Bible and Tract Society, by J. F. RUTHERFORD, page 311

ልዑላኑ [እነ አብርሃም] ሲመለሱ የተወሰኑት ይህን ንብረት ይኖሩበታል፣ይህ እምነት እና ተስፋ ቤተሳሬምን እንድንሰራ አድርጎናል፡፡


ሳልቬሽን ከሚባለዉ መጽሓፋቸዉ ገጽ 312 ላይ የተወሰደ የቤተሳሬም ምስል

 “was built, in 1930, and named "Beth- Sarim", meaning "House of the Princes”. The New World, Watchtower Bible and Tract Society,1942, page 104
“በ1930 ተሰራ፣ስሙም ቤተሳሬም ፣ትርጉሙም የልዑሎች ቤት ነዉ፡፡” House of the Princes”. The New World, Watchtower Bible and Tract Society,1942, page 104
“It is now held in trust for the occupancy of those princes on their return. The most recent facts show that the religionists of this doomed world are gnashing their teeth because of the testimony which that "House of the Princes" bears to the new world” House of the Princes”. The New World, Watchtower Bible and Tract Society,1942, page 104
“እሱም ልዑሎቸቹ ሲመለሱ እንዲኖሩበት ተጠብቆ ተይዞዋል፡፡በዚህ የኣዲሱ አለም ምስክር የልዑሎች ቤት ላይ የዚህ  ክፉ አለም ሀይማኖተኞች ጥርሳቸዉን እያፏጩበት ነዉ፡፡ “House of the Princes”.The New World, Watchtower Bible and Tract Society,1942,page 104
ከላይ እንደምንረዳዉ ቤተሳሬም የተሰራዉ እነ ኣብርሃም እንዲኖሩበት ነዉ፡፡
በጃንዋሪ 8 ፣1942 ራዘርፎርድ ሞተ፡፡
የይሖዋ ምስክሮችም ተስፋ ቆረጠዉ ቤተሳሬምን ሸጡት፡፡
“The audience...applauded when informed that the Society’s board of directors had voted unanimously to dispose of Beth-Sarim, either by outright sale or by rent, because it had fully served its purpose and was now only serving as a monument quite expensive to keep; our faith in the return of the men of old time whom the King Christ Jesus will make princes in ALL the earth (not merely in California) is based, not upon that house Beth-Sarim, but upon God’s Word of promise.” The Watchtower, 15 December 1947, page 382.
የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ቤተሳሬምን ነመሸጥ ወይም ለማከራየት ወስነዋል፣ምክንያቱም ኣላማዉን ሙሉ በሙሉ አገልግሎዋል፤አሁን እንደ ሀዉልት ብች እያገለገለ ነዉ፣ንጉስ እየሱስ ክርስቶስ የምድር ሁሉ ልዑሎች የሚያደርጋቸዉ የደሮ ሰዎች የማማለስ እምነታችን በቤተሳሬም ሳይሆን በእግዚኣብሄር የተስፋ ቃል ላይ ነዉ፡፡
“And ultimately, with its sale in 1948” BETH-SARIM: A Monument to a False Prophet and to False Prophecy ፣by Edmond C. Gruss and Leonard Chretien፣ page 6
“በመጨረሻም በ1948 ተሸጠ”  BETH-SARIM: A Monument to a False Prophet and to False Prophecy ፣by Edmond C. Gruss and Leonard Chretien፣ page 6
የይሖዋ ምስክሮች ሀሰተኛ ነብይ ናቸዉ፡፡
ራዘርፎርድ ስለሀሰተኛ ነብይ እንዲህ ተጠይቆ ነበር፡፡
"How are we to know whether one is a true or a false prophet?" The Watch Tower, 15 May 1930, 154.

“ሀሰተኛ እና እዉነተኛ ነብይን እንዴት እንለያለን;”መጠበቂያ ግንብ ሜይ 15፣1930፣ገፅ 154
His answer was,
 "If he is a true prophet, his message will come to pass exactly as prophesied. If he is a false
prophet, his prophecy will fail to come to pass. This rule is laid down by God himself, through Moses, as follows:.... — Deut. 18:21, 22." The Watch Tower, 15 May 1930, 154.

መልሱም ይህ ነበር
“እዉነተኛ ነብይ ከሆነ፣ትንቢቱ በትክክል ይፋጸማል፡፡ሀሰተኛ  ነብይ ከሆነ፣ትንቢቱ አይፈጸምም፡፡ይህ ህግ እግዚኣብሄር በሙሴ በኩል እንዲህ አስቀምጦታል…--ዘዳግም 18፡21፣22” መጠበቂያ ግንብ ሜይ 15፣1930፣ገፅ 154
የይሖዋ ምስክሮች የ1925ቱ የእነአብርሃም ስጋዊ ትንሳኤ አምላካዊ ፣መጽሓፍ ቅዱሳዊ ነዉ ብለዉ ቢተነብዩም አልተፈጸማም፡፡ስለዚህ እንደ ፣መጽሓፍ ቅዱስም፣እንደ ራዘርፎርድም የይሖዋ ምስክሮች ሀሰተኛ ነብይ ናቸዉ፡፡

ኦሪት ዘዳግም 18፡20 ላይ ሀሰተኛ ነብይ እንዲገደል ያዛል፡፡
በመጨረሻም ተስፋ ቆርጠዉ ቤቱንም ሸጡት፡፡
ቤተ ሳሬም ፣የሀሳዊ (ሀሰተኛ) ነብይ ሀዉልት ሆኖ እስከ አሁን የይሖዋ ምስክሮችን አያሸማቀቀ ይኖራል ፡፡



ቤተሳሬምን በቪዲዮ


መግለጫ፡
1)  የመጠበቂያ ግንብ እና ሌሎችም የአማርኛ ትርጉሞች የኔ ናቸዉ፡፡
2) A Monument to a False Prophet and to False Prophecy ከሚለዉ መጽሓፍ ዉጪ ሁሉም የራሳቸዉ የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፎች ናቸዉ፡፡
3) የይሖዋ ምስክሮችን ከ1879 እስከ 1949 ያሉትን ጽሁፎች ከዚህ በማግኛት መረጃዎችን ማጣራት ይችላሉ፡፡http://www.jwfacts.com/watchtower/historical-publications.php



የአለም ፍጻሜ እና የክርስቶስ ዳግም ምጽኣት (1914)


የአለም ፍጻሜ እና የእየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽኣት (1914)፡-
የይሖዋ መስክሮች ትንቢተ ዳንኤልን (ምዕራፍ 9፡24፣26 ሰባት ሱባኤ እና ስልሳ ሰባት ሱባኤ የሚለዉን) ትከክለኛዉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነዉ ፣ገጽ 199 እና destruction of the Kingdom of Judah by Nebuchadnezzar in 607 B.C.(
Jerusalem did not fall in 607 B.C.
) ዘመን በመዉሰድ የእየሱስ ዳግም ምጽኣት እና የአለም ፈጻሜ በ1914 ነዉ ብለዉ ተንብየዉ ነበር፡፡በመሁኑም ( 539 B.C. was the destruction of Babylon.) የይሖዋ ምስከሮች 539 የባብሎን መሰራረስ በማለት የእያሩሳሌምን መዉደቅ ደግሞ 607 ነዉ ይላሉ፡፡
"The date of 539 B.C.E. for the fall of Babylon can be arrived at not only by Ptolemy's canon." Insight on the Scriptures p.454
ምንም እንኳን  የይሖዋ ምስክሮች  የእየሩሳሌም መዉደቅ በ607 ከክርስቶስ ልደት በፊት ቢሉም ሌሎች መራጃዎች በ587 እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡
READ EVIDENCE FROM 607: 1914 : Seven Times, jw FACTS
የይሖዋ ምስክሮች በ587 የሚለዉ መረጃዉ የተሳሳተ ፣ እምነት የማይጣልበቸዉ የኢአማኒያን ስሌት እና መጽሓፍ ቅዱሰዊ ያልሆነ ነዉ ብለዉ ያጣጥሉታ፡፡ነገር ግን እነሱ ያስቀመጡት 607 ትክክለኛ በሚታመነዉ የእግዚኣብሄር ቃል የተቀመጠ ይሉታል፡፡በተጨማሪም ሌሎቹ ምንም ይበሉ ምን እኛ በመጽሓፍ ቅዱስ የተቀመጠዉን (607ን ) ያለምንም ጥርጥር እነቀበላለን የላሉ፡፡
"If we follow the accurate timekeeping of Jehovah God as recorded in his Word, we see that the desolation of Judah ran from 607 to 537 B.C.E. and will thereby avoid making the mistake of the chronologers of Christendom who ignore the prophecy of the seventy years' desolation and date Jerusalem's destruction as occurring in 587 B.C.E. They limit the desolation of Jerusalem and the land of Judah to merely fifty years, accepting the unreliable calculations of pagan historians rather than the infallible Word of God." Watchtower 1965 Sep 15 p.569 
"However, where the interpretation of these findings conflicts with clear statements in the Bible, we accept with confidence what the Holy Scriptures say, whether on matters related to chronology or any other topic." Watchtower 1989 Mar 15 p.22
ነገር ግን ይህ የይሖዋ ምስክሮች ሀሳብ መሰረተቢስ እና መልሶ ራሳቸዉን
የይሖዋ ምስክሮች የባብሎን መሰራረስ ዘመን 539ን ለማረጋገጫነት የተጠቀሙት አርኪኦሎጂኣዊ መረጃዎችን እና ታሪካዊ መዛግብትን ነዉ፡፡ለምሳሌ ካምባይሲስ የተባለዉን ንጉስ 7ኛ ንግስና አመት ሰነፈላካዊ ሰንተረዥ (astronomical tablet) እና የምሁራንን (Strassmaier, Kugler, Oppolzer and Gingerich) ስራ ተጠቅመዉ ነዉ፡፡
"A Babylonian clay tablet is helpful for connecting Babylonian chronology with Biblical chronology. This tablet contains the following astronomical information for the seventh year of Cambyses II son of Cyrus II: … (Inschriften von Cambyses, König von Babylon, by J. N. Strassmaier, Leipzig, 1890, No. 400, lines 45-48; Sternkunde und Sterndienst in Babel , by F. X. Kugler, Münster, 1907, Vol. I, pp. 70, 71). … Thus, this tablet establishes the seventh year of Cambyses II as beginning in the spring of 523 BCE. This is an astronomically confirmed date." Insight on the Scriptures p.453
ይህን ከተቀበሉ በኋላ በ(Ptolemy’s Canon) የተቀመጠዉን አለማዊ የዘመን ቅደምተከተል (secular chronology) በመጠቀም የባብሎንን መፈራረስ 539 የስቀምጣሉ፡፡
"The date of 539 B.C.E. for the fall of Babylon can be arrived at not only by Ptolemy's canon." Insight on the Scriptures p.454
ይህን ለ539 የተጠቀሙትን ማስረጃ ደግሞ 607 የእያሩሳሌም መዉደቅ የሚለዉን ስለማይስማማበት መልሰዉ የመረጃዉ አስተማማኝነት አጠያያቂ ነዉ ይላሉ፡፡
"Though the classical historians and the canon of Ptolemy disagree with this date [607 B.C.], valid questions can be raised about the accuracy of their writings."Watchtower 2011 Oct 1 p.31
ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች የባብሎንን መፈራረስ 539 መሆኑን ለማስረጃነት የተጠቀሙት ማስረጃ ራሱ  የእያሩሳሌም  መፈራረሰስ በ607 ሳይሆን በ587 መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ከግለዊ የጽሓፍ ቅዱስ አረዳዳቸዉ ዉጪ ስለ እያሩሳሌም በ607 መፈራረስ  ምንም ማስረጃ የለቸዉም፡፡ ግለዊ የጽሓፍ ቅዱስ አረዳዳቸዉም ቢሆን 607ን ለማግኘት መነሻዉን (539ን) ከታሪክ ጸሓፍዎች ማግኘት ኣለበቸዉ፡፡የይሆዋ ምስክሮች ደግሞ እነዚህ ታሪካዊ ጽሁፎች ላይ ያለዉን የእያሩሳሌም መዉደቅ 587 መሆኑን የሚያሳየዉን ትልቅ መረጃ መልስ መስጠት ይከብዳቸዋል፡፡ምክንያቱም ነሱም ይሄንኑ ማስረጃ ስለሚጠቀሙ ነዉ፡፡  (put ref or rethink about this)
የሚገርመዉ ነገር የይሆዋ ምስክሮች  ጽሁፎች ራሳቸዉ  የእያሩሳሌም መዉደቅ 607 ነዉ ያሉት  ስህተት መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሁሉም ከየይሖዋ ምስክሮች ጽሑፎች የተወሰዱ ናቸዉ፡፡

Babylon fell
"Babylon fell in 539 B.C." Babylon the Great Has Fallen - God's Kingdom Rules p.184
539 B.C.
Plus Nabonidus
"On the basis of cuneiform texts he is believed to have ruled some seventeen years(556-539 B.C.E.)." Aid to Bible Understanding - Nabonidus p.1195
17 years
Plus Labashi-Marduk
"Labashi-Marduk ... was a vicious boy, and within nine months he had his throat cut by an assassin." Babylon the Great Has Fallen - God's Kingdom Rules p.184
1 year
Plus Neriglissar
Neriglissar ... reigned four years Babylon the Great Has Fallen - God's Kingdom Rules p.184
4 years
Plus Evil-Merodach
"After reigning but two years King Evil-Merodach was murdered"Babylon the Great Has Fallen - God's Kingdom Rules p.184
2 years
PlusNebuchadnezzar
"Nebuchadnezzar ruled as king for 43 years" Insight on the Scriptures, Volume 2 p.480
43 years
Equals start of Nebuchadnezzar's reign
Calculated by adding above figures
606 B.C.
MinusNebuchadnezzar's 19th year
2 Kings 25:8-9 "And in the ... nineteenth year of King Neb·u·chad·nez´zar ... the servant of the king of Babylon, came to Jerusalem. And he proceeded to burn the house of Jehovah"
19th year
Date for Destruction
Therefore calculated as:
587 B.C.
የይሆዋ ምስክሮች የታሪክ ጸሓፍዎች እንዳስቀመጡት እናሱም የእነዚህን ነገስታት ዘመን በቅደምተከተል በመጠበቂያግንብ 1965፣ጃኑዋር 1 ገጽ 29 ላይ ዘርዝረዋል፡፡
 Evil-merodach reigned two years and was murdered by his brother-in-law Neriglissar, who reigned for four years, which time he spent mainly in building operations. His underage son Labashi-Marduk, a vicious boy, succeeded him, and was assassinated within nine months. Nabonidus, who had served as governor of Babylon and who had been Nebuchadnezzar's favorite son-in-law, took the throne and had a fairly glorious reign until Babylon fell in 539 B.C.E." Watchtower 1965 January 1 p.29
የጀማሪያዉ የይሖዋ ምስክሮች ፕሮዝዳንት ረስል የእስራኤል መዉደቅ በ607 ሳይሆን በ606 እንደሆነ ኣሰተምሮ ነበር፡፡ይህምንንም  አስተምሮ ሁለተኛዉ ፐርዝዳንት ራዘር ፎረድ ቀጥሎበት ነበር፡፡ሁለቱም የባቢሎን መዉደቅ 536 እንደሆነ ነበር ያስተማሩም፡፡
The Bible evidence is clear and strong that the "Times of the Gentiles" is a  period of 2520 years,  from the year B. C. 606 to and including A. D. 1914. ( Millennial Dawn Volume 2) Studies In the Scriptures Series II - The Time Is at Hand page 79
both  secular and religious histories with marked unanimity agreeing with Ptolemy's  Canon, which places it B. C. 536.  And if  B. C. 536 was the year in which the seventy years of Jerusalem's desolation ended and the restoration of the Jews began, it follows that their kingdom was over- thrown just seventy years  before B. C. 536, i.e., 536 plus 70, or B. C. 606.  This gives us the date of the beginning of the Times of the Gentiles-B.  C. 606. ( Millennial Dawn Volume 2) Studies In the Scriptures Series II - The Time Is at Hand  page 80
Now bear in mind the date already found for the beginning of these GC ntile Times-viz.,  B. C. 606-while  we proceed to examine the evidence proving their length to be 2520 years, ending A. D. 1914.  ( Millennial Dawn Volume 2) Studies In the Scriptures Series II - The Time Is at Hand page 87
twenty-five hundred and twenty years, they will end A. D. 1914.  (2520 - 606 = I 914.)  ( Millennial Dawn Volume 2) Studies In the Scriptures Series II - The Time Is at Hand page  90
 The period from the time of the restoration of the Jews from Babylon, at the close of the seventy years desolation of their land, in the first year of Cyrus,  down to the date known as A. D. I, is not covered by Bible history.  But, ,as before stated, it is well established by secular history as a period of 536 yearsPtolemy, a learned Greek-Egyptian, a geometer and astronomer, has well established these figures.  They  are generally  accepted by scholars, and known as Ptolemy's  Canon.  ( Millennial Dawn Volume 2) Studies In the Scriptures Series II - The Time Is at Hand page  51
"It seems to be well settled now in the minds of the anointed that the Gentile Times, which began in 606 B.C., ended in 1914: ..." Watchtower 1925 Mar 1 p.67 
በ1940ዎቹ የይሖዋ ምስክሮች ከባቢሎን መዉደቅ በኋላ 2520 ያሉት የስሌት ስህተት እንዳለበት ራሳቸዉ ኣመኑ፡፡በመሆኑም የ1914ን አስተምሮኣቸዉን ለመጠበቅ ሲሉ የእያሩሳሌምን መዉደቅ ከ606 ወደ 607 ቀየሩት፡፡ይህም እንደገና 536ትን ወደ 537 እንዲቀይሩ አደረጋቸዉ፡፡
"Providentially, those Bible Students had not realized that there is no zero year between "B.C." and "A.D." Later, when research made it necessary to adjust B.C. 606 to 607 B.C.E., the zero year was also eliminated, so that the prediction held good at "A.D. 1914."-See "The Truth Shall Make You Free," published by theWatch Tower Society in 1943, page 239." Revelation - Its Grand Climax at Hand! p.105
ከ606 ወደ 607 የተደረገዉ ለዉጥ የለምንም ታሪካዊ ማስረጃ በዘፈቀደ ነበር፡፡የዚህ ለዉጥ ትልቁ ችግር የነበረዉ የታሪክ ጸሓፍዎች የባቢሎን መዉደቅ በ539 መሆኑን በ1940ዎቹ ማረጋገጣቸዉ ነበር፡፡የይሖዋ ምስክሮችም 536 የባቢሎን ዉድቀት ዘመን መሆኑን ተስማሙ፡፡
"The date of 539 B.C.E. for the fall of Babylon can be arrived at not only by Ptolemy's canon." Insight on the Scriptures p.454
ነገር ግን አሁንም የ1914ትን አስተምሮኣቸዉን ለመጠበቅ 70 አመት (የባቢሎን ግዛት ዘመን) የሚያበቃዉ ከባቢሎን ዉድቀት ዘመን (539) ሳይሆን እስራኤሎች ከስደት ወደ ሀገራቸዉ ከተመለሱበት አመት ነዉ በማለት ይህም በ537 ነዉ ብለዋል፡፡
"There is strong evidence - and most scholars agree - that the Jewish exiles were back in their homeland by 537 B.C.E." Watchtower 2011 Oct 1 p.31[u1] 
ነገር ግን ነገር ግን የይሖዋ ምስክሮች የእስራኤሎች ወደ እየሩሳሌም መመለስ በ537 ነዉ ኣሉ እንጂ ምንም ማስረጃ አላቀረቡም፡፡እንዲሁም  በትንቢተ ኤረሚያስ ይህ ሰባ አመት የሚያበቃዉ በባቢሎን ዉድቀት ዘመን እንደሆነ የገልጻል፡፡ይህም እንደ የይሖዋ ምስክሮች በ539 ማለት ነዉ፡፡
እነዚህም ኣሕዛብ ለባቢሎን ነዱስ ሰባ ዓመት ይገዛል፡፡ሰባዉ አመት በተፈጻመ ጊዜ ፣የባቢሎንን ንጉስና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢኣታቸዉ እቀጣለሁ፣ይላል እግዚኣብሔር፣የከላዳዊያንንም ምድር ለዘላለም ባድማ አደርጋታለሁ፡፡ ትንቢተ ኤረሚያስ 2511-12::
ስለዚህ የእስረኤል ዉድቀት 607 ሳይሆን 539+70 = 609 ይሆናል ማለት ነዉ፡፡በመሆኑም በ2520 ስሌቱ ዉጤት 1914 አይሆንም ማለት ነዉ፡፡



በዚህ ዙሪያ እና ለየይሖዋ ምሰክሮች መጠበቂያ ግንብ ኦክቶበር 1 2011 እና ኖቬምበር 1 2011 መልስ ሰፊ ማብራሪ በእንድሊዝኛ እነዚህን ያንብቡ፡-
 Carl Olof Jonsson

Part 1
Part 2
Doug Mason
Part 1
Part 2-A
Part 2_B











ዋቢ መጻህፍት፡-

እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ (ምሳሌ 8፡22)

በይብራይስጥ የይሖዋ ምስክሮች ራስ ምታት ምሳ 8:22 " የመንገዱ መጀመሪያ "

አንባቢያን በይብራይስጥ ማለቴን አስተውሉ፡፡ ብሉይ ኪዳን መጀመሪ የተጻፈው በይብራይስጥ ቋንቋ ነው፡፡ ሌሎቹ ሁሉ ትርጉም ናቸው፡፡ ምናልባትም የመጀመሪው ትርጉም በግሪክ ቋንቋ የተጻፈው የሰባዎቹ ልቃውንት ትርጉም የሚባለው ነው፡፡ ይህ ትርጉም የተሰራው በግሪኮች ቅኝ ግዛት እና ወረራ ምክንየት እስራኤላዊያን በየአገሩ ተበትነው ስለነበር እና የግሪክ ቋንቋ (ጽርዕ) ዛሬ እንገሊዝኛ በየ አገሩ እንደሚወራው በሰፊው የግሪክ ግዛት ልክ አቴንሰ የሚወራውን የህል ይወራ ነበር፡፡ መሆኑም የእስራኤል ትውልዶች ቋንቋቸው መናገር እያቃታቸው ሲመጣ ይህ የግሪክ ትርጉም ተሰራ፡፡ የግሪክ ቋንቋ ከክርስቶስ ልደት በኋላ እንኳን በሰፊው በአገልግሎት ላይ ነበረ፤ የወቅቱ የቤተክርስቲያን አባቶችም ብዙ ጽሁፎቻቸውን የጻፉት በግሪክ ነበር፣ እንዲሁም አዲስ ኪዳን መጀመሪያ በግሪክ ነበር የተጻፈው፡፡ በወቅቱም በቋንቋው አገልግሎት ስፋት የተነሳ ፣ በሰፊው በአገልግሎት ላይ ይውል የነበረው ጠብሉይ ኪዳን መጽሃፍ ከይብራይስጡ ይልቅ ፣ ትርጉም የሆነው የግሪኩ የሰባዎቹ ልቃውንት መጽሓፍ ነበር፡፡ እነ አርዮስም ሲያነሱ ለነበሩት የክህደት ጥያቄዎች ይጠቀሙ የነበረው ይሄንኑ ትርጉም ነበር፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብዙ አርዮሳዊያን እየሱስ ፍጡር ነው ለማት በብዛት የሚጠቀሙት የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ምሳ 8፡22 ላይ ያለውን ነው፡፡ ‹‹ እግዚኣብሄር የመንገዱ መጀመሪያ ….?››

የትርጉሞች ዳሰሳ፡-


የዚህ ሀይላቃል ቁልፉ ቦታ ከላይ በ… የተውኩት ነው፡፡ በአማርኛ ትርጉሞች ‹‹አደረገኝ 1962 እና1980›› ፤ቀድሞ ይሖዋ ምስክሮች ይጠቀሙት የነበረው መደበኛ ትርጉም ደግሞ ‹‹አድርጎ አመጣኝ›› ሲል የይሖዋ ምስክሮች የራሳቸው ትርጉም ደግሞ ‹‹ አድርጎ ፈጠረኝ ›› ይላል፡፡ የመጀመሪው ትርጉም ከላይ እንደጠቀስኩት የግሪኩ ሰባዎቹ ልቃውንት ትርጉም ነው፡፡ በዚህ ትርጉም ἔκτισέν (ፈጠረኝ ) ተብሎ ነው የተተረጎመው፡፡ ብዙ አርዮሳዊያንም ይህን ትርጉም እየጠቀሱ ነበር የሚከራከሩት፤ አባቶችም ቢሆኑ ይሄንኑ ትርጉም በመጠቀም ነበር መልስ ለመስጠት ይጥሩ የነበረው፡፡ ጥቂት አባቶች ግን ወደ መሰረታዊው የይብራይስጥ ትርጉም ሲሄዱ ነገሩ ለአርዮሳዊያን እንዳሰቡት አልጋ ባልጋ አለመሆኑን ተረዱ፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ቅዱስ ባሲሊዮስ (St.Basil) አንዳንድ ይብራይስጡን መጽሃፍ ያጠኑ ‹‹ ἔκτισέν ሳይሆን  έκτήσατό με መሆን እንዳለበት ደርሰውበታል ፤ ይህ ደግሞ ፍጥረታዊ ነው ብለው ለሚክዱት አርሳዊያን ትልቅ እንቅፋት ነው ›› በማለት የገለጹት፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ባሲሊዮስ ይህን ክፍል ከዘፈ 4፡1 ጋር አመሳክረውታል፡፡

ጥቂት ዳሰሳ ስለ ጥበብ መጽሃፈ ምሳሌ 8፡-


ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል ቃል በቃል እየሱስ ብሎ ወይም የእግዚኣብሄር ልጅ ብሎ አይናገርም፤ ይልቁንስ ጥበብን በሰውኛ ዘይቤ ይገልጻል፡፡ለምሳሌ በምሳ 7፡3 ላይ ጥበብ እህት ተብላለች፡፡እየሱስ ግን ተባዕታዊ ፆታ ነዉ፡፡ ነገር ግን  እየሱስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡24 ላይ “እያሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ” መባሉን ምክንያት በማድረግ ፤ምሳ 8፡22 እየሱስ መጀመሪያ ስለመፈጠሩ ያወራል ይላሉ አርዮሳዊያን፤ምክንያቱም እነሱ እየሱስ ፍጡር ነው የሚል አስቀድሞ በአዕምሮኣቸው አለ፡፡እዚህ ላይ ሁሉም ክርስቲያን ማስተዋል የለበት እየሱስ በእግዚኣብሄር ጥበብ ተመሰለ እንጂ ምሳ8፡22 የሚያወራዉ ስለ አምላክ ጥብብ ነዉ፡፡ የእየሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ መባልን፤ይህን የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል እንዳለ ከተረዳን በኋላ አያይዘን እንመለከታለን፡፡ 

ቀናኒ ትርጉሙ ምንድን ነዉ?


በዚህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል በተለያየ መንገድ የተተረጎመው የይብራይስጥ ቃል ‹‹ቀናኒ›› የሚል ነው፡፡ ቡርኔይ የሚባል ምሁር በዚህ ቃል (ቀናኒ) ትርጉም እና በምሳሌ 8፡22 ትርጉም ላይ ሰፊ ምርምር አድረጓል፡፡ጥናቱንም The Journal of Theological Studies ላይ አሳትሟል፡፡ ይህም ሰዉ (ቡርኔይ) ይህ የአይሁድ ቃል (ቀናኒ) የተለያዩ ትርጉሞች እንዳሉት ከመጽሓፍ ቅዱስ በመጥቀስ ያስረዳል፡፡ከነዚህም ትርጉሞች ዉስጥ መፍጠር (create) እና መዉለድ (beget) የሚሉት ይገኛሉ፡፡ በመዝ 139፡13 አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በለበት ጊዜ ፈጥረሃል ተብሉ የተተረጎመዉ ይሀዉ ቀናኒ የሚለዉ ቃል ነዉ፡፡ በዘፍ 4፡1 ላይ ሄዋን ቀኤልን ስለመዉለድዋ በተናገረች ጊዜ ቀናኒ የሚለዉን ቃል ተጠቅማለች፡፡ አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም። ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ (ቀናይተ) አለች።(ዘፍ 4፡1) የሄዋን የመጀመሪያ ለጅም ስም ቃየን የሚለዉ ከዚህ ቃል ጋር የተያያዘ ነዉ፡፡ ስለዚህ ከላይ እንደምንረዳው ቀናኒ የሚለው የይብራይስጥ ቃል ቢያንስ ፈጠረኝ ወይም ወለደኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ በምሳ 8፡22 ላይ የተኛውን ትርጉም ነው የያዘው?

ምሳ 8፡22 የቀናኒ ትርጉም መዉለድ ነዉ ወይስ መፍጠር ነዉ?


የዚህ መልስ በግል ወይም ሀይማኖታዊ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆን የለበትም ፡፡ ብዙ ትርጉም ያለውን ቃል ትክክለኛ ትርጉሙን ማወቅ የሚቻለው በዙሪያው ካሉት ሀሳቦች ነው፡፡ ለምሳሌ በዘፍ 4፡1 ላይ ይህ ቃል ስለመውለድ ስለመሆነ በዙሪያው ያሉት ቃላት ጸነሰች ወለደች የሚሉት ቃላት ያሳያሉ፡፡ ይህም ምሁር የዚህን ቃል(ቀናኒ) ትርጉም በዚህ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል (ምሳ 8፡22) ዉስጥ ከሁለቱ የተኛዉ እንደሆነ ለመለየት የሚቀጥሉትን አንቀጾች ዉስጥ ያሉትን ፍንጮች ማየት ያስፈልጋል ይላል፡፡ለዚህም በቁጥር 24፣25 ‹‹ሆላልቲ›› የሚሉትን የይብራይስጥ ቃላት ትርጉም የስቀምጣል፡፡ በምሳሌ 8፡24-25 ላይ ያለዉ ሆላልቲ የሚለዉ ቃል ደግሞ ያለጥርጥር  ‹‹መዉለድን›› ይገልጻል ይላል፡፡ ይህን ቃል ከላይ የጠቀስኳቸው ትርጉሞች በሙሉ ‹‹ተወለድኩ›› ብለው ነው የተረጎሙት፤ የይሖዋ ምስክሮችን ጨምሮ፡፡ ቡርኔም እንዲህ በማለት ያብራራል፡-

“in  v - 24, 25 (stage 3) חוֹלָ֑לְתִּי (ሆላልቲ) means ' I was brought forth with travail' (birth),” C:F.BurneyChrist as the Apex of Creation (Prov. viii 22, Col. i 15-18, Rev. iii 14.)” The Journal of Theological Studies page 165 (አማርኛዉ የኔ ነዉ)

በቁጥር 25 (ሆላለቲ የሚለዉ የይብራይስጥ ቃል) ያለጥርጥ መዉለድ ማለት ነዉ ካለ በኋላ፣በዚህ ምክንያት በቁጥር 22 ያለዉ ቀናኒ የሚለዉ የይብራይስጥ ቃል ትርጉም ፈጠረኝ ሳይሆን ወለደኝ ነዉ ይላል፡፡  

“the inference is obvious that the figure described in v. 22 by (stage 1) קָ֭נָנִי (ቀናኒ)is 'beget me' (act of procreation).” ibd: page 165 (አማርኛዉ የኔ ነዉ)

 ነገር ግን ፈጠረኝ ወይም ተመሳሳይ ትርጉም ለዚህ ቃል (ምሳ 8፡22 ቀናኒ) ለመስጠት የመረጡት አካላት ከግል እና ሀይማኖታዊ ፍላጎታቸዉ ዉጪ ምንም ምክንያት ሊኖራቸዉ አይችልም፣ምክንያቱም ይህ ቃል ሁለቱንም (ፈጠረኝም ወይም ወለደኝም) ትርጉሞች ስላሉት ነዉ ፡፡ እንደ አገባቡ ግን ፈጠረኝ የሚለው ትርጉም ድጋፍ የለውም፡፡

ቡርኔይ “in the beginning “የሚለዉም ስህተት ነዉ ይላል፡፡ በአማርኛዉ ደግሞ ‹‹በመንገዱ መጀመሪ››ያ የሚለዉ ስህተት ነዉ ማለቱ ነዉ፡፡ ምክንያቱም “in” የሚለዉን ቃል የሚወክለዉ  (በ) የሚባለዉ የይብራይስጥ ቃል (ዘፍጥርት 1፡1 መጀመሪያ ላይ ያለዉ ማለት ነዉ) በምሳሌ 8፡22 ላይ የለም ይላል፡፡ 

2
Yah·weh   22
יְֽהוָ֗ה   22
Yahweh   22
N‑proper‑ms   22
7069 [e]
qā·nā·nî
קָ֭נָנִי
possessed me
V‑Qal‑Perf‑3ms | 1cs
7225 [e]
rê·šîṯ
רֵאשִׁ֣ית
at the beginning
N‑fsc
 
 

 
 
 1870 [e]
dar·kōw;
דַּרְכּ֑וֹ
of His way
N‑csc | 3ms
6924 [e]
qe·ḏem
קֶ֖דֶם
Before
N‑msc
4659 [e]
mip̄·‘ā·lāw
מִפְעָלָ֣יו
His works
N‑mpc | 3ms














*ይብራይስጥ ከቀኝ ወደ ግራ ነው የሚነበበው፡፡

ስለዚህ እንደ የይብራይስጡ በኩረ ጽሁፍ ምሳ8፡22፣ጥበብ የእግዚኣብሄር ስራ (ፍጥረት) መጀመሪያ ነች፡፡

የመንገዱ መጀመሪያ ማለትስ ምን ማለት ነው


መንገድ የተባለው ፍጠረትታት መሆናቸውን እዚያው ‹‹ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ›› መጀመሪያ ከማለቱም በላይ በተከታታይ የአምላክን ፍጥረታት ይተነትናል፡፡ እናም መንግድ የተባለው ፍጥረታት ናቸው፡፡ እናም ጥበብ ‹‹የእግዚኣብሄር ፍጥረታት መጀመሪያ ›› ተብላለች በዚህ ክፍል፡፡ ማስተዋል ያለብን ጥበብ ‹‹በእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ›› አልተባለችም፡፡ ‹በ› ቅጥያ ትልቅ ትርጉም ይሰጣል፡፡ በፍጥረት መጀመሪያ ማለት ፤ ከፍጥረታት ውስጥ መጀመሪያ ማለት ነው፤ ነገር ግን እንዲህ አልተባለም፡፡ የእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት የእግዚኣብሄር ፍጥረታት ምንጭ ወይም አስገኚ ማለት ነው፡፡ እግዚኣብሄር ሁሉንም ፍጥረታት የፈጠረዉ በጥበቡ እንደሆነ እዚሁ ምሳ 8፡30 ላይ ‹‹ዋና ሠራተኛ ነበርሁ›› ከሚለው እንረዳለን፡፡ ዋና ሰራተኛ ማለት የለጥበብ ምንም ነገር እንዳልተደረገ፤ ወይም አምላክ ሁሉንም የፈጠረው በጥበቡ እንደሆነ መግለጹ ነው፡፡ እንዲሁም በመዝ 104:24 ላይ ‹‹ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ›› በማለት አምላክ ሁሉን ያረገው ወይም የፈጠረው በጥበቡ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በመሆኑም እዚህ (ምሳ 8 ላይ) ጥበብ እንደ እግዚኣብሄር ፍጥረታት ምንጭነት/አስገኚነት ተነገረች እንጂ እንደ የመጀመሪያዋ ፍጥረት አይደለችም፡፡ይህም የአባይ መጀመሪያ/ምንጭ ኢትዮጲያ ነች እንደማለት ነዉ፡፡  በመሆኑም ይህ የይብራይስጥ የቋንቋ ምሁር የዚህ ምሳ 8፡22 ትርጉም እንደሚከተለዉ መሆን ኣለበት ይላል፡፡
“The Lord begat me as the beginning of His way, The antecedent of His works, of old.” ibd: page 168 (አማርኛዉ የኔ ነዉ)

ይህም በአማርኛ እንደሚከተለዉ ሊተረጎም ይችላል፡፡ “ጌታ የመንገዱን መጀመሪያ ወለደኝ፣የቀድሞ ስራዉ መጀመሪያ፡፡”

ስለዚህ ከመሰረታዊው ቋንቋ ነው የተረጎምነው የሚሉት የይሖዋ ምስክሮች ያለምንም ምክንያት በገዛ ፍላጎታቸዉ ፈጠረኝ ብለዉ ተርጉመዋል፡፡ የይብራይስጡ ማሳሌ 8፡22 የጥብብን መፈጠር አያስተምርም፡፡ አዚህ ላይ እያሱስ በጥበብ ተመሰለ እንጂ ጥበብ በእያሱ እንዳልተመሰለ መረዳት ኣለብን፡፡ስለዚህ ምሳሌ 8፡22ትን ስናነብ ጥበብን አስመልክተን ነዉ፡፡እግዚኣብሄር ሁሉንም ነገር የሰራዉ በጥበብ ነዉ፡

የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፡፡


አብዛኞቹ የአማርኛ መጽሃፍ ቅዱስ ትርጉሞች ቀናኒ የሚለዉን የይብራይስጥ ቃል አደረገኝ ብለዉ ትረጎመዋል፡፡ይህ በእርግጥ አደረገኝ ሲል በመዉለድ ይሁን በመፍጠር ግልጽ አይደለም፡፡ነገር ግን እነዚሁ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉሞች በቀጣይ ያሉትን ሆላልቲ የሚሉትን በትክክልም ተወለድኩ ብለዉ ስለሚተረጉሙ ምሳ 8፡22 ስለ ጥብብ መወለድ እንደሆነ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ስለዚህ የሀሳብ ግጭት የለበትም ለማለት ያስችላል፡፡ ይልቁንም በይብራይስጡ ያለውን አይነት ግርታ በውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡

ምሳ 8፡22-25
22፤ እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥  በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ። 23፤ ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ፤ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ።  24፤ ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ ተወለድሁ፥  የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ።  25፤ ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥  ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድሁ

ታዲያ የይሖዋ ምስክሮች ለምን ፈጠለኝ ብለዉ ተረጎሙ?


ትክክለኛዉን ትምህርት የማይታገሱበት ጊዜ ይመጣልና፤ከዚህ ይልቅ ከራሳቸዉ ፍላጎት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ጆሯቸዉን እንዲኮረኩሩላቸዉ በዙሪያቸዉ አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ፡፡2ኛ ጢሞ 4፡3 አአት (የይሆዋ ምስክሮች ትርጉም)

ምሳ 8፡22 እንደ ይሖዋ ምስክሮች ጥበብ ተፈጠርኩ ኣለች ስንል ምን ማለታችን ነዉ?


በመጀመሪያ እዚህ ላይ ምሳሌ 8 የሚያወራው ስለ ጥበብ መሆኑን ማስተዋል ኣለብን፡፡ ይህ ክፍል ሙሉ በሙሉ የሚያወራዉ ስለ ጥበብ በሰዉኛ ዘይቤ ነዉ፡፡ ኣንድም ቦታ እየሱስ ብሉ አይጠራም፡፡ ይህን ስል እየሱስ በእግዚኣብሄር ጥበብ አልተመሰለም ማለቴ አይደልም፡፡ ነገር ግን ስለጥበብ የተባለዉን በትክክል ከተረዳን በኋላ እየሱስ ለምን በእግዚአር ጥበብ እንደተመሰለ ማጥናት ኣለብን፡፡ ስለዚህ እዚህ ጋር (ምሳ 8፡22) ተፈጠረም ተወለደም ስንል በመጀመሪያ ጥበብን ነዉ እንጂ እየሱስን አይደለም፡፡ በእየሱስ ላይ ባለን አስተምሮ ተጽእኖም ይሁን በሌላ፣ጥበብ ተፈጠረች ብለን ሰንተረጉም የሚያስከተለዉን ክህደት እንደሚከተለዉ እናያለን፡፡

እዚህ ምሳ8፡22 ላይ ጥበብ ተፈጥራለች (በእግዚኣብሄር) ካልን፣ጥበብ ያለነበረችበት ጊዜ ነበር ስለሚሆን፣እግዚኣብሄር የጥበብ ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ምሳ8፡22 ላይ ጥበብ ተፈጥራለች ካልን፣ አምላክ በፊት ለዘላለም ጥበብ አልነበረዉም ማለት ነዉ፡፡ ይህም እግዚኣብሄር ከጥበብ አልባነት ወደ ጥበበኛነት ተለወጠ ማለት ነዉ፡፡ እኔ እግዚኣብሄር አልለወጥም እንደሚል አስተዉሉ (ት.ሚልክያስ 3፡6) ፡፡እግዚኣብሄር ደግሞ ሁሉንም ነገር በጥበብ ስለሰራ፣ጥበብ ለመፍጠር ደግሞ ጥበብ ስለሚያስፈልገዉ ራስዋ ጥበብ ልትፈጠር አትችልም፣እገዚኣብሄርም የሌለችዉን ጥበብ ባለቤት መሆን ስለማይችል፣እግዚኣብሄር ጥበበኛ ሳይሆን ይቀር ነበር ማለት ነዉ፡፡ስለዚህ ጥበብ ተፈጠረች ማለት እግዚኣብሄር ጥበበኛ አልነበረም የሚል ክህደት ያስከትላል፡፡ይህንንም ብዙዎች ያስተዋሉት አይመስልም፡፡ ‹‹<<ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ ›› የሚለዉ ይህን ነዉ፡፡

ጥበብ ተወለድኩ ማለትዋ ምን ማለት ነዉ?


እዚህ ምሳ8፡22 ላይ ጥበብ ተወለደች (በእግዚኣብሄር) ካልን፣የጥበብ ዘላለማዊነት ወለድኩሽ ባላት አካል ባህሪ ላይ ይመሰረታል፡፡ ጥበብን ወለድኩሽ ያለዉ አካል ዘላለማዊ ካልሆነ (የተፈጠረ ከሆነ) ከሱ የተወለደችዉም ጥበብ ዘላለማዊ አትሆንም (የተፈጠረች ትሆናለች)፡፡ ነገር ግን ጥበብን ወለድኩሽ ያለዉ አካል ዘላለማዊ ከሆነ (ያልተፈጠረ ከሆነ) ከሱ የተወለደችዉም ጥበብ ዘላለማዊ ትሆናለች (ያልተፈጠረች ትሆናለች)፡፡ስለዚህ በምሳ8፡22 መሰረት ጥብብ ዘላለማዊ እና ያልተፈጠረች ከመሆንዋም በተጨማሪ እግዚኣብሄር እኔ እግዚኣብሄር አልለወጥም ባለዉ መሰረት እግዚኣብሄር ከዘላለም እስከ ዘላለም በባህሪዉ ጥበበኛ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
ለምሳሌ ኣንድ አካል ከሰዉ ተወለድኩ ካለ የሰዉን ባህሪ ይላበሳል ማለት ነዉ፡፡በመሆኑም ወለደኝ ያለዉ ሰዉ ዘላለማዊ ካልሆነ ከሰዉ ተወለድኩ ያለዉም ዘላለማዊ አይሆንም ማት ነዉ፡፡ ስለዚህ ኣንድ አካል ከተፈጠረ ነገር ተወለድኩ ካለ እሱ ራሱ ፍጡር መሆኑን መናገሩን መረዳት ኣለብን ፡፡
ስለዚህ በምሳ8፡22 ላይ ጥብብ ከዘላለማዊዉ አምላክ ተወለድኩ በማለት ዘላለማዊነትዋን ትናገራለች፡፡-እግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ በማለት ደግሞ የፍጥረታት ምንጭ መሆንዋን ትገልጻለች፡፡
ጥበብ የመንገዱ መጀመሪያ ነች እንጂ መንገዱ መጀመሪያ (ፍጥረት) አይደለችም፡፡ስለዚህ ጥበብ በ-እግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ሳትሆን የ-እግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ናት እንደ ምሳ8፡22፡... ሀሳብ፡፡ ጥበብም ከዘላለማዊው አምላክ ተወለድኩ በማለት ዘላለማዊነትዋን ትናገራለች፡፡ይህም እኔ እግዚኣብሄር አልለወጥም እንዳለዉ እግዚኣብሄር ከዘላለም እስከዘላለም በባህሪዉ ጥበበኛ መሄኑን ይገልፃል፡፡ስለዚህ ጥበብ የእግዚኣብሄር የመጀመሪያ ፍጥረት አይደለችም፡፡ይልቁንም የባህሪዉ ነች፡፡

ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይነሳሉ፡፡እነዚህ ሰዎች ጥፋት የሚያስከትል ኑፋቄ በስዉር ያስገባሉ፤ የዋጃቸዉን ጌታ እንኳ ሳይቀር ክደዉበራሳቸዉ ላይ ፈጣን ጥፋት ያመጣሉ፡፡2ኛ ጴጥ 2፡1 አአት

ትልቁ የአዳም ስህተት እንኳን እግዚኣብሄርን (ሁሉን አዋቂ) ለመሆን ተመኘ እንጂ የእግዚኣብሄርን ምንነት (ባህሪ) አልካደም፡፡ ስለዚህ ጥብብ ተፈጠረች ስንል እግዚኣብሄርን እየካድን መሆናችንን መዘንጋት የለብንም፡፡ ልጁን ስንክት አብንም እንክዳለን ፡፡ ይሖዋ ምስክሮች እየሱስን ፍጡር ለማለት ሲሞክሩ ይሆዋ የሚሉትን አምላካቸውን ጥበብ አልባ ብለው ክደውታል፡፡ <<ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።›› (1ኛ ዮሐ 2፡23) የቆጡን ኣወርድ ብላ የብብትዋን ጣለች እንደሚባለዉ የይሖዋ ምስክሮች እየሱስን በመካዳቸዉ ብቸኛ አምላካችን ይሖዋ የሚሉትንም ክደዋል፡፡ይህን አላስተዋሉም፡፡ሁላችንም ይህን ልንነግራቸዉ ይገባል፡፡ ‹‹<<ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ ›› የሚለዉ ይህን ነዉ፡፡


የእግዚኣብሄር ጥበብ እና እየሱስ፡-



እየሱስ ክርስቶስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡24 ላይ “እያሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ” ተብሎኣል፡፡ ከዚህም በጨማሪ እየሱስ በራዕ 3፡14 ላይ ‹‹ የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ›› ተብሎኣል፡፡ ይህን ራዕይ 3፡14ን ትርጉም ደግሞ መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አዲስ ኪዳን የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ ነው፡፡ ይህን ክፍል የተለያዩ ትርጉሞች እንደሚከተለው ተርጉመዋል፤ ‹‹በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው 1962፣1980›› እንዲሁም የይሖዋ ምስክሮች ትርጉም‹‹ ከአምላክ ፍጥረት የመጀመሪያ የሆነው ›› ፡፡ የይሖዋ ምስክሮች እንግሊዝኛው ደግሞ ‹‹the beginning of the creation by God:
›› በማለት ተርጉሞታል፡፡የእንግሊዝኛው ኪንገ ጀምስ ደግሞ ‹‹
the beginning of the creation of God:
›› በማለት ተርጉሞታል፡፡  ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ትርጉም በግሪኩ ቃል በቃል የይሖዋ ምስክሮች ከተጠቀሙት የግሪክ መጽሓፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ነው፡፡

(the) (Amen,) (the) μάρτυς(witness) (the) πιστὸς(faithful) καὶ(and) (the) (true,)   (the) ἀρχὴ(beginning) τῆς(of the) κτίσεως(creation) τοῦ(of the) (God,)

ከግሪኩ እንደምንረዳው ሁሉም ትርጉሞች በትክክል አልተረጎሙትም፡፡ በ1962 እና 1980ው ውስጥ ‹‹በእግዚአብሔርም›› የሚለው ውስጥ በግሪኩ ‹‹›› የሆነው ‹‹በ›› የሚለው ቅጥያ የለም፡፡ ይህ ‹‹በእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ ›› የሚለው ፣ እየሱስን ከፍጡር ውስጥ የሚመድብ የሚያወናብድ ትርጉም ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ደግሞ የበለ ግልጽ እንዲሆን ‹‹ከአምላክ ፍጥረት የመጀመሪያ›› ቢተረጉሙም ይህም ስህተት ነው፤ ምክንያም በግሪኩ ‹‹ἀπὸ(from) ›› የሆነው ‹‹ከ›› ቅጥያ የለም፡፡ በእንግሊዝኛውም ይሆዋ ምስክሮች ትርጉም ስህተት ነው ፣በግሪኩ ‹‹ ὑπ’(by) (hypo)›› የሆነው ‹‹ by›› የሚለው ቅጥያ የለም፡፡ ስለዚህ ከግሪኩም እንደምንመለከተው ‹‹የእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ/the beginning of the creation of God›› የሚለው ትክክል ነው፡፡ እናም ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል በምሳ 8፡22 ላይ ጥበብ ‹‹ የእግዚኣብሄር መንገድ (ፍጥረት) መጀመሪያ›› ከተባለችው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም እየሱስ እዚህ ጋር የተባለው የፍጥረታት ምንጭ ነው የተባለው፡፡ ‹‹ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።›› (ዮሐ 1፡1)


ጥብብ ከእግዚኣብሄር ተወለድኩ በማለት ዘላለማዊነትዋን እና የእግዚኣብሄር የባህሪዉ መሆንዋን ትናገራለች፡፡እየሱስ ክርስቶስ የእግዚኣብሄር ኣንድያ ልጅ /ኣንተ ልጄ ነህ መባሉ  ዘላለማዊነቱን እና የባህሪ ልጅነቱን ይናገራል፡፡ዘላለማዊ ካልሆነዉ ሰዉ የሚወለደዉ ዘላለማዊ አይደለም ነገር ግን ዘላለማዊ ከሆነዉ የሚወለደዉ ዘላለማዊ ነዉ፡፡ዘላለማዊ ልደት፡፡

ጥብብ የእግዚኣብሄር መንገድ/ስራ/ፍጥረት መጀመሪያ በመባል ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩት በእግዚኣብሄር ጥበብ መሆኑን ይገልጻል፡፡እየሱስ ክርስቶስም በራዕ 3፡14 የእግዚኣብሄር ፍጥረት መጀመሪያ በመባል ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩት በእርሱ መሆኑን ይገልጻል፡፡በተጨማሪም ዮሓ1፡3፣ቆላ 1፡15-16፡፡

ዋቢ ማስረጃዎች

1 , C:F.BurneyChrist as the Apex of Creation (Prov. viii 22, Col. i 15-18, Rev. iii 14.)” The Journal of Theological Studieshttps://digilander.libero.it/domingo7/Burney.pdf
2,ምሳ 8፡22 ቃል በቃል ትርጉም ፣ https://biblehub.com/interlinear/proverbs/8-22.htm

3,የይሖዋ ምስክሮች ግርክ ቃል በቃል ትርጉም ፣KIT https://wol.jw.org/en/wol/b/r1/lp-e/int/E/1985/66/3#s=14&study=discover



ስሉስ ቅዱስ የተመሰገነ ይሁን፡፡