ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት እስቲ “ሰዉ ማለት ምን ማለት ነዉ?” የሚለዉን እንመልስ፡፡‘ሰዉ’ የሚለዉ ቃል ሁለት ነገር ይገልፃል፡፡ኣንደኛ፡የሰዉን ተፈጥሮ(ባህሪ)(ምንነት) ይገላፃል፡፡ይህም ሰዉ የሚባለዉ ተፈጥሮ (ባህሪ) የራሱ የሆኑ መገለጫዎች(attributes, characteristics ) ኣሉት፡፡እነዚህም መገለጫዎች(attributes, characteristics ) በጥቂቱ፡ያስባል፣መጀመሪያ ኣለዉ፣የተፈጠረ ነዉ፣ያመዛዝናል፣ይገነዘባል፣ይናገራል፤ወዘተ ::ስለዚህ አነዚህን መገለጫዎች(attributes, characteristics ) ያሉትን ተፈጥሮ(ባህሪ) ሰዉ እንለዋለን፡፡ በዚህ ትርጉሙ ይህ ‘ሰዉ’ የሚለዉ ቃል ‘ማንድን ነዉ?’ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ሁለተኛ፡የሰዉን አካል(ማንነት) ይገላፃል፡፡ይህም ከላይ የተገለፃዉን ሰዉ የሚለዉን ተፈጥሮ(ባህሪ) ያለዉን አካል ነዉ፡፡ በመሆኑም ይህ ሁለተገኛዉ ሰዉ የሚለዉ ቃል ማን ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ለምሳሌአበበ ከሰዉ ጋር ነዉ፡፡የሚለወዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ ሰዉ የሚለዉ ቃል ኣንድን ግለሰብ ነዉ፡፡
ይህ ዐረፍተነገር ‘አበበ ከማን ጋር ነዉ?’
የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡ ስለዚህ ይህ ዐረፍተነገር
ሁለት አካላዊ ሰዎችን(ግለሰቦች) ይገልፃል(አበበን እና አብሮት ያለዉን ሰዉ)፡፡
አበበ ሰዉ ነዉ፡፡
የሚለወዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ ሰዉ የሚለዉ ቃል ሰዉ የሚባለዉን ተፈጥሮ(ባህሪ) ይገላፃል፡፡
የሚለወዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ ሰዉ የሚለዉ ቃል ሰዉ የሚባለዉን ተፈጥሮ(ባህሪ) ይገላፃል፡፡
ይህ ዐረፍተነገር ‘አበበ ምንድን
ነዉ?’ የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡ስለዚህ ይህ ዐረፍተነገር
ኣንድ ሰዉ(ግለሰብ) ይገልፃል(አበበን)፡፡
በኣለም ላይ ኣንድ
ሰዉ(በተፈጥሮ፣በባህሪ፣ በምንነት) ስድስተ ቢሊዮን ሰዎች(በአካል)
ኣሉ፡፡ስለዚህ ሰዎች በአካል ቢሊዮኖች ሲሆኑም በባህሪ፣በነተፈጥሮ፣በምንነት
ኣንድ ናቸዉ፡፡እንዲሁም ሌሎች ፈጥረታትም ከሰዉ የሚለያቸዉ የራሳቸዉ ባህሪ፣ነተፈጥሮ፣ምንነት እና አካል ኣላቸዉ፡፡ኣንድ አካል እና ልጁ ኣንድ ተፈጥሮ ቢኖራቸዉም የተለያየ አካል ኣላቸዉ፡፡ሰዉ ልጅ ሲወልድ፤አባት እና ልጅ ሁለት የተለያዩ አካላት ሲሆኑ ሁለቱም ግን ሰዉ በመሆናቸዉ ኣንድ ናቸዉ፡፡ሰዉ ሰዉን ይወልዳል ማለት ነዉ፡፡ፈረስም ፈረስን ይወልዳል ማለት ነዉ፡፡
እግዚኣብሔር ማለት ምን ማለት ነዉ?
በተመሳሳይ ማልኩ ‘እግዚኣብሔር’ የሚለዉ ቃል ሁለት ነገር ይገልፃል፡፡
ኣንደኛ፡
የእግዚኣብሔርን ያልተፋጠረ ተፈጥሮ(ባህሪ)(ምንነት) ይገላፃል፡፡
ይህም እግዚኣብሔር የሚባለዉ ያልተፋጠረ ተፈጥሮ (ባህሪ) የራሱ የሆኑ መገለጫዎች(attributes,
characteristics ) ኣሉት፡፡እነዚህም መገለጫዎች(attributes, characteristics ) በጥቂቱ፡ያስባል፣መጀመሪያ የለዉም፣ያልተፋጠረ ነዉ፣ፈጣሪ
፣ያመዛዝናል፣ይገነዘባል፣ይናገራል፤ ሁሉን ቻይ ነዉ፣ወዘተ፡፡ በዚህ ትርጉሙ ይህ ‘እግዚኣብሔር’ የሚለዉ ቃል ‘ማንድን ነዉ?’ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡
ሁለተኛ፡
የእግዚኣብሔርን አካል(ማንነት) ይገላፃል፡፡
ይህም ከላይ የተገለፃዉን
እግዚኣብሔር የሚለዉን ያልተፋጠረ ተፈጥሮ(ባህሪ) ያለዉን አካል ነዉ፡፡በመሆኑም ይህ ሁለተገኛዉ እግዚኣብሔር የሚለዉ ቃል ማን ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡
ለምሳሌ፡
አብረሃም ከእግዚኣብሔር ጋር ነዉ፡፡
የሚለዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ እግዚኣብሔር የሚለዉ ቃል ኣንድን አካል ነዉ የሚገልጸዉ፡፡ይህ ዐረፍተነገር ‘አብረሃም ከማን ጋር ነዉ?’
የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡ስለዚህ ይህ ዐረፍተነገር
ሁለት አካላትነ ይገልፃል(አብረሃምን እና አብሮት ያለዉን አካለ እግዚኣብሔር)፡፡
አብ እግዚኣብሔር ነዉ፡፡
የሚለወዉ
ዐረፍተነገር ዉስጥ እግዚኣብሔር የሚለዉ ቃል እግዚኣብሔር የሚባለዉን ተፈጥሮ(ባህሪ) ይገላፃል፡፡ይህ ዐረፍተነገር ‘‘አብ ምንድን ነዉ?’ የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡
በአማርኛ
|
በእንግሊዝኛ
|
በግሪክ
|
ባህሪ፤ተፈጥሮ
|
substance,essence,nature,being
|
ουσία, ousia (ኦዉሲያ)
|
አካል
|
person
|
Enter your comment...G
ReplyDelete