Pages

Friday, September 4, 2015

እግዚኣብሔር ማለት ምን ማለት ነዉ?

ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት እስቲ “ሰዉ ማለት ምን ማለት ነዉ?” የሚለዉን እንመልስ፡፡
‘ሰዉ’ የሚለዉ ቃል ሁለት ነገር ይገልፃል፡
ኣንደኛ፡
የሰዉን ተፈጥሮ(ባህሪ)(ምንነት) ይገላፃል፡፡
ይህም ሰዉ የሚባለዉ ተፈጥሮ (ባህሪ) የራሱ የሆኑ መገለጫዎች(attributes, characteristics ) ኣሉት፡፡እነዚህም መገለጫዎች(attributes, characteristics ) በጥቂቱ፡ያስባል፣መጀመሪያ ኣለዉ፣የተፈጠረ ነዉ፣ያመዛዝናል፣ይገነዘባል፣ይናገራል፤ወዘተ ::ስለዚህ አነዚህን መገለጫዎች(attributes, characteristics ) ያሉትን ተፈጥሮ(ባህሪ)  ሰዉ እንለዋለን፡፡ዚህ ትርጉሙ ይህ ‘ሰዉ’ የሚለዉ ቃል ‘ማንድን ነዉ?’ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡
ሁለተኛ፡
የሰዉን አካል(ማንነት) ይገላፃል፡፡
ይህም ከላይ የተገለፃዉን ሰዉ የሚለዉን ተፈጥሮ(ባህሪ) ያለዉን አካል ነዉ፡፡ በመሆኑም ይህ ሁለተገኛዉ ሰዉ የሚለዉ ቃል ማን ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡
ለምሳሌ
አበበ ከሰዉ ጋር ነዉ፡፡
የሚለወዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ ሰዉ የሚለዉ ቃል ኣንድን ግለሰብ ነዉ፡፡

ይህ ዐረፍተነገር  ‘አበበ ከማን ጋር ነዉ?’ የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡ ስለዚህ ይህ ዐረፍተነገር ሁለት አካላዊ ሰዎችን(ግለሰቦች) ይገልፃል(አበበን እና አብሮት ያለዉን ሰዉ)፡፡

አበበ ሰዉ  ነዉ፡፡
የሚለወዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ ሰዉ የሚለዉ ቃል ሰዉ የሚባለዉን ተፈጥሮ(ባህሪ) ይገላፃል፡፡
ይህ ዐረፍተነገር  ‘አበበ ምንድን ነዉ?’ የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡ስለዚህ ይህ ዐረፍተነገር ኣንድ ሰዉ(ግለሰብ) ይገልፃል(አበበን)፡፡

በኣለም ላይ ኣንድ ሰዉ(በተፈጥሮ፣ባህሪ፣ ምንነት) ስድስተ ቢሊዮን ሰዎች(በአካል) ኣሉ፡፡ስለዚህ ሰዎች በአካል ቢሊዮኖች ሲሆኑም በባህሪ፣በነተፈጥሮ፣በምንነት ኣንድ ናቸዉ፡፡እንዲሁም ሌሎች ፈጥረታትም ከሰዉ የሚለያቸዉ የራሳቸዉ ባህሪ፣ነተፈጥሮ፣ምንነት እና አካል ኣላቸዉ፡፡ኣንድ አካል እና ልጁ ኣንድ ተፈጥሮ ቢኖራቸዉም የተለያየ አካል ኣላቸዉ፡፡ሰዉ ልጅ ሲወልድ፤አባት እና ልጅ ሁለት የተለያዩ አካላት ሲሆኑ ሁለቱም ግን ሰዉ በመሆናቸዉ ኣንድ ናቸዉ፡፡ሰዉ ሰዉን ይወልዳል ማለት ነዉ፡፡ፈረስም ፈረስን ይወልዳል ማለት ነዉ፡፡

እግዚኣብሔር ማለት ምን ማለት ነዉ?

በተመሳሳይ ማልኩ ‘እግዚኣብሔር’ የሚለዉ ቃል ሁለት ነገር ይገልፃል፡፡

ኣንደኛ፡

የእግዚኣብሔርን ያልተፋጠረ ተፈጥሮ(ባህሪ)(ምንነት) ይገላፃል፡፡
ይህም እግዚኣብሔር የሚባለዉ ያልተፋጠረ ተፈጥሮ (ባህሪ) የራሱ የሆኑ መገለጫዎች(attributes, characteristics ) ኣሉት፡፡እነዚህም መገለጫዎች(attributes, characteristics ) በጥቂቱ፡ያስባል፣መጀመሪያ የለዉም፣ያልተፋጠረ ነዉ፣ፈጣሪ ፣ያመዛዝናል፣ይገነዘባል፣ይናገራል፤ ሁሉን ቻይ ነዉ፣ወዘተ፡፡ በዚህ ትርጉሙ ይህ ‘እግዚኣብሔር’ የሚለዉ ቃል ‘ማንድን ነዉ?’ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡

ሁለተኛ፡

የእግዚኣብሔርን አካል(ማንነት) ይገላፃል፡፡

ይህም ከላይ የተገለፃዉን እግዚኣብሔር የሚለዉን ያልተፋጠረ ተፈጥሮ(ባህሪ) ያለዉን አካል ነዉ፡፡በመሆኑም ይህ ሁለተገኛዉ እግዚኣብሔር የሚለዉ ቃል ማን ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡

ለምሳሌ፡

አብረሃም ከእግዚኣብሔር ጋር ነዉ፡፡
የሚለዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ እግዚኣብሔር የሚለዉ ቃል ኣንድን አካል  ነዉ የሚገልጸዉ፡፡ይህ ዐረፍተነገር  ‘አብረሃም ከማን ጋር ነዉ?’ የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡ስለዚህ ይህ ዐረፍተነገር ሁለት አካላትነ ይገልፃል(አብረሃምን እና አብሮት ያለዉን አካለ እግዚኣብሔር)፡፡

አብ እግዚኣብሔር  ነዉ፡፡
የሚለወዉ ዐረፍተነገር ዉስጥ እግዚኣብሔር የሚለዉ ቃል እግዚኣብሔር የሚባለዉን ተፈጥሮ(ባህሪ) ይገላፃል፡፡ይህ ዐረፍተነገር  ‘‘አብ ምንድን ነዉ?’ የሚለዉ ጥያቄ ይመልሳል፡፡


በአማርኛ
በእንግሊዝኛ
በግሪክ
ባህሪ፤ተፈጥሮ
substance,essence,nature,being
ουσία, ousia (ኦዉሲያ)
አካል
person
hypostasis: (ሀይፖስታሲስ)

ዮሓንስ 1፡1(John 1:1)

የይሖዋ ምስክሮች ዮሓ1፡1ን በእንግሊዝኛዉ (… the Word was with God, and the Word was God.) በአማርኛዉ ደግሞ (ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚኣብሄር ነበር፡፡)  የሚለዉን “…the Word was with God, the Word was a god,” ብለዉ ተርጎመዋል፡፡ለአጽንኦት ከስር ያሰመርኩት እኔ ነኛ ፡፡ ይህም ትርዱማቸዉ (የይሆዋ ምስክሮች)ማለት አነስተገኛ መለኮት ፡አብሮት ካለዉ እግዚኣባሄር ያነሰ መለኮታዌ ባህሪ ያለዉ ማለት ነዉ፡፡ ይህም ትርጉም የተሳሳተ እንደሆነ ምሁራን የግሪክን ስዋስዉ

ዮሓ 1፡1
“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር(1) ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር(2)  ነበረ።በቅንፍ ቁጥር የፃፍኩት እኔ ነኝ (1) የመጀመሪያዉን እግዚአብሔር የሚለዉን ቃል ሲያመለክት (2) ደግሞ የሁለተኛዉን እግዚአብሔር የሚለዉን ቃል ያመለክታል፡፡


በግሪኩ ደግሞ (KIT)






በግሪኩ የተብራራ Interlinear



በግሪክ ቐንቐ ኣንድ ቃል እንደ አገባቡ ቅርፁሊለያይ ይችላል፡፡ለበለጠ ግንዛቤ ይህን ይመልከቱ፡፡

ስለዚህ ከላይ እንደምናየዉ እግዚአብሔር የሚለዉ ቃል በግሪክ ቴኦስ (theos/ theon) ይባላል፡፡
ለወጥነት ሁለቱንም ቴኦስ ብዬ አጠቀማለሁ፡፡

በእንግሊዝኛዉ (definite article ‘the’) በግሪኩ ( ho)የሚባለዉ ነዉ፡፡ይህን ቃል የይሖዋ ምስክሮች ፡”በስላሴ ማመን ይገባሃላን?”፡ የሚለው መፅሓፋቸዉ ላይ አመልካች ቃል ይሉታል፡፡

በግሪክ the የሚባለዉ አመልካች ቃል እንደ አገባቡ ፣እንደ ፆታ ፣እንደ ስዋስዉ ሁኔታ ቅርፁ ይለያያል፡፡
ለምሳሌ ከላይ እንደምናየዉ ቶን( τὸν ፣ ton)ም ‘the’ ማለት ነዉ፡፡


በግሪኩ ዮሐ 1፡1 ላይ የመጀመሪያዉን ‘እግዚአብሔር’ የሚለዉን ቃል የሚያመለክተዉ የግሪኩ ‘ቴኦስ’ ከፊቱ አመልካች ቃል ( ho)ኣለዉ፡፡ የሁለተኛዉን ‘እግዚአብሔር’ የሚለዉን ቃል የሚያመለክተዉ የግሪኩ ‘ቴኦስ’ ከፊቱ አመልካች ቃል ( ho)የለዉም፡፡
ይህን የመፅሓፍ ቅዱስ ክፍል የይሖዋ ምስክሮች በእንግሊዝኛዉ ‘a god‘ ብለዉ ተርጉመዋል፡፡
ይህም ማለት አነስተገኛ መለኮት ፡አብሮት ካለዉ እግዚኣባሄር ያነሰ መለኮታዌ ባህሪ ያለዉ ማለት ነዉ፡፡
ለምን (a god) እንዳሉ የሚከተሉትን ምክንያቶች ይሰጣሉ፡፡ማስረጃ፡፡”በስላሴ ማመን ይገባሃላን? ገፅ 26-28፣Aid-To-Bible-Understanding 1971 page 919,Watch tower Nov-15-1975 page 702 -704፣KIT 1969 page1158-1160)
1.      ቃልም እግዚአብሔር(2)  ነበረ። (The Word was God)
ማለት ቃልን አብሮት ካለዉ እግዚአብሔር ጋር በአካል ኣንድ ያረገዋል ይላሉ፡፡
2.     ከግሪኩ ቴኦስ በፊት አመልካች ቃል ( ho)ስለሌለ ‘a god‘ መሆን ኣለበት ይላሉ፡፡
3.     የግሪክ ስዋስዉ a god የሚለዉን ይደግፋል ይላሉ፡፡


መልስ

የይሖዋ ምስክሮች ምክንያት 1
በእርግጥ በመሠረታዊዉ ግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ ዉስጥ ከዉለተኛዉ ቴኦስ በፊት ሆ የሚለዉ አመላካች ቃል ቢኖር ኖሮ የይሖዋ ምስክሮች እንደሚሉት ቃልን አብሮት ካለዉ እግዚኣብሄር ጋር በአካል ኣንድ ያደርገዉ ነበር፡፡
ትርጉሙም “The word was the God” ቃልም እግዚኣብሄሩን ነበር፡ወይም ቃልም ያንኑ እግዚኣብሄር ነበር፡፡ የሚል ይሆን ነበር፡፡
በመጀመሪያም ይህ ሀሳብ በመሠለታዊዉ ግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ ዉስጥም ይሁን በእንግሊዚገኛዉ እንዲሁም የአማርኛ ትርጉም ዉስጥ የለም፡፡
ነገር ግን የይሖዋ ምስክሮች ያልተፃፈዉን በማንበብ ሰዎችን እያደነጋገሩ ነዉ፡፡ለምሳሌ በKIT 1969  ገፅ 419 እና  KIT 1985  ገፅ 401 ላይ  “A god” in contrast to “the God” በማለት በዮሐ1፡1 ግረጌ ማስታወሻ ላይ ፅፈዋል፡፡ይህም ማለት “the God” ሳይሆን “A god” ነዉ መሆን ያለበት ይላሉ፡፡ነገር ግን “the God” የሚለው  በመሠለታዊዉ ግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ ዉስጥም ይሁን በእንግሊዚገኛዉ እንዲሁም የአማርኛ ትርጉም ዉስጥ የለም፡፡ምክነያቱም ‘the’  የሚለዉን አመልካች ቃል የሚወክለዉ ‘ሆ ‘ የሚለዉ የግሪክ ቃል የለም፡፡
ስለዚህ  የይሖዋ ምስክሮች “The word was God”  ወይም በአማርኛዉ  “ቃልም እግዚኣብሄር ነበር፡፡” የሚለዉ ቃልን አብሮት ካለዉ እግዚኣብሄር ጋር ኣንድ አካል ያደርገዋል የሚሉት ፈፁም ስህተት እና የግሪክ ቓንቓን በተክክል ካለመረዳት ወይም ሆን ተብሎ ሰዎችን ለማደነጋገር የተደርገ ነዉ፡፡
ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ያስቀመጡት ይህ ምክንያት መሰረተቢስ ነዉ፡፡

የይሖዋ ምስክሮች ምክንያት 2
ከዉለተኛዉ ቴኦስ በፈፊት የግሪኩ አመልካች ቃል (ሆ) ስለሌለ ትርጉሙ a god  መሆን ኣለበት ይላሉ፡፡
ባጠቃላይ 
ሆ ቴኦስ(ሆ የለዉ ቴኦስ) = God
ቴኦስ (ሆ የሌለዉ ቴኦስ) = a god
ነዉ ይላሉ፡፡
ነገር ግን በዚህ ምክንያት እንዳልሆነ እዚያዉ የዮሓንስን ወንጌል ምእራፍ ኣንድን ማየት ይቻላል፡፡
አመልክች ቃል ሆ የሌለዉን ቴኦስን  a god ብለዉ መተርጎም ሲኖርባቸዉ God  ብለዉ ተርጉማዋል፡፡

Kit 1969 አና KIT 1985 





በአጠቃላይ በመሠረታዊዉ ግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ ዉስጥ ካሉት 282 አመልካች ቃል አልባ ቴኦስ ሁሉንም   a god,god,gods ወይም godlike ብለዉ መተርጎም ሲኖርባቸዉ  16ቱን ብቻ ነዉ በዚህ መልኩ የተረጎሙት፡፡
ስለዚህ እራሳቸዉ ያስቀመጡትን ህግ 266 (94%) ጊዜ ጥሰዋል፡፡
ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ያስቀመጡት ይህ ምክንያትም (ሁለተኛዉ) መሰረተቢስ ነዉ፡፡



የይሖዋ ምስክሮች ምክንያት 3
ሦስተገኛዉ ምክንያታቸዉ ደግሞ ትንሽ ክዚህ ከፍ ያለ የግሪክ ስዋስዉ ነዉ፡፡
ይህም አመልካች ቃል (ሆ) አልባ ተሳቢ የሚል ነዉ፡፡
ተሳቢ ምን እንደሆነ በምሳሌ
1,  Abebe is man.                                                             አበበ ሰዉ ነዉ፡፡                                       
2, Abebe is the man.                                                        አበበ ሰዉዬዉ ነዉ፡፡
በዐረፍተነገር (1)     ዉስጥ ያሉት man እና ሰዉ የሚሉት አመልካች ቃል አልባ ተሳቢዎች ናቸዉ፡፡   
በዐረፍተነገር (2)    ዉስጥ ያሉት the man እና ሰዉዬዉ የሚሉት አመልካች ቃል ያላቸዉ ተሳቢዎች ናቸዉ፡፡  
Abebe እና አበበ የዐረፍተነገሮቹ ባለቤት ናቸዉ፡፡
            በግሪክ የእንደዚህ አይነት ዐረፍተነገር ባለቤት የሚሆነዉ አመልካች ቃል ከፍቱ ያለዉ ስም ነዉ፡፡
ስለዚህ ዮሓ 1፡1 ላይ አመልካች ቃል(ሆ) ከሎጎስ በፊት ስለሆነ ሎጎሰ (ቃል) የዐረፍተነገሩ ባለቤት ነዉ ማለት ነዉ፡፡
ቴኦስ ደግሞ ከፊቱ አመልካች ቃል (ሆ) ከፊቱ ስለሌለ ተሳቢ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
በግሪክ ተሳቢ ቃለል ከግስ በፊትም  በኃለም ሊመጣ ይችላል፡፡በዮሓ 1፡1 ላይ ያለዉ ቴኦስ ከግስ በፊት  የመጣ ተሳቢ ነዉ፡፡

በመሆኑም



በዚህ ምክንያታቸዉ ላይ ብዙ ምሁራንን እንደማስለጃ ጠቅሰዋል፡፡KIT 1969 ገፅ 1158-1160,NWT 1950  ገፅ 773-777 ይመልከቱ
የይሖዋ ምስክሮች የግሪክ አመልካች ቃል አልባ ተሳቢን ስንተረጉም ከፊቱ ‘a’ ን ማስገባት ኣለብን ይላሉ፡፡
 ነገር ግን ለምሳሌ(በጥቂቱ)
ዮሓ 1፡14 ላይ ቃልም ሥጋ ሆነ፡፡የሚለዉ ዉስጥ ሥጋ የሚለዉ ቃል በግሪኩ አመልካች ቃል አልባ ተሳቢ ነዉ፡፡
የይሖዋ ምስክሮች ከላይ ባስቀመጡት ምክንያት መሰረት “The word became a flesh” ብለዉ  መተርጎም ሲኖርባቸዉ እንደ ሌሎቹ ትርጉሞች “The word became flesh” ብለዉ ትክክለኛዉን ትርጉም ሰጥተዋል፡፡
ዮሓ 1፡49
የይሖዋ ምስክሮች ከላይ ባስቀመጡት ምክንያት መሰረት ‘a king’ ብለዉ መተረጎም ሲኖርባቸዉ ‘King’ ብለዉ ትጉማዋል፡፡
1ኛ ዮሓ 1፡5
እግዚኣብሔር ብርሃን ነዉ፡፡
የሚለዉ ዉስጥ ብርሃን የሚለዉ ቃል በግሪኩ አመልካች ቃል አልባ ተሳቢ ነዉ፡፡
የይሖዋ ምስክሮች ከላይ ባስቀመጡት ምክንያት መሰረት “God is a light” ብለዉ  መተርጎም ሲኖርባቸዉ እንደ ሌሎቹ ትርጉሞች “God is light” ብለዉ ትክክለኛዉን ትርጉም ሰጥተዋል፡፡
1ኛ ዮሓ 1፡8፣16
እግዚኣብሔር ፍቅር ነዉ፡፡
የሚለዉ ዉስጥ ፍቅር የሚለዉ ቃል በግሪኩ አመልካች ቃል አልባ ተሳቢ ነዉ፡፡
የይሖዋ ምስክሮች ከላይ ባስቀመጡት ምክንያት መሰረት “God is a love” ብለዉ  መተርጎም ሲኖርባቸዉ እንደ ሌሎቹ ትርጉሞች “God is love” ብለዉ ትክክለኛዉን ትርጉም ሰጥተዋል፡፡
ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ያስቀመጡት ይህ ምክንያትም (ሦስተኛዉ) አሁንም መሰረተቢስ ነዉ፡፡
እስቲ አሁን a god በሚለዉን ትርጉማቸዉ ዙሪያ የጠቀሰዋቸዉ ምሁራን ምን እንዳሉ አንመልከት፡፡
ከዚያ በፊት ግን


ባህሪ፤ተፈጥሮ በእንግሊዝኛ substance,essence,nature,being በግሪክ ደግሞ ουσία, ousia (ኦዉሲያ) 
አካል በእንግሊዝኛ  person  በግሪክ ደግሞ  hypostasis: (ሀይፖስታሲስ)

ባህሪ፡ተፈጥሮ ወይም ምንነት (essence,substance nature,being) እና አካል(person,individual) ምን ማለት እንደሆኑ እዚህ ይመልከቱ፡፡
1፣ ዳነ እና ማንቲ
የይሖዋ ምስክሮች በ NWT1950(ኣዲሱ አለም ትርጉም) ገፅ 774 እና በ KIT1969 ገፅ 1158 ላይ መፅሓፋቸዉን ለማስለጃነት ጠቅሰዋል፡፡
ነገር ግን በዳነ እና ማንቲ መፅሓፍ ላይ እንዲህ ይላል
“The use of theos in Jn1:1 … points to Christs fellowship with the person of the Father…emphasizes Christs participation in the essence of the divine nature.” በማለት ዮሓ 1፡1 ክርስቶስ በባህሪዉ (በአምላክነቱ) ከኣብ ጋር እኩል (fellowship) መሆኑን እና ኣንድ አይነት መለኮታዊ የልተፈጠረ ተፈጠሮ (ባህሪ)(essence) እንደሚጋሩ (participation) ይገላፃል፡፡
በመቀጠልም
“the other person of trinity maybe implied in Theos” በማለት የስላሴን ሦስተኛ አካል( person) ሊያሳይ እንደሚችልይገላፃል፡፡
ዶክተር ማንቲ ዮሓ1፡1ን በተመለከተ ዶክተር ማርቲን ላቀረበለት ጥያቄ እነዲህ ብሎ መልሶዋል
DR. MARTIN: In John 1:1, the New World Translation (NWT) says that “the Wordwas a God,” referring to Jesus Christ. How would you respond to that?
DR. MANTEY: The Jehovah’s Witnesses have forgotten entirely what the order of the sentence indicates - that the “Logos” has the same substance, nature, or essence as the Father. To indicate that Jesus was just “a god,” the JWs would have to use a completely different construction in the Greek
order of the sentence indicates - that the “Logos” has the same substance, nature, or essence as the Father.
በማለት በዮሓ1፡1 ለይ ያለዉ የዐረፍተነገር አደራደር (order of the sentence) ቃል እና ኣብ ኣንድ ባህሪ፣ያልተፈጠረ ተፈጥሮ( same substance, nature, or essence) እንዳላቸዉ ያሳያል ይላል፡፡
የሚለዉን ትርጉም የሚሰጠዉ ዮሓ 1፡1 ላይ ያለዉ የዐረፍተነገር አደራደር (order of the sentence) ሳይሆን ፍፁም የተለየ( completely different) የዐረፍተነገር አደራደር (order of the sentence) እንዳለ ይገልፃል፡፡
ስለዚህ ማንቲ “a god,” የሚለዉ የዮሓ1፡1 ትርጉም ስህተት ነዉ ይላል፡፡የላቁንም ቃል እና ኣብ እግዚኣብሄር በመሆን ኣንድ ናቸዉ ይላል፡፡
2፣ ግሪን
የዚህን ሰዉ መፅሓፍ በ NWT 1950 ገፅ 775 እና በ KIT 1159 ገፅ 1159 ላይ ይጠቅሱታል፡፡
ነገር ግን በግሪን መፅሓፍ ላይ እንዲህ ይላል
“Without the article throws the stress rather upon the general conception of the Divine Character…one who is Omnipotent All-holly, Infinity, &c”
በማለት አመልካች ቃል አልባዉ ቴኦስ ጠቅላላን አምላካዊ ባህሪ(የእግዚኣብሄር ባህሪ)( general conception of the Divine Character) ሁሉን ቻይነቱን (Omnipotent) ፍፁም ቅዱስነቱን (All-holly) በጊዜ እና በቦታ ያለመወሰኑን  (Infinity,) ነዉ ይላል፡፡
ስለዚህ ግሪንም ቃል ሁሉንም የእግዚኣብሄር ባህሪያት እንዳሉት ይገልፃል ይላል፡፡ይላል፡፡ይህም ኣብ በባህሪዉ እግዚኣብሄር እንደሆነ ሁሉ ቃልም በባህሪዉ እግዚኣብሄር ነዉ ማለት ነዉ፡፡
ግሪን በፅሓፉ ገጽ 194 ለይ ዮሓ 1፡1ን the Word was God ብሎ ተርጎሞዋል፡፡


3፣ሮበርትሰን
የዚህን ሰዉ መፅሓፍ በ NWT 1950 ገፅ 775 እና በ KIT 1969 ገፅ 1159 ላይ ይጠቅሱታል፡፡
በተራቁጥር 2 ላይ የጠቀስነዉ ግሪን በመፅሓፍ ገጽ 193 ላይ ሁሉን አቀፍ ህግ (General rule) በማለት እንዲህ ጽፎዋል
“the general rule, that in the simple sentence the Subject takes the article, the Predicate omits it.”
“ሁሉን አቀፍ ህግ ፣የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት አመልካች ቃል (ሆ) ሲኖረዉ የዐረፍተ ነገሩ ተሳቢ ደግሞ አመልካች ቃል የለዉም፡፡”
የይሖዋ ምስክሮች ዳና እና ማንቴ በመጽሓፋቸዉ ገፅ 140 ላይ የሮበርትሰንን መጽሓፍ ገጽ 761 ጠቅሰዉ የጻፉትን በመጥቀስ ዮሓ 1፡1 ሁሉን አቀፍ (General rule) ዉስጥ አይካተትም ስለዚህ የስለሴ አማኞችን ምክንያት ያሳጣል ይላሉ፡፡
ነገር ግን ዮሓ 1፡1 በዚህ ህግ ዉስጥ እንደሚታቀፍ የይሖዋ ምስክሮች አዝያዉ መጽሓፋቸዉ(KIT 1969 page 775) ላይ  ጽፈዋል፡፡
ሮበርትሰንም በገጽ 767
“As a rule the predicate is without the article, even when the subject uses it….. The word with the article is then the subject, whatever the order may be. So in Jo. 1 : 1, …, the subject is perfectly clear.”
ሮብንሰን የገሪንን general rule መልሶ በማተት ዮሓ 1፡1 general rule ዉስጥ  እንደሚታቀፍ ገላጾዋል፡፡
ግሪንም በመፅሓፉ ገጽ 193 ላይ ዮሓ 1፡1ን በምሳሌነት በማስቀመጥ general rule ዉስጥ  እንደሚታቀፍ ገላጾዋል፡፡
ዳነ እና ማንቲም በመፅሓፉቸዉ ገጽ 140 ላይ ሮብንሰንን መጽሓፍ በመጥቀስ እና በመደገፍ ጽፈዋል፡፡
 ሮብንሰን WORD PICTURES IN THENEW TESTAMENT, THE FOURTH GOSPEL THE EPISTLE TO THE HEBREWS በሚለዉ መጽሓፉ ላይ

“And the Word was God (kai theos ên ho logos). By exact and careful language John denied Sabellianism by not saying ho theos ên ho logos. ……. here John disposes of Arianism also because the Logos was eternally God, fellowship of Father and Son,”
“ቃልም እግዚኣብሄር ነበር (ካይ ቴኦስ እን ሆ ሎጎሰ)፡፡በጠንቃቃ ቋንቋዉ  ሆ ቴኦስ እን ሆ ሎጎሰ ባለማለት የሰባሊዮስን ትምህርት ካደ፡፡….እዚህ ዮሓንስ የኣርዮስን ትምህርት ያጣጥላል ምክንያቱም ቃል ዘላለማዊ አምላክ፣ከኣብ እና ከወልድ ጋር ኣቻ ነዉ፣… ”
ስለዚህ ሮብንሰን “the Word was a god,” የሚለዉን ይቃወማል “the Word was God” የሚለዉን ይደግፋል፡፡
ከላይ የጠቀስናቸዉ ሙሁራን የይሖዋ ምስክሮች “the Word was a god,” ለሚለዉ ትርጉማቸዉ ይደግፉናል ብለዉ ዋቢ ያረጉዋቸዉ ሰዎች ናቸዉ፡፡
ነገር ግን አዉነታዉ ሁሉም ከላይ እንዳየነዉ የሚቃወሙኣቸዉ ናቸዉ፡፡
የይሖዋ ምስክሮች እነዚህን ሙሁራን ዋቢ ያደረጉት በኣዲሱ አለም ትርጉም 1950(New World Translation 1950) እና ኪንግደም ነትረሊነኣር 1969(KIT 1969) ላይ ነዉ፡፡
ዶክተር ማርቲን ዶክተር ማንቴን ስለ የይሖዋ ምስክሮች ዮሓ1፡1 ትርጉም እንዲህ ብሎ ጠይቆት ነበር፡፡
“DR. MARTIN: Often we find JW publications quoting scholars. Do they quote
these people in context?”
“ዶክተር ማርቲን፡ብዙ ጊዜ የይሖዋ ምስክሮች በጽሁፎቻቸዉ ላይ ምሁራንን ዋቢ ያረጋሉ፡፡አነዚህን ሰዎች በአግባቡ ነዉ የሚጠቅሱት?”
“DR. MANTEY: No. They use this device to fool people into thinking that scholars
agree with the JWs.”
“ዶክተር ማንቴ፡አይደለም፡፡ ምሁራን ከይሖዋ ምስክሮች ጋር ይስማማሉ ብለዉ ሰዎች እንዲያስቡ ለማሞገኘት ይሄንን ይጠቀማሉ፡፡”
ምንም እንኳን የይሖዋ ምስክሮች የምሁራንን ሀሳብ አጣመዉ በመጠቀም ምሁራን ይደግፉናል ብለዉ ሰዎችን ላማሞኛት ቢሞክሩም እዉነቱ ማዉጣቱ አልቀረም፡፡
በእርግጥ ምስኪን የይሖዋ ምስክሮች ድርጅታቸዉን ኣምነዉ መረጃዉን ያልመረመሩት እየተሞኙ ኖረዋል፡፡
በጣም የሚያሳዝነዉ ግን ይህ ድርጅት እነዚህን እሱን ያመኑትን ምስኪኖች ለማታለል እንዴት ህሊናዉ እንዴት ፋቀደለት ነዉ፡፡

ዉድ የይሖዋ ምስክር ወንዲሞች ሆይ፣ሐይማኖታችሁን ማርምሩ፣እዉነታዉን ተረዱ፣ብዙ መስዋእተነተ የምትከፍሉበትን ሀይማኖታችሁን አሁን ሳይረፍድ ማርምሩ፡፡
የይሖዋ ምስክሮች ከ1950() እና ከ1969(KIT 1969) እ.አ.አ በኃለ በጻፉት የ1985ቱ የኪንግደም ነትረሊነኣር (KIT)መጽሓፋቸዉ ላይ  ከላይ የጠቀስናቸዉን ምሁራንን ከመጥቀስ ተቆጥበዋል፡፡ይህም ምሁራኑን በተሳሳተ መንገድ መጥቀሳቸዉን ማረዳታቸዉን ያሳያል፡፡ነገር ግን ምሁራኑንም ሆነ ምስኪኑን የይሖዋ ምስክሮችን ይቅርታ እንኳን ኣልጠየቁም፡፡
በ1985ቱ የኪንግደም ነትረሊነኣር (KIT)መጽሓፋቸዉ ላይ ኣንድ የስዋስዉ ምሁር ብቻ ነዉ ዋቢ ያረጉት፡፡
እስቲ አሁን ደግሞ በ1985ቱ የኪንግደም ነትረሊነኣር (KIT)መጽሓፋቸዉ ላይ ዋቢ ያረጉትን ምሁር እንይ፡፡
4፣ፍሊፕ ቢ ሀርነር
በ1985ቱ የኪንግደም ነትረሊነኣር (KIT)መጽሓፋቸዉ ላይ የይሖዋ ምስክሮች የፍሊፕ ቢ ሀርነርን ጥናታዊ ጽሁፍ ገጽ 85ን ዋቢ ኣርገዋል፡፡ፍሊፕ ቢ ሀርነርም “the Word was a god,” የሚለዉን ትርጉማቸዉን እንደሚደግፍ በስላሴ ማመን ይገባሃልን; የሚለዉ መጽሓፈቸዉ(የይሖዋ ምስክሮች ) ላይ ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን ፍሊፕ ቢ ሀርነር ዮሓ1፡1ን በተመለከተ ቁልጭ ኣርጎ ኣስቀምጦዋል፡፡
“the Word was a god,” የሚለዉን የሚሰጠዉ የግሪክ ዐረፍተ ነገር ho logos en theos ነዉ፡፡ ይህም የግሪኩ መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ የለም፡፡ስለዚህ “the Word was a god,” የሚለዉ የይሖዋ ምስክሮች ትርጉም የግሪኩ መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ እንዳሌለ ፍሊፕ ቢ ሀርነርን ገልጾኣል፡፡
የግሪኩ መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ የለዉ theos en ho logos ነዉ፡፡ይህም ትርጉሙ ኣብ እና ቃል (ወልድ) ኣንድ እዉነተኛ ኣምላካዊ ባህሪ እንደሚጋሩ ነዉ በማለት ፍሊፕ ቢ ሀርነርን  እንደሚከተለዉ ይገልጻል፡፡
they share the same nature as belonging to the reality theos.
“አንድ እዉነተኛ ኣምላካዊ ባህሪ ይጋራሉ፡፡”
"the Word had the same nature as God."
“ቃል እና እግዚኣብሄር(አብሮት ያለዉ እግዚኣብሄር) ኣንድ (ያልተፈጠረ)ተፈጥሮ ኣላቸዉ፡፡”
that ho logos, no less than ho theos, had the nature of theos.
ቃል (ho logos) አብሮት ካለዉ እግዚኣብሄር( ho theos) አያንስም፡፡ ኣንድ ተፈጥሮ(ያልተፈጠረ) ኣላቸዉ፡፡
“by differentiating between theos,as the nature that the Logos shared with God, and ho theos as the “person” to whom the Logos stood in relation. Only when this distinction is clear can we say of the Logos that “he was God””
ቃል እና እግዚኣብሄር(አብሮት ያለዉ እግዚኣብሄር) ኣንድ (ያልተፈጠረ)ተፈጥሮ እንደሚጋሩ እና በአካል የተለያዩ እንደሆኑ ስንረዳ ብቻ  ቃልም እግዚኣብሄር ነበር ማለት ያለብን ይላል፡፡ይህ ደግሞ ሁሉም የስላሴ አማኞች የሚሉት ነዉ፡፡
ስለዚህ ሆረነርም “the Word was a god,” የሚለዉን የዮሓ1፡1 ን ትርጉም ይቃወማል፡፡
አሁንም የይሖዋ ምስክሮች የሚቃወማቸዉን ሆረነርን የሚደግፋቸዉ አስመስለዉ ለማታለል ሞክረዋል፡፡
ምኪኖቹን የይሖዋ ምስክሮችን ደግሞ አታለዋል፡፡
ከዚህ በኃለ የምናየዉ በሌሎች ጽሑፎቻቸዉ የጠቀስዋቸዉን ምሁራን ነዉ፡፡
5፣ዌስተኮት
የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፍ ቅዱሳቸዉን (ኣዲሱ አለም ትርዱምን) ለመተረጎም የተጠቀሙት የዚህን ሰዉ(ዌስተኮትን) የግሪክ መጽሓፍ ቅዱስ ነዉ፡፡በይሖዋ ምስክሮች ኪንግደም ነትረሊነኣር (KIT)መጽሓፋቸዉ ላይ በግራ ያለዉ የዚሁ ሰዉ(የዌስተኮት) የግሪክ መጽሓፍ ቅዱስ ነዉ፡፡
ዌስተኮት “the Word was a god,” የሚለዉን ይደግፋል በማለት የይሖዋ ምስክሮች Aid To Bible Understanding, 1971, በሚለዉ መጽሓፋቸዉ ገጽ 919 ላይ ዌስተኮትን ይጠቅሱታል፡፡
ነገር ግን ዌስተኮት እንዲህ ይላል
“No idea of inferiority of nature is suggested by the form of expression …Which simply affirms the true deity of the word”
“ምንም የባህሪ በታችነትን አይገልጽም፡፡የቃልን ፈጹም አምላክነትን ይገልጻል፡፡”በማለት ዮሓ1፡1 ቃል እና ኣብ በባህሪ ኣቻ መሆናቸዉን ይገላጻል ዌስተኮት፡፡
ስለዚህ ዌስተኮትም “the Word was a god,” የሚለዉን ቃል እና ኣብ በባህሪ ኣቻ ኣለመሆናቸዉን የሚገልጸዉን ትርጉም  ይቃወማል፡፡
6፣ዊሊያም ባርክሌይ
ይህን ሰዉ መጠበቂያ ግንብ ሜይ 1977 ገጽ 320(Watch Tower 1977, May 15,page 320 ) ላይ ለዚሁ ዋቢነት ይጠቅሱታል፡፡
ነገር ግን ባርክሌይ በመጽሓፉ ስለ ዮሓ1፡1 እንዲህ ይላል፡፡
"The Word was as to his essence essential deity."
ቃል በባህሪዉ ጉድለት የሌለበት ፍጹም        (እዉነተኛ) አምላክ ነዉ፡፡ይላል፡፡
"What God was the Word was."
አብሮት ያለዉ እግዚኣብሄር ያሆነዉን ቃልም ነዉ፡፡በማለት አብሮት ያለዉ እግዚኣብሄር ያለዉን ባህሪ ሁሉ ቃልም ኣለዉ ይላል፡፡


ስለዚህ ባርክሌይም ቃልን አብሮት ካለዉ እግዚኣብሄር ጋር በባህሪዉ እኩል በማድረግ “the Word was a god,” የሚለዉን ቃል እና ኣብ በባህሪ ኣቻ ኣለመሆናቸዉን የሚገልጸዉን ትርጉም  ይቃወማል፡፡ 

ከላይ እንደ ተረዳነዉ ሁሉም ምሁራን የይሖዋ ምስክሮች መጽሓፍ ቅዱሳቸዉ ላይ ያለዉን “the Word was a god,” የሚለዉን ትርጉም የግሪክ ስዋስዉ እንደማይፈቅድ እና “the Word was a god,” የሚለዉ ትርጉም ስህተት ስንደሆነ ገላጸዋል፡፡
ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ሆን ብለዉ እያሱስ ከርስቶስ ከኣብ በበህሪዉ ያንሳል የሚለዉን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ያልሆነዉን ትምህርታቸዉን በግድ መጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ ለማስገባት ዮሓ1፡1ን በተሳሳተ ማልኩ ተርጉመዋል፡፡
ይህንንም ሆን ብለዉ በፍላጎታቸዉ እንዳረጉት የሚያሳይ ሀሳባቸዉን እንዲህ ገልጸዋል
“..we chose to insert … “a” ..”watchtower 1975,nov 15,page 702-704
“እንደገዛ ምኞታቸዉ ለራሳቸዉ አስተማሪዎችን ያከማቻሉ፡፡”2ኛ ጢሞቲ 4፡3
ዋቢ መጻህፍት
1)           H. E . D a n a , and J u l i u s r. M a n t e y ,”A Manual Grammar of the Greek New Testament”, fifteenth printing, 1967,
2)      Maurice Barnett  “Jehovah's Witnesses “Printing Service; 1975
3)     Samuel G. Geeen  ”Handbook to the Grammar of the Geeek Testament”. London : The Religious Tract Society, 66, Paternoster Row; 65, ST. Paul's Churchyard;and 164, Piccadilly.
4)         A. T. Robertson,”A Grammar of the Greek New Testament in the Light of HistoricaL Research” Hodder & Stoughton New York George H. Doran Company, 1914
5)     Archibald Thomas Robertson “Word Pictures in the New Testament,  Volume V the Fourth Gospel the Epistle to the Hebrews.”
6)         Philip Harner "Qualitative Anarthrous Predicate Nouns: Mark 15:39 and John 1:1." The Journal of Biblical Literature 92, March 1993,
7)    B.F.Westcot “Gospel according to St John the Authorized with introduction and notes” London,John Murray,Asbemarle Street,1882
8)       William Barclay “Many Witnesses, One Lord “ Westminster John Knox Press,2001
9)      New World Bible Translation Committee “The Kingdom Interlinear Translation of the Greek Scriptures,” Watchtower Bible and Tract Society of New York. inc. Brooklyn, New York. u.s.a., 1969,
Copyright by WATCH TOWER BIBLE AND TRACT SOCIETY OF PENNSYLVANIA
10)  New World Bible Translation Committee “The Kingdom Interlinear Translation of the Greek Scriptures,” Watchtower Bible and Tract Society of New York. inc. Brooklyn, New York. u.s.a.,1985,
WATCH TOWER BIBLE AND TRACT SOCIETY OF PENNSYLVANIA all Rights Reserved
1 11)  New World Bible Translation Committee “The New World Translation of the Christian Greek Scriptures” Watchtower Bible and Tract Society of New York. inc. Brooklyn, New York. u.s.a.,1950,
Copyright by WATCH TOWER BIBLE AND TRACT SOCIETY OF PENNSYLVANIA

Kingdom Interlinear Translation (KIT)

Kingdom Interlinear Translation (KIT)

ይህ የይሖዋ ምስክሮች መፅሃፍ ነዉ፡፡ይህን መፅሓፍ ምናልባትም ብዙዎቹ የይሖዋ ምስክሮች አያዉቁት ይሆናል፡፡ነገር ግን ይህ መጽሓፍ ብዙ መራጃዎችን የሚሰጥ ጠቃሚ መጽሓፍ ነዉ፡፡የይሆዋ ምስክሮችንም መጽሓፍ ቅዱስ ስህተቶችን ለማጥናት በጣም ጠቃሚ መረጃ የሰጣል፡፡
ይህ መጽሓፍ ሙሉ ርዕሱ The Kingdom Interlinear Translation of the Greek Scriptures ሲሆን በብዛት(KIT) ተብሎ በምህጻረቃል የጠራል፡፡KIT ሁለት እትሞች (Editions) ኣሉት፣ የ1969 እና 1985 እ.ኤ.አ ናቸዉ፡፡

በKIT በግራ አምዱ የዌስትኮት እና ሆርትን የግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ እና ከግሪኩ ቃላት ስር የእንግሊዝኛ ቃል በቃል ትርጉም ኣለዉ፡፡በቀኝ አምድ በኩል ደግሞ የይሖዋ ምስክሮች የእንግሊዝኛዉ ኣዲሱ አለም ትርጉም (New World Translation(NWT)) ኣለ፡፡


KIT ሽፋን  እና ባለቤትነት ገፆች



KIT ዉስጥ ናሙናዉን ይመልከቱ!!


መፅሓፉን ያዘጋጁበት ምክንያት (KIT1969 ገፅ 5 ን ይመልከቱ)
1. መሰረታዊዉ ግሪክ መፅሓፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ለመረዳት ፡፡
2. የመፅሓፍ ቅዱስ ትክክለኛነት ለማጥናት ነዉ ይላሉ፡፡


እኛም በዚሁ መሰረት ይሄንኑ መፅሓፋቸዉን (KIT) በመጠቀም የይሖዋ ምስክሮች መፅሃፍ ቅዱስ (New World Translation(NWT)) ትክክለኛ ኣለመሆን እናሳያለን፡፡


መፅሓፉን ከፈለጉ በዚህ ይፃፉልን፡፡ silasieamagn@gmail.com