Pages

Friday, September 4, 2015

Kingdom Interlinear Translation (KIT)

Kingdom Interlinear Translation (KIT)

ይህ የይሖዋ ምስክሮች መፅሃፍ ነዉ፡፡ይህን መፅሓፍ ምናልባትም ብዙዎቹ የይሖዋ ምስክሮች አያዉቁት ይሆናል፡፡ነገር ግን ይህ መጽሓፍ ብዙ መራጃዎችን የሚሰጥ ጠቃሚ መጽሓፍ ነዉ፡፡የይሆዋ ምስክሮችንም መጽሓፍ ቅዱስ ስህተቶችን ለማጥናት በጣም ጠቃሚ መረጃ የሰጣል፡፡
ይህ መጽሓፍ ሙሉ ርዕሱ The Kingdom Interlinear Translation of the Greek Scriptures ሲሆን በብዛት(KIT) ተብሎ በምህጻረቃል የጠራል፡፡KIT ሁለት እትሞች (Editions) ኣሉት፣ የ1969 እና 1985 እ.ኤ.አ ናቸዉ፡፡

በKIT በግራ አምዱ የዌስትኮት እና ሆርትን የግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ እና ከግሪኩ ቃላት ስር የእንግሊዝኛ ቃል በቃል ትርጉም ኣለዉ፡፡በቀኝ አምድ በኩል ደግሞ የይሖዋ ምስክሮች የእንግሊዝኛዉ ኣዲሱ አለም ትርጉም (New World Translation(NWT)) ኣለ፡፡


KIT ሽፋን  እና ባለቤትነት ገፆች



KIT ዉስጥ ናሙናዉን ይመልከቱ!!


መፅሓፉን ያዘጋጁበት ምክንያት (KIT1969 ገፅ 5 ን ይመልከቱ)
1. መሰረታዊዉ ግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ለመረዳት ፡፡
2. የመፅሓፍ ቅዱስ ትክክለኛነት ለማጥናት ነዉ ይላሉ፡፡


እኛም በዚሁ መሰረት ይሄንኑ መፅሓፋቸዉን (KIT) በመጠቀም የይሖዋ ምስክሮች መፅሃፍ ቅዱስ (New World Translation(NWT)) ትክክለኛ ኣለመሆን እናሳያለን፡፡


መፅሓፉን ከፈለጉ በዚህ ይፃፉልን፡፡ silasieamagn@gmail.com

No comments:

Post a Comment