Pages

Sunday, August 20, 2017

የይሆዋ ምሰክሮች በብዛት የሚጠቀሙት ጥቅሶች እና መልሶቻቸው


እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ (ምሳሌ 8፡22)

የይሖዋ ምስክሮች ምሳሌ 8፡22 ላይ ስለ ጥብብ ያለዉን የይብራይስጥ መጽሓፍ ቅዱስ ቃል “ይሖዋ የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ “ ብሎ ተርጉመዋል፡፡ እንዲሁም እየሱስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡24 ላይ “እያሱስ የእግዚኣብሄር ጥበብ” መባሉን ምክንያት በማድረግ ፤ምሳ 8፡22 እየሱስ መጀመሪያ ስለመፈጠሩ ያወራል ይላሉ፡፡እዚህ ላይ ሁሉም ክርስቲያን ማስተዋል የለበት እየሱስ በእግዚኣብሄር ጥበብ ተመሰለ እንጂ ምሳ8፡22 የሚያወራዉ ስለ አምላክ ጥብብ ነዉ፡፡በምሳ 7፡3 ላይ ጥበብ እህት ተብላለች፡፡እየሱስ ግን ተባዕታዊ ፆታ ነዉ፡፡

ይህ የይሖዋ ምስክሮች አድርጎ ፋጠረገኝ ብለዉ በሁለት ቃላት የተረጎሙት የይብራይስጥ ቃል ኣንድ ቃል ነዉ ይህም “ቀናኒ” የሚባል የይብራይስጥ ቃል ነዉ፡፡ይህ የመጀመሪያዉ የይሆዋ ምስከሮች ትርጉም ስህተት ነዉ፡፡



የፍጥረታት  ሁሉበኩር  (ቆላ 1፡15-17)
    የፍጥረታት በኩር ማለት ምን ማለት ነዉ?
      በቆላ 1፡15 ላይ እየሱስን የፍጥረታት ሁሉ በኩር ይለዋል፡፡ይህ ቆላ 1፡15 የይሆዋ ምስክሮች እንደሚሉት እየሱን የመጀመሪየዉ ፍጥረት ማለቱ ነዉን? በኩር ማለትስ ምን ማለት ነዉ?ይህ በኩር ተብሎ የተተረጎመዉ የግሪክ ቃል ፕሮቶኮስ( prototokos) የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛዉ ፈርስት ቦርን (Firstborn) ነዉ፡፡መጀመሪያ የተፈጠረ (First created) ለማለት የግሪኩ ቃል ፕሮቶክቲሲሰ (protoktisis)  ነዉ፡፡ታዲያ ይህ ቆላ 1፡15 እየሱስን መጀመሪያ የተፈጠረ ለማለት ከፈለገ ለምን ፕሮቶክቲሲሰ/ First created አላለም?




      የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ  (ራዕ 3፡14)

      ይህም የመጽሓፍ ቀዱስ ክፍል የይሖዋ ምስክሮች ክርስቶስ የመጀመሪያው የአምላክ ፍጡር ነው ለሚለው አስተምሮኣቸው የኒጠቀሙት ጥቅስ ነው፡፡



      የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ (ራዕ 3፡14)

      የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ  (ራዕ 3፡14)

      ይህም የመጽሓፍ ቀዱስ ክፍል የይሖዋ ምስክሮች ክርስቶስ የመጀመሪያው የአምላክ ፍጡር ነው ለሚለው አስተምሮኣቸው የኒጠቀሙት ጥቅስ ነው፡፡


      የደም መቀበል ህክምና (Blood transfusion) ክልከላ እና የይሖዋ ምስክሮች አላማ

      የይሖዋ ምስክሮች የደም መቀበል ህክምና (Blood transfusion) ክልከላ የአምላክን ትዕዛዝ ለማክበር ነው ወይስ ሌላ አላማ አለው? ይህን ጽሑፍ በጥሞና በማንበብ  ወገንን ከሞት ያድኑ፡፡

      የይሐዋ ምስክሮች እስከ 1927 ደም መብላትን የሚከለክለው የመጽሓፍ ቅዱስ ህግ ለክርስቲያኖች አይደለም ብለው ያስተምሩ ነር፡፡ በመጠበቂያ ግንብ መጽሄታቸው ኖቬምበር 15፣1892፣ገጽ 350-351 ላይ እና ኤፕሪል 15፣1909፣ገጽ 116-117 ላይ የደም መብላት ክልከላው ህግ ለአይሁዶች ብቻ እንደሆነ እና በአዲስኪዳን ያለውን ሀሳብ ክርስቲያኖች ለአይሁድ እና ለአረማዊያን መሰናከያ እንደይሆኑ እና ለቤክርስቲያን ሰላም ነበር ይላሉ፡፡

      በመጠበቂያ ግንብ መጽሄታቸው 1927 ዲሴምበር 15፣ገጽ 371 ላይ ነው ለመጀመሪ ጊዜ ነው የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት የቀድሞ ሐሳቡን በመቀያር አምላክ ከኖህ ጋር የገባው ቃልኪዳን ለሰው ዘር ሁሉ ይሆናል በማለት ለመጀመሪ ጊዜ የደም መብላት ክልከላውን ያደረጉት፡፡


      የደም መቀበል ህክምና (Blood transfusion) ክልከላ እና የይሖዋ ምስክሮች አላማ


      የይሖዋ ምስክሮች የደም መቀበል ህክምና (Blood transfusion) ክልከላ የአምላክን ትዕዛዝ ለማክበር ነው ወይስ ሌላ አላማ አለው? ይህን ጽሑፍ በጥሞና በማንበብ  ወገንን ከሞት ያድኑ፡፡

      የይሐዋ ምስክሮች እስከ 1927 ደም መብላትን የሚከለክለው የመጽሓፍ ቅዱስ ህግ ለክርስቲያኖች አይደለም ብለው ያስተምሩ ነር፡፡ በመጠበቂያ ግንብ መጽሄታቸው ኖቬምበር 15፣1892፣ገጽ 350-351 ላይ እና ኤፕሪል 15፣1909፣ገጽ 116-117 ላይ የደም መብላት ክልከላው ህግ ለአይሁዶች ብቻ እንደሆነ እና በአዲስኪዳን ያለውን ሀሳብ ክርስቲያኖች ለአይሁድ እና ለአረማዊያን መሰናከያ እንደይሆኑ እና ለቤክርስቲያን ሰላም ነበር ይላሉ፡፡

      በመጠበቂያ ግንብ መጽሄታቸው 1927 ዲሴምበር 15፣ገጽ 371 ላይ ነው ለመጀመሪ ጊዜ ነው የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት የቀድሞ ሐሳቡን በመቀያር አምላክ ከኖህ ጋር የገባው ቃልኪዳን ለሰው ዘር ሁሉ ይሆናል በማለት ለመጀመሪ ጊዜ የደም መብላት ክልከላውን ያደረጉት፡፡

      እስከ 1940ዎቹ መጀመሪያ ድርስ የይሖዋ ምሰክሮች ድርጅት የደምን በደም ሥር ለህክምና መውሰድ (Blood Transfusion) አይከለክልም ነበር፡፡1940ው Consolation መጽሓፋቸው ዲሴምበር 25፣ገጽ 19 ላይ ደም በመለገስ አንዲት ሴትን ያተረፈው ሐኪም ታሪክ በመልካም ያትታል፡፡

      እስከ 1945 ድረስ ይህ የደም ክልከላ የደምን በደም ሥር መውሰድን አያካትትም ነበር (መጠበቂያ ግንብ፣ሜይ 15፣1995፣ገጽ 23)፡፡ ነገር ግን ከ1945 ጀምሮ እስከ 1961 በተለያዩ ጽሁፎቻቸው (Watchtower 1945 Jul 1 p.201፣Watchtower 1950 May 1 p.143፣Awake! 1954 Jan 8 p.24፣Watchtower 1959 Oct 15 p.640) ደምን ለህክምና በደም ሥር መውሰድ ስህተት እና የአምላክን ትዕዛዝ መሻር መሆኑን ሲገልጹ ነበር፡፡

      በመጠበቂያ ግንብ መጽሄታቸው ኦገስት 1፣1958 ገጽ 478 ላይ የአንዲትን በሆስፒታል እያለች ደም ስለ ወሰደች ሴት ታሪክ ያነሳል፡፡ ሴትዬዋ ደም በመውሰድዋ ስህተት እንደሰራች ይገልጽና ድርጅታቸው የዚህን አይነት ሰው ከድርጅቱ እንድናስወግድ አዞን አያውቅም ይላል፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት በመጽሓፍ ቅዱስ ትምህርት የሚያምን ከሆነ የድርጅቱ ትዕዛዝ ለምን አስፈለገ ? በተጨማሪም ሴትዬዋ ለሰራችው ጥፋት ፍርዱን ለይሖዋ እንተዋለን ይላል፡፡ ስለዚህ ቢያንስ እስከ 1958 ድረስ ይህ ጥፋት ከድርጅቱ የሚያስወግድ ያልበረ እና ለጥፋቱም ፍርዱ የይሖዋ እንደሆነ እንረዳለን፡፡

      የ1961ዱ Jehovah's Witnesses - Proclaimers of God's Kingdom የሚለው መጽሃፋቸው ገጽ 183-184 ላይ ደግሞ ደምን በደም ሥራቸው ለህክምና የሚወስዱትን ድርጅቱ የጥፋት ውሳኔ (ፍርድ) እንደሚወስንባቸው እና ከድርጅቱ እንደሚያስወግዳቸው መሆኑን ይገልጻል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በኋላ ድርጅቱ ፍርዱ የይሖዋ ነው ያለውን ፍርድ ለራሴ አደረገ፡፡

      መጽሓፍ ቅዱስ ስለ ደም ክልከላ ሲናገር ሁል ጊዜ ደምን ስለ መብላት ፤ደምን በምግብነት ስለመጠቀም ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮችም የሚጠቅሱኣቸው የጽሓፍ ቅዱስ ክፍሎች ሁሉም (1ኛ ሳሙ 14፡31-35፤ት.ሕዝ 33፡25፤ዘ.ዳግ 12፡13-27፤ዘ.ሌዋ 7፡14-37፣ዘ.ዳግ 15፡19-23)  ደምን በምግብነት ስለመውሰድ ወይም ደምን ስለመብላት ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ድርጅተም ይህን ሐቅ በግልጽ በመጠበቂ ግንብ መጽሄታቸው ሴፕቴምበር 15፣1958፣ገጽ 575 ላይ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ለው የደም ክልከላ ሁል ጊዜ ደምን በምግብነት ስለ መውሰድ መሆኑን እንዲህ ይገልጻል፡፡

      Each time the prohibition of blood is mentioned in the Scriptures it is in connection with taking it as food, and so it is as a nutrient that we are concerned with in its being forbidden. The Watchtower, September 15, 1958 ,page 575

      ታዲያ መጽሃፍ ቅዱስ ደምን የሚከለክለው የአምላክ ቃል ደምን ስለ መብላት ከሆነ እና ደምን በደም ሥር ስለመውሰድ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ካሌለ የይሖዋ ምስክሮች ለምን ደምን ለህክምና በደም ሥር መውሰድን ይከለክላሉ? የአምላክን ቃል ለመጠበቅ ነው ወይስ ለሌላ አላማ?

      የይሖዋ ምስክሮች በ1990 እ.ኤ በሳተሙት How Can Blood Save Your Life? በሚለው ብሮሸራቸው ሙሉ በሙሉ ስለ ደም በደም ስር መውሰድ (Blood Transfusion) ክልከላቸው ያትታሉ፡፡ ከዚህ ብሮሸራቸው እና ከሌሎች ጽሁፎቻቸው እንደምንረዳው፣የይሖዋ ምስክሮች ይሄንን ክልከላቸውን ለማጠነካር የተለያዩ ምክንያቶችን ያቀርባለ፡፡ ከእናዚህም ውስጥ መጽሓፍ ቅዱስ፣ደም መብላት እና መውሰድ አንድ ናቸው፣የአምላክ ቃል ኪዳን፣የተከበረውን አምላክ የሰጠንን ህይወት በደም እንዲቀጥል ማድርግ ተገቢ አይደለም፣የደም ህክምና ለብዙ በሽታዎች ያጋልጣል እና ከደም ራቁ ይላል የሚሉት ይገኙበታል፡፡

      መጽሓፍ ቅዱስ ሰው ክቡር እንደሆነ ይነግረናል፡፡ አምላክ የሰውን ልጅ እንስሳ ሲል አናይም፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች የይሖዋ ምስክሮችን ጨምሮ ሰውን ከእንስሳ እኬል በማድረግ ያስተምራሉ፡፡ መጽሓፍ ቅዱስም ይህን ሰውን እንደ እንስሳ የማየቱን ነግር ፈተና በማለት ስህተት መሆኑን ከመናገሩም በላይ የሰውን እና የእንስሳትን ልዩነት በሰፊው ይገልጻል፡፡

      12 ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። መዝ 49፡12

      የአምላክም አላማ ማንም ሰው በህይወት ቆይቶ ለንስሃ እንዲበቃ ነው እንጂ እንዲሞት አይደለም፡፡

      ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። 2ኛ ጴጥ 3፡9

      የጌታችን የእየሱስንም ተግባር ስናይ ይሄን ያሳያል፡፡ ክርስቶስ የሞቱትን ሰው ያስነሳው አምላክ ሰው እንዲሞት ስለማይፈልግ ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የሰው ሞት የአምላክ አላማ አይደለም፡፡ ከዚህም ውጪ ክርስቶስ በአይሁድ ህግ ንጹህ ያልሆነችው ደም ይፈሳት የነበረችው ሴት ልብሱን ስትነካ፣ንጹህ አይደለሽም ዞር በይ ኣላላትም ይልቁንም የአምላክ አላማ የሆነውን ፈውስን ሰጣት፡፡ በሰንበት ማደኑንም ማስተዋል  አለብን፡፡ የሰውን ልጅ ለማደን ህግ አልከለክለውም፡፡ ሁሌም በደዌ ለተመቱት እና ለሞቱት ሲደርስላቸው እንመለከታለን፡፡ ምክንያቱም የአምላክ አላማ የሰው ልጅ እንዲሞት አይደለም፡፡

      የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፍ ቅዱስ ክቡር ስለሚለው የሰው ህይወት How Can Blood Save Your Life? በሚለው ብሮሸራቸው, 1990ገጽ ላይ እንዲህ ጽፈዋል፡፡

                ህይወትን እንደ ፈጣሪ ስጦታ የሚያከብሩኣት ፣ደምን በመውሰድ አያቆዩኣትም፡፡

      ከላይ እንደያነው ክርስቶስ ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት የአይሁድን ህግ እና ልማድ እንኳን ሳይገድበው እንዳይሞት ሲያደርግ ነበር፡፡ የአምላክ አላማ ሁሌም ሰው እንዳይሞት ነበር፡፡ የይሖዋ ምስክሮች የሰው ህይወት ክቡር ነው ቢሉትም ፣መጽሓፍ ቅዱስሳዊ ያልሆነውን ህጋቸውን ለመጠበቅ ሲሉ፣ መሞት አለበት ይላሉ፡፡

      ሥለደም መጽሓፍ ቅዱስ፡-

       መጽሓፍ ቅዱስን ስናጠና ሁል ጊዜ የሚያዘን የእንስሳትን ደም በምግብ መልክ እንዳንወስድ ነው፡፡ ሁሉም የይሖዋ ምስክሮች የሚጠቅሱኣቸው ክፍሎች በሙሉ ደምን እንደ ምግብነት ስለ መውሰድ ከመሆኑም በላይ እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለ እንስሳት መስዋዕትነት ያወራሉ፡፡
      የደም በምግብነት የመከልከሉ ነገር በመጽሃፍ ቅዱስ በምክንያት የተከለከለ ነገር ነው፡፡ መጽሓፍ ቅዱስ ደምን በምግነት አትጠቀሙ ያለበትን ምክንያት እንዲህ ይነግረናል፡፡ እንዲውም ከአይሁድ ድርገጾች ካየሁት መረጃ፣ አምላክ ምክንያት የሰጠበት ብቸኛው ክልከላ ነው፡

      11 የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት።12 ስለዚህ የእስራኤልን ልጆች፦ ከእናንተ ማንም ደምን አይበላም፥ በመካከላችሁም ከሚኖሩ እንግዶች ማንም ደምን አይበላም አልሁ።ዘሌ 17፡10-15

      ከላይ እንደምንረዳው፣ አምላክ ደምን ለምግብነት የከለከለው ደም ለአምላክ በመስዋዕትነት ስለሚቀርብ ነው፡፡ የእንስሳት ህይወታችው በደማቸው ስለሆነ ነው፡፡ታዲያ አምላክ ሰው በስዋዕትነት እንዲቀርብለት ይፈልጋል ? መጽሓፍ ቅዱስን ስናጠና አንድም ቦታ ሰው ለአምልከ ሲሰዋ አንመለከትም፡፡ የአብርሓምን እና የይስሃቅን ታሪክ ማየት ይቻላል (ዘፍ 22፡2-13)፡፡ አምላክ በግ በፋንታው እንዳዘጋጀለት፡፡

      በተመሳሳይ ምክንያት መጽሓፍ ቅዱስ በብሉይ ጊዜ ስብ መብላትን ይከለክል ነበር፡፡

      22፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። 23፤ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው። የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ ከቶ አትብሉ። 24፤ የሞተውን ስብ፥ አውሬ የሰበረውንም ስብ ለሌላ ተግባር አድርጉት፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም አትብሉ፤  25፤ ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሁሉ፥ ያ የበላ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋልና። ዘሌ 7፡22-25

       መስዋዕት አቅራቢ ሰው ሲሆን መስዋዕት የሚቀርቡት ደግሞ  እንስሳት እና አዕዋፋት ናቸው፡፡ነገርግን የተለያዩ ባዕድ አምላኪዎች ሰውን ለአማልክቶቻቸው እንደሚሰው ግልጽ ነው፡፡ በሌላ መንግድ ለአምላካቸው ሲሉ የሰውን ህይወት የሚያጠፉ እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ የህም መጀመሪያውኑ ሞትን ወደ ሰው ላማጣው ለሰይጣን መሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ሰይጣን ሁል ጊዜም በአምላክ ተቃራኒ የሰው ልጅ እንዲሞት ይፈልጋል፡፡

      እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሓ 8፡44

      አምላክ እንኳን ህይወታችን ሳያልፍ ሰው መርዳት እየቻልን ሰው እየሞተ እንድናይ ይቅርና አንዳችን ለሌላችን ህይወታችንን እስከ ማሳለፍ እንድንወደድ ይመክረናል፡፡

      ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም ፡፡ዮሓ 15፡13

      ደም መብላትና ደም መውሰድ፡-

      ከላይ እንዳየነው መጽሓፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ስለ ደም ያለው ክልከላ፣ደምን እንደ ምግብነት ስለመውሰድ ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮችም ይሄን ያምናሉ፡፡ ታዲያ ይህ ከሆነ ለምን ደምን በደም ስር መውሰድን ይከለክላሉ? የይሖዋ ምስክሮች ይህን ክልከላቸውን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ የተጠቀሙት ዘዴ ደም በደም ስር መውሰድ እና ደም መብላት አንድ ነው የሚል ነው፡፡ ይህ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ስለሆነ ለዚህ ማስረጃነት የተጠቀሙት ጥናታዊ ጽሁፍ ከ300 አመታት በፊት (Thomas Bartholin (1616-80)) ገና ስለ ደም በግምት በሚወራበት ጊዜ የተጻፈን እና ምንም የለቦራቶሪ መረጋገጫ ይልተደረገበት ጽሁፍ ነው (How Can Blood Save Your Life? በሚለው ብሮሸራቸው, 1990ገጽ 6)፡፡ ተመለክቱ፣ ለምን በዘመናችን ያሉ ጥልቅ ጥናታዊ ጽሁፎች እያሉ ከ300 አመታት በፊት የነበረውን ጽሁፍ ተጠቀሙ?

      በእርግጥ ደም በደም ስር መውሰድ እና ደም በአፍ መብላት አንድ ነው ማለት ማንም ተራ ሰው የሚለየው ሐሰት ነው፡፡ ነገር ግን የይሖዋ ምስክሮች ይህን አስተሳሳባቸውን በሰዎች አዕምሮ ለመጫን ወቅታዊ የሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎችን ከመጠቀም ይልቅ የተለያዩ ምሳሌዎችን መውሰድ መርጠዋል፡፡ ከእናዚህም ጉሉኮስን ወይም አልኮልን በደም ስር መውሰድ እና በአፍ መውሰድ አንድ ነው፤እናም ደምም እንዲሁ ነው የሚል ነው (መጠበቂግንብ ጁሌ 1፣1951፣ገጽ 414፤ መመራመር Reasoning From the Scriptures, Watch Tower Bible & Tract Society, 1989, page 73.)፡፡ ይህ ሰዎችን ለአላማቸው ለማጃጀል የፈጠሩት የማይመሳሰል ማመሳሰል ነው፡፡ የዚህ ምሳሌ ትልቁ ስህተት ደም ህይት ያለው መሆኑ እና አልኮል እና ጉሉኮስ ህይወት የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ ደምን በአፍ ስንወስድ ወይመም ስንበላው ይሞታል፣በድም ሥር ስንወስደው ግን አይትም፡፡ ደምን በአፍ ስንወስድ ደሙ እንደምግብነት ሲያገልግል በደም ሥር ስንወስድ ደግሞ እንደምግብነት አያገለግልም፣ በህይወት ይቀጥላል፡፡ ይህ ደግሞ ለጉሉኮስ እና ነአልኮል አይሰራም፤ህይወት የሌላቸው ነገሮች ናቸው፡፡

      ከደም ራቁ (የሓዋ ሥራ 15፡28-29)፡-

      የይሖዋ ምስክሮች ለዚህ ደም ክልከላቸው የሚጠቅሱት የመጽሓፍ ቅዱስ ቃል ነው፡፡ ከደም ራቁ ይላል፡፡ ይህ ምን ማለት ነው ? ደምን አትንኩ ማለት ነው?  ደምን አትዩ ማለት ነው? ከደም በ2፣በ3 ወይም በ10 ኪሎ ሜትር ራቁ ማለት ነው? ወይስ ደምን በደም ሥር አትውሰዱ ማለት ነው? የዚህ መልስ በሁለት መንግድ ሊሆን ይችላል፡፡ ከመጽሓፍ ቅዱስ አንጻር ወይም ከግል ፍላጎት አንጻር፡፡ ከመጽሓፍ ቅዱ እንጻር ከሆነ መልሱ አንድ ነው፡፡ ይህም ደምን እንደ ምግብነት መውሰድ ነው፣ምክንያቱም ደም ለመስዋዕትነት ያገለግላል (1ኛ ሳሙ 14፡31-35፤ት.ሕዝ 33፡25፤ዘ.ዳግ 12፡13-27፤ዘ.ሌዋ 7፡14-37፣ዘ.ዳግ 15፡19-23) ፡፡ በግል ፍላጎት ከሆነ እንደ አላማችን ይለያያል፡፡ ሰው እንዲሞት ከሆነ ደምን በደም ሥር መከልክ ትክክል ነው፡፡ መክንያቱም ደም የሚፈልግ ሰው ደም ካላገኘ መሞቱ ግልጽ ስለሆነ ምንም ማምለጫ የለውም፡፡ ደምን መንከት የሚጸየፍ ደግሞ ደም መንካት ነው የተከለከለው ሊል ይችላል፡፡ ወዘተ፡፡ ታዲያ በራስ ፍላጎት እንኳን ብዙ አማራጮች እያሉ የይሖዋ ምስክሮች ለምን ደም በደም ሥር መውሰድን መረጡ?

      ለመሆኑ የይሖዋ ምስክሮች ከደም እየራቁ ነው?የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፍ ቅዱስ ደምን በደም ሥር መውሰድን ይከለክላል ብለው አንድም የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል መጥቀስ አይችሉም፡፡ ነገር ግን የነጋገርኳቸው የይሖዋ ምስክሮች ይህ ክልከላቸው መጽሓፍ ቅዱስ እንዳለ ይነግሩኝና ቀጥረውኝ ይጠፋል፡፡ እውነታው ስላሌለ ነው፡፡

      በመጽሓፍ ቅዱስ የተከለከለው ደም መብላት ነው፡፡ የዛሬዎቹም አይሁዶች ይህን የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል አክርረው የሚያከብሩት ነው፡፡ከማክረራቸው የተነሳ የእንስሳትን ሥጋ ሲበሉ ደሙ ሙሉ በሙሉ ለማውጣት ስጋውን መጨው በመዘፍዘፍ እና በሌሎች ዘዴዎች ይተቀማሉ፡፡ በተቻላቸው መጠን ሥጋው ድም እንዳይኖረው እጅግ ይጥራሉ፡፡ ነገርግን ደምን በደም ሥር መውሰድን አይከለክሉም፡፡

      የይሖዋ ምስክሮች ግን ይህን በመጽሓፍ ቅዱስ በግልጽ የታዘዘውን ትዕዛዝ ከማክርር ይልቅ በመጽሓፍ ቅዱስ የሌለውን እና የሰው ልጅን የሚገድለውን ያከራሉ፡፡ እስቲ የይሖዋ ምስክሮች የሚበሉትን ሥጋ ከሚቀቅሉት  ወይም በጥሬ ከሚበሉት ትንሽ ወስደው በውሃ ዘፍዝፈው ምን ያህል ደም እንዳለው ይመልከቱ፡፡ የሚበሉት ጉበት ውስጥ ያለውን ደም ይመለክቱ፡፡ ታዲያ የዚህ ድርጅት አላማ የአምላክን ትዕዛዝ ለማክበር ከደም መራቅ ነው ወይስ ሌላ?

      ከዚህም በተጨማሪ የይሖዋ ምስክሮች ይህን ክልከላ በጀመሩበት ጊዜ ከማክረራቸው የተነሳ ከደም ቅንጣቶች የተሰሩ ነድሃኒቶችን እንዳይወስዱ ይከለክል ነበር (መጠበቂያ ግንብ፣ኖቬምበር 1፣1961፣ገጽ 669) ፡፡ የሰውም ደም መጠራቀም የለበትም ወደመሬት መፍሰስ አለበት ይሉ ነበር (ንቁ!፣ጁን 22፣1982፣ገጽ 25)፡፡ አምላክ ስለ እንስሳት ደም መፍሰስ የተናገረው ለመስዋዕትነት ስለሆነ ነው፡፡ የሰውን ደም ስለማፍሰስ ግን እንዲህ ይላል፡፡
      የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና። ዘፍ 9፡6
      አሁን ያለው የይሖዋ ምስክሮች አቋም ደግም እንዲህ ነው?

      የይሖዋ ምስክሮች አሁን ያለው የዚህ አስተምሮ (ክልከላ ) አቋም በመጠበቂያ ግንብ (2000) ፣ ጁን 15 ገጽ  29-30 መጽሔታቸው ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መጽሄታቸው ላይ  ‹‹የይሖዋ ምሥክሮች ማንኛውንም የደም ተዋጽኦ ለሕክምና ይወስዳሉን? ›› ተብሎ ከአንባቢያን ለቀረበው ጥያቄ  ‹‹ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መሠረታዊ መልስ የይሖዋ ምሥክሮች ደም አይወስዱም የሚል ነው።›› ብለው ይመልሳሉ፡፡ ከዚያ ደምን በ4 ዋና ዋና ክፍሎች ፣ (1) ቀይ የደም ሕዋስ፤ (2) ነጭ የደም ሕዋስ፤ (3) አርጊ ሕዋስ ደም (platelets) (4) ፕላዝማ (እዥፈሳሹ ክፍል ይከፍላሉ፡፡ከዚያም  ‹‹ የይሖዋ ምሥክሮች ሙሉ ደምም ሆነ ከአራቱ ዋና ዋና ክፍሎች ውስጥ አንዱን መውሰድ የአምላክን ሕግ እንደሚያስጥስ ያምናሉ። ›› ይላሉ፡፡ ስለዚህ ከእናዚህ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ መውሰድን ይከለክላሉ ማለት ነው፡፡  ይሄው መጽሓፋቸው ከእነዚህ ዋና ዋና ክፍል ፋዮች የሚገኘውን አነስተኛ ክፍልፋይ ደግሞ ‹‹ደቃቅ ክፍልፋዮች›› ይለዋል፡፡ ከ4ቱ ዋና ዋና ክፍሎች የሚገኙትን ደቃቅ ክልፋችን በጥቂቱ እንዲህ ዘርዝረዋል፤በርካታ ሆርሞኖችን፣ ኢካርቦናማ ጨውን (inorganic salt) ኤንዛይሞችንና ንጥረ ምግቦችም፣አልቡሚን፣ ደም እንዲረጋ የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮችንና በሽታ ተከላካይ ፀረ እንግዳ አካላትን የመሳሰሉ ፕሮቲኖችን፣ፋክተር 8፣ጋማ ግሎቡሊን ፡፡ ከዚህም በላይ ድርጅቱ ቀድሞ የተከለከለውን ከደም ግብኣት የተሰሩትን መድሓኒቶችን መውሰድ እንደሚቻል ይገልጻል፡፡

      እነዚህን ደቃቅ ክፍልፋዮችን ስለመውሰድ እንዲህ ይገልጻል፡፡
      ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ [ስለ እነዚህ ደቃቅ ክፍልፋዮች] ዝርዝር መመሪያ ስለማይሰጥ እያንዳንዱ ክርስቲያን በአምላክ ፊት ማስተዋል የተሞላበት የራሱን ውሳኔ ማድረግ አለበት።›› በማለት የክልከላ ግዴታ እንዳሌለ ወይም እንደሚፈቀድ ይገልጻል፡፡

      እዚህ ላይ ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ የይሖዋ ምስስክሮች መጽሓፍ ቅዱስ ስለ ደቃቅ ክፍልፋዮች ዝርዝር መመሪያ የለውም፣እናም ክልከላ የለም ይላሉ፡፡ ታዲያ መጽሓፍ ቅዱስ ስለ ዋና ዋናዎቹ ዝርዝር መመሪያ ሰጥቶኣል? ስለ ቀይ የደም ህዋስ፣ስለ ነጭ የደም ህዋስ ስለ ላትሌት መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የቱ ጋር ነው በዝርዝር የሚገኘው? ሁላችንም የይሖዋ ምስክሮችን ይህን ልንጠይቅ ይገባል፡፡ እንኳን ስለ ዋና ዋናዎቹ ክፍልፋዮች ይቅርና ስለ ደምን በደም ሥር መውሰድ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም መመሪያ የለም፡፡ ስለዚህ ምንም እንከዋን ድርጅቱ 4ቱን ዋና ዋና ክፍልፋዮች ቢከለክልም፣ለደቃቅ ክፍልፋዮች ለመፍቀድ የሰጠው ምክንያት ለዋና ዋናዎቹም ይሰራል፡፡ ይህ የሚያሳየው ድርጁት ምን ያህል ግራ እንደ ተጋባ ነው፡፡ ወይም ደግሞ ማኞቹን ግራ እንደሚያጋባ ነው፡፡

      በሌላ መልክ ድርጅቱ እናዚህን ደቃቅ ክፍልፋዮች መፍቀድ ማለት፣ከደም ራቁ ለሚለው ለራሱ አስተምሮ እንዳልተገዛ ነው፡፡ ከሥጋው ጾሜኛ ነኝ ከመረቁ ስጡኝ ኣለ ፡፡

      ይህን የይሖዋ ምስክሮች ጽሁፍ ስናስተውል፣ምንም እንኳን 4ቱን ዋና ዋናዎቹን በግልጽ አነጋገር ቢከለክልም፤ ለደቃቅ ክፍልካዮች የሰጠው ምክንያት ግን ለዋና ዋናዎቹም ይሰራል፡፡ ታዲያ አንድ የይሖዋ ምስክሮ በመጽሓፍ ቅዱስ በግልጽ መመሪያ ስላልተሰጠ ብሎ ዋና ዋናዎቹን ቢወስድ ምን ስህተት አለበትለመሆኑ ይሄን የጠየቀ የይሖዋ ምስክር አለ?
      በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱ የአስተምሮውን ለውጥ የሚያሳውቀው በአንቢ ጥያቄ መሆኑ ያስገርማል፡፡ ይህም አንድም ድርጅቱ ለአማኞቹ በራሱ እንደማያስብ ሁለትም ደግሞ  ለአንባቢያን እርካታ ብቻ እንደሚያደርግ ያሳያል፡፡ ሌላው ድግሞ ምናልባትም ድርጅቱ ጥያቄውን ራሱ ፈጥሮ ነው፡፡

      ከደም ጋር የሚመጡ በሽታዎች፡-

      የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት ከደም ልገሳ እና ቅበላ ጋር በተያየዘ የሚመጡትን መሽታዎች እንደ ኤድስ፣የጉበት በሽታ (ሄፕታይተስ) የመሳሰሉትን በመጥቀስ ደም አለመቀበል እንደሚሻል ከመግለጹም በላይ  እንደመስፈራሪያም ይጠቀመዋል፡፡ ማምሻም እድሜ ናት ይላል ያገሬ ሰው፡፡ አንድ ምሳሌ እናንሳ፡፡ አንድ ሰው ደም ወስዶ ከህመሙ  ተፈውሶ ግን በኤድስ ተያዘ እንበል፣ከዚያም በቀረው ጊዜ ንስሃ ገባ፡፡ ጥቅሙን እንመልከት፡፡ የአምላክም አላማ ሰዎች እድሜ ኖሮኣቸው ንስሓ እንዲገቡ ነው፡፡

      ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። 2ኛ ጴጥ 3፡9

      ይህ ዘላለማዊ ህይወት ይቅርና በሥጋዊ ህይወት እንኳን ምን የህል የቀረው ጊዜ ነገሮችን እንደሚያስተካክልበት እናስተውል፡፡ እናም ይህ የይሖዋ ምስክሮች አስተሳሰብ እድሜውን እናሳጥር የሚል ይመስላል፡፡ ሌላው ደግሞ የደም ቅበላ በጥንቃቄ ተመርምሮ ስለሚደረግ የዚህ ያህል አሳሳቢ አይደለም፡፡ የይሖዋ ምስክሮች በሚፈቅዱት የአካል (ጉበት፣ኩላሊት..) ነቅሎ ተከላ ውስጥም ይህ በእነዚህ በሽታ የመያዝሥጋት ኣለ፡፡ የእንደዚህ አይነት ችግር እንኳን ቢፈጠር ከብዙ ሰው ጥቂት ላይ ነው፡፡ የህክምናውም አላማ ሰዎችን ለማትረፍ ነው እንጂ በሌላ በሽታ መስያዝ አይደለም፡፡ በማንኛውም ህክምና ሁሉም ከምንም ችግር የጸዳ ህክምና ያገኛል ማለት አይቻልም፡፡

      በእርግጥ የይሖዋ ምስክሮችን ድርጅት ታሪክ ስንመለከት፣ይህ የደም ክልከላ ትምህርታቸው የሰው ልጆች በገዛ ፍቃዳቸው ራሳቸውን እንዲያጠፉ የማድርግ የቀድሞው አላማቸው ቀጣይ ነው፡፡ ብዙ አረማዊ እምነቶች ደግሞ ሰውን በመግደል መስዋዕት በማድርግ ይታወቃሉ፡፡

      የይሖዋ ምስክሮች ሰዎች በቀላሉ ራሳቸውን እንዲጢፉ ዛሬ ንቁ በሚባለው እና በወቅቱ Golden Age  በሚባለው መጽሄታቸው በ1926 ፣ኤፕሪል 7፣ገጽ 438 እንዲህ መክረው ነበር፡፡

      "If any overzealous doctor condemns your tonsils go and commit suicide with a case-knife. It's cheaper and less painful."  1926 Apr 7 p.438
      “ኣንድ ዶክተር ቶንሲልህን (ከጉሮሮ ግራና ቀኝ ያለ የአካል ቁራጭ፣ አንቃር) ቢነቅፍ ፣ሂድና ራስህን በሴንጢ አጠፋ፡፡ ህመሙ ከነቀፋዉ ይቀላል፡፡” Golden Age 1926 Apr 7 p.438

      ይህ ሰዎች ትዕግስት አጥተው ያለ ምንም መጽሓፍ ቅዱስ ማስረጃ በቀላሉ ራሳቸውን እንዲያጠፉ ያደርግ የነበረው ድርጅት ይህን ሐሳቡን ስለመተው እንኳን ምንም ያለው ነገር ዛሬም የለም፡፡
      ይህ ድርጅት ደም ውጪ ሌሎች ህክምናዎችንም በመከልከል የሰው ልጅ በገዛ ፍቃዱ ራሱን እንዲያጠፋ ማድረጉን ከታሪኩ እንረዳላን፡፡

      ህክምና ሰይጣናዊ ነው፡-

      ይህ ድርጅት ህክምና ዲያቢሎሳዊ ነው ከማለቱም በላይ በሽተኛውን ከመፈወስ ይልቅ ይጎደዋል በማለት ያስተምሩ ነበር፡፡ The Golden Age, August 5, 1931, p. 751-754 :: ታዲያ የተኛው ታማኝ አማኝ ነው ይህን እያወቀ ህክምና የሚወስደው፡፡

      ክትባት፡-

      ከ1921 እስከ 1965 ድረስ የይሖዋ ምስክሮች ክትባትን ሰይጣናዊ፤ጭካኔኣዊ፣ከምንም በሽታ የማይከላከል፣ወደፊትም የማይከላከል፣አምላክ ከኖህ ጋር የገባውን ቃልኪዳን መጻረር፣የእግዚኣብሄርን ህግ የሚጻረር፣ደምን የሚያቆሽሽ፣በማለት ዜጎች መባታቸውን ተጠቅመው እስከወዲያኘው እንዲያስወግዱት ከመጠየቃቸውም በላይ ክትባት ወንጀል ነው ይሉ ነበር፡፡( ዘጎልደን ኤጅ (Golden Age)፣1921፣  ጃኑዋሪ 16፣1924 ገጽ 250፣ዘጎልደን ኤጅ (Golden Age) 1929  ሜይ 1 1929 ገጽ 502፣ዘጎልደን ኤጅ (Golden Age) 1929  ኖቬምበር 13 1929 ገጽ 106-107፣ጎልደን ኤጅ (Golden Age)፣1931 ፌብሩዋሪ 4፣ገጽ 293፣የመጠበቂ ግንብ 1952፣ዲኤምበር 15፣ገጽ 764፣)፡፡ በተላይ ጎልደን ኤጅ መጽሄታቸው 1931 ፌብሩዋሪ 4፣ክትባታ ክርስቲያናዊ ላለመሆኑ ለማስረዳት ስዕሎችንም በመጠቀም  10 ገጾችን ተጠቅሞኣል፡፡ በኋላ ይህን ሐሳባቸውን በመቀየር በንቁ! መጽሄታቸው፣ኦገስት 22፣1965፣ገጽ 20 ላይ ክትባት ብዙ በሽታዎችን እንደቀነሰ ጽፈዋል፡፡ ከዚያም የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት ለአማኞቹ ክትባትን የማደረግ ሙሉ ነጻነት ሰጥቶኣቸዋል (ንቁ!፣ኦገስት፣22፣1965፣ገጽ 17-21)፡፡ ታዲያ በእነዚህ 30/40 አመታት ገደማ ስንቶቹ በከንቱ ህይዋታቸውን እንዳጡ አለያም አካል ጉዳተኛ እንደሆኑ ማስተዋል አለብን፡፡ በውኑ ይህ መስዋዕትነት ለአምላክ ነው ወይስ ለሰይጣን;

      የአካል ነቅሉ ተከላ ህክምኛ (Organ transplantation)፡-

      የአካል ነቅሎ ተከላ ለተማመሚ የሌላን ሰው አካል (ኩላሊት፣ልብ ወዘተ) መስጠት ወይም መትከል ነው፡፡ የይሖዋ ምስክሮች ይህን የአካል ነቅሎ ተካለ () ህክምና ሰው በላነት ነው በማለት ከ1967 እስከ 1980 ይከለክሉ ነበር (Watchtower 1967 Nov 15 pp.702-704፣ Watchtower 1980 Mar 15 p.31)፡፡ ከክልከላው በፊት ድርጅቱ ይህን ህክምና ጠቃሚ እና በጣም ጥሩ በማለት አድንቆታል (Awake! 1949 Dec 22 p.20) ፡፡ Watchtower 1961 Aug 1 p.480  ላይም የህን የሚከለክል ምንም የመጽሓፍ ቅዱስ ህግ ያለ አይመስለንም በማለት ህክናውን መቀበል ያለመቀበል የግል ምርጫ ነው ብለው እንደማይከለክሉ ገልጸው ነበር፡፡
      የይሖዋ ምስክሮች ይህን ህይወትን አድን ህክምና ለመከልከል ግን ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ በ1967ቱ መጠበቂያ ግንብ መጽሄታቸው ኖቬምበር 15 ፣ገጽ 702-704 ላይ የአካል ነቅሎ ተከላ ሰው በላነት ነው በማለት እንዲሁም አምላክ ሥጋ መብላትን በፈቀደ ጊዜ የሰውን ሥጋ መብላት አልፈቀደም በማለት ከለከሉ፡፡ ከዚህም በተማሪ የአካል ነቅሎ ተከላ የመንነት ነቅሎ ተከላ ነው በማለት ከሌባ ኩላሊት የወሰደ ሰው ሌባ ይሆናል በማለት ነበር (መጠበቂያ ግንብ 1975፣ሴብቴምበር 1፣ገጽ519)፡፡አካል ነቅሎ ተከላ ሰው በላነት ነው ብሎ ማሰብ መቼም ሊያስገርም ይችላል፡፡ ድርጅቱም በመጠበቂያ ግንብ መጽሄታቸው፣1980፣ማርች 15፣ገጽ 31 ላይ ‹‹አካሉን ሰጪው ስለማይሞት፣የአካል ነቅሎ ተከላ ህክምና ሰው በላነት አይደለም ››በማለት የአካል ነቅሎ ተከላን ፈቀደ፡፡  በደም ህክምናስ ደም ሰጪው ይሞታል፡፡ በተለይ የይሖዋ ምስክሮች ደም ፈሳሽ ከመሆኑም ውጪ እንደ ማንኛውም የሰው አካል (ጉበት፣ኩላሊት…) ነው ብለው ነበር፡፡ ስለዚህ የደም መስጠት እና መቀበል ከአካል ነቅሎ ተከላ ጋር እንድ ነው ማለት ነው፡፡ በእርርግጥ ይህ ሳይንሳዊ ሀቅ ነው፡፡ አሁንም በክልከላው ወቅት ደመከልብ ሆነው ያለቁትን እናስብ፡፡

      በአጠቃላይ የዛሬው የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት የደም ህክምና ክልከላ ምንም መጽሓፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው እና በቀጥታ ራሳችሁን አጥፉ ከሚለው ትዕዛዙ በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜ ሰዎች ህክምናን በመጥፎ እንዲያዩ እና በገዛ ፍቃዳቸው ራሳቸውን እንዲያጠፉ የማድረጉ ቀጣይ አጀንዳ ነው፡፡ ታዲያ ይህ የአምላክ አላማ ነው?
      እንዲያውም የይሖዋ ምስክሮችን ድርጅት ታሪክ ስንመለከት ከባዕድ አምልኮ ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዳለው ነው፡፡ ይህ ድርጅት የአረማዊውን የግብጽ ፈርኦን የፒራሚድ ሐውልት መጽሓፍ ቅዱስ ነው ይል የነበረ ድርጅት ነው (በጽዮን መጠበቂያ ግንብ 1881፣ሜይ ፣ገጽ 224 ላይ እና በጽዮን መጠበቂያ ግንብ 1911፣ማርች 15 ፣ገጽ 94-95 ላይ)፡፡ ሰን ዲስክ የሚባለውን ባለ ክንፉ የጸሓይ ክበብ የተለያዩ አረማዊ እምነቶች (ፍሪ ማሶናሪዎችን ጨምሮ) እና የግብዕ አረማዊ እምነት መሰረት የሆነውን ድርጅቱም ራሱ የባዕድ አምልኮ አርማ ነው ብሎ በኋለ የገለጸውን በተለያዩ መጽሆቶቹ የሽፋን ገጽ ላይ (Studies In the Scriptures Series) ሲጠቀም የነበረ ድርጅት ነው (ንቁ! 1976፣ዲሴምበር፣22፣ገጽ 13)፡፡ምንም እንኳን የክርስቲን ጥምቀት መሰረቱ መጽሓፍ ቅዱስ ቢሆንም የይሖዋ ምስክሮች ጥምቀታቸው  ግን መሰረቱ አረማዊ እንደሆነ ይገልጻሉ (መጠበቂያ ግንብ፣1993፣ኤፕሪል፣1፣ገጽ 4)፡፡

      በአጠቃላይ የደም ህክምና ክልከላ መጽሓፍ ቅሳዊ አለመሆኑን እና አንድም ቦታ ይህን ህክምና የሚከክል እንዳሌለ እንረዳለን፡፡ መጽሓፍ ቅዱስም የሚከለክለው ደም መብላትን ሲሆን የዚህም ምክንያት ደም ለመስዋዕትነት የሚቀርብ ስለሆነ ነው፡፡ አምላክ ግን ለመስዋዕትነት የፈቀደው እንስሳን ነው እንጂ ሰውን አይደለም፡፡ ሌላው ድግሞ ደም መብላት እና ደም በደም ሥር መውሰድ አንድ ናቸው ማለት ከእውነት የራቀ እና ማንም ተራ ሰው የሚረዳው ሐሰት ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ የድርጅቱ አማኞች ምንም እንኳን ቢማሩም የሚያስቡት እንደ ድርጅቱ ስለሆነ ደም መብላት እና መውሰድ አንድ ነው ይላሉ፡፡ ይህ የዚህን ድርጅት አደገኛ የአዕምሮ ቁጥጥርን ያሳያል፡፡ ደም መላት እና ደም መውሰድ አንድ ነው የሚለው በዘመናዊ ሳይንስም ይሁም መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ነገር ነው፡፡ ሌላው ከላይ እንደ ተረዳነው በዚህ ትምህርታቸው የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት የሰውን ልጆች ራሳቸው እንዲጠፉ ከማድረጉ ውጪ በመጽሓፍ ቅዱስ እንዳለው ከደም አለመራቁን ነው፡፡ ከሚበሉት የእንስሳት ሥጋ ውስጥ ብዙ ደም መኖሩ እና የደም ደቃቅ ክፍሎችን መጠቀማቸው ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬም ሰዎች በከንቱ እየሞቱ ነው፡፡ እንዲውም በዚህ ክልከላቸው ምክንያት የሞቱትን ደመ ከልብ የሆኑትን ምንም የማያውቁትን ህጻናጽን ጀግኖች በማለት ያሞካሻል (ንቁ! 1994፣ማይ፣22)፡፡

      ታዲያ ደም መብላት ክልክል ነው?

      ደም መብላጽ ስንል ደም በደም ሥር መውሰድ አይደለም፣ምክንያቱም ሁለቱ የተለያዩ ናቸው፡፡ ደም መብላት ስንል የእንስሳትን ደም ማለት ነው፡፡ ይህን ጥያቄ ለመመለስ መጽሓፍ ቅዱስን መመልከት ተገቢ ነው እንጂ በገዛ ፍቃዳችን መሆን የለበትም፡፡ ይህን መልስ በሁለት መንገድ እናየዋለን፡፡ አንደኛ ደም መብላት የተከለከለበት ምክንያት፡፡ ከመጽሓፍ ቅዱ ስንረዳ ደም መብላት የተከለከለበት ምክንያት የእንስሳት ደም በብሉይ ጊዜ ለመስዋዕትነት ስለ ነበረ ነው፡፡ ይህንንም ከላይ ተመልክተናል፡፡ይህንንም መጽሓፍ ቅዱስ የቀድሞ የደም ቃል ኪዳን በማለት ይናገራለ፡፡ ነገር ግን ይህ የቀድሞ አላመ አሁን በክርስቶስ ቤዛነት ቀርቶኣል፡፡ ይህንንም የክርስቶስ ቤዛነት አዲሱ ቃል ኪዳን ይለዋል፡፡ ስለዚህ ደም እንዳይበላ የተከለከለበት ምክንያት አሁን ቀርቶኣል፡፡

      ሀለተኛው ድግሞ በአዲስ ኪዳን ደምን አትብሉ የተባለበት ምክንያት ነው፡፡ ይህንንም መጽሓፍ ቅዱስ ለሌሎች መሰናክል የምትሆኑ ከሆነ አትብሉ ይላል፡፡
      19፤ ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥ 20፤ ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።… 29፤ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ የሓ ሥራ 15፡19-29
      ይህንንም የመጽሓፍ ቅዱስ ምክንያት የይሖዋ ምስክሮች ድርጅት ራሱ ራሳችሁን አጥፉ የሚለውን ምክር ከመስጠቱ በፊት ይጠቀም ነበር፡፡ ከቀድሞው የአይሁድ እምነት የመጡት ክርስቲያኖች ደምን ሲበሉ፣እንዳይሰናከሉ እና ከእውነት እንዳይርቁ ከፈለጋችሁ አትበሉ ነው፡፡
      ስለዚህ ከዚህ ስንመለከት ደምን መብላትም ሆነ አለመብላት ክልከላ የለውም፡፡ ደም አላለመብላት አማራጮች ስላሉ ባንበላ ይመረጣል፡፡ ይህ ደግሞ ኢትዮጲያ በተለይ አመጋገብዋ ከብሉይ የወሰደችው ከመሆኑ አንጻር ነው፡፡

      እንደ አምላክ አላማ ለንስሓ የበቃን ያድርገን፡፡