የይሖዋ ምስክሮች በሮሜ9፡5 ላይ ያለዉን እያሱስ
ክርስቶስን “እሱ ‹ክርስቶስ› ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምለክ” በመለት የሚገልጸዉን ከክርስቶስ በመነጠል ክርስቶስ
እንዲህ አልተባለም የሚል ትርጉም እንዲኖረዉ አድርገዋል፡
ወደሮሜ 9፡5 ከሜሄዳችን በፊት ሮሜ 9፡4 ላይ
የይሖዋ ምስክሮች በግሪኩ መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ የሌለዉን አምለክ የሚለዉን ቃል በገዛ ፈቃዳቸዉ መጨመራቸዉን እነመለከታለን፡፡ ይህንንም
እነሱ ራሳቸዉ ለትርዱማቸዉ የተጠቀሙትን እና የቃል በቃል ትርጉም የሰሩለትን የግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ ፣በ1962 የታተመዉን የአማርኛ
መጽሓፍ ቅዱስ እና በ2007 ባሳተሙት የራሳቸዉ (የይሖዋ ምስክሮች) የአማርኛ መጽሓፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚከተለዉ በማወዳደር በቀላሉ
መረዳት ይቻላል፡፡
የይሖዋ ምስክሮች
በ1985 ከሳተሙት የግሪክ ቃል በቃል ትርጉም ()የተወሰደ፣አምለክ የሚለዉን ትርዱም የያዘዉ GOD ወይም Theos የሚለዉ ቃል
ኣለመኖሩን የስተዉሉ፡፡
4፤ እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና
ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤ (1962 መጽሃፍ ቅዱስ) በግሩኩ ላይ የሌለዉ አምለክ የሚለዉ ቃል እዚም አለመኖሩን የስተዉሉ፡፡
4 እነሱ እስራኤላውያን ናቸው፤ አምላክ
ልጆቹ አድርጎ የወሰዳቸው፣+ ክብር ያገኙት፣ ቃል ኪዳን የተገባላቸው፣+ ሕግ የተሰጣቸው፣+ ቅዱስ አገልግሎት የማቅረብ መብት ያገኙትና+ ተስፋ የተሰጣቸው+ እነሱ ናቸው። (አአት ሮሜ 9፡4 አጽንኦቱ የኔ ነዉ)በግሩኩ ላይ የሌለዉ አምለክ የሚለዉ ቃል መኖሩን
የስተዉሉ፡፡
የይሖዋ ምስክሮች በሮሜ 9፡5 ላይ ደግሞ እሱ
በእንግሊዝኛዉ (the one/who) የሚለዉን የግሪክ ቃል ባለመተርጎም ክርስቶስ ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምለክ የሚለዉን
ትርጉም እንደይኖረዉ አድርገዉታል፡፡ይህንንም ከላይ እንዳወዳደርነዉ ሱስቱን መጻህፍት በማወዳደር እንመለከታለን እንደሚከተለዉ እንመለከታለን፡፡


ሮሜ 9፡5
የይሖዋ ምስክሮች በ1985 ከሳተሙት የግሪክ ቃል በቃል ትርጉም ()የተወሰደ፣ከስር የተሰመሩባቸዉን በመመልከት the
one /
who የሚለዉ ቃል በግሪኩ ውስጥ መኖሩን የስተዉሉ
5፤ አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ
በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ
ነው፤ አሜን።(1962 መጽሃፍ ቅዱስ) በግሩኩ ላይ የለዉ the
one /
who የሚለዉ
ቃል እርሱም ተብሎ መተርጎሙን የስተዉሉ፡፡
5 አባቶችም የእነሱ ናቸው፤+ ክርስቶስም በሥጋ የተገኘው ከእነሱ ነው።+ የሁሉ የበላይ የሆነው አምላክ ለዘላለም ይወደስ። አሜን። (አአት ሮሜ 9፡4 አጽንኦቱ
የኔ ነዉ) በግሩኩ ላይ የለዉ the one / who የሚለዉ ቃል እርሱም ተብሎ ኣለመተሩጎሙን የስተዉሉ፡፡
ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች በሮሜ 9፡4 ላይ በመሰረታዊዉ የግሪክ መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ የሌለዉን አምልክ
የሚለዉን ቃል ከማስገባታቸዉም በላይ በሮሜ 9፡5 ላይ ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ የተባለዉ ለክርስቶስ
መሆኑን የሚያመለክተዉን one / who ወይም እሱም የሚለዉን ቃል ባለመተርጎም
ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ የተባለዉ ለክርስቶስ አይደለም የሚል ትርጉም እንዲኖረዉ አድርገዉታል፡፡
No comments:
Post a Comment