Pages

Friday, September 23, 2050

ስለ ጦማሩ

‘People should examine all the evidence by examining both sides of a matter.’ Awake, 22 October 1973, p.6).
ከላይ እንደምናየዉ የይሆዋ ምስክሮች መጽሔት የሆነዉ ፣የኦክቶበር/22/ገጽ 6 ንቁ መጽሔት ሰዎች(የይሆዋ ምስክሮችን ጨምሮ) ኣንድን ጉዳይ መረጃ በመጠቀም ግራ ቀኙን እንዲመረምሩ ያበረታታል፡፡
በጽሓፍ ቅዱስም ይሄንኑ ያሳስባል፡፡
·         “የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ በመንፈስ የተነገረን ቃል* ሁሉ አትመኑ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ የተነገሩት ቃላት* ከአምላክ የመነጩ መሆን አለመሆናቸውን መርምሩ፤+ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+1 ዮሐንስ 4:1 (አአት)
·         “በእምነት ውስጥ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ዘወትር ራሳችሁን ፈትሹ፤ ማንነታችሁን ለማወቅ ዘወትር ራሳችሁን መርምሩ።2 ቆሮንቶስ 13:5(አአት)
·         “ሁሉንም ነገር መርምሩ፤+ መልካም የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ። 22 ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ራቁ።+1” ተሰሎንቄ 5:21(አአት)
·         “መንገዳችንን እንመርምር፤ ደግሞም እንፈትን፤+ ከዚያም ወደ ይሖዋ እንመለስ።ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:40(አአት)
·         “አሁንም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘መንገዳችሁን ልብ በሉ።*ሐጌ 1:5(አአት)

የዚህም ጦማር አላማ ይሄዉ ነዉ፡፡ ይሆዋ ምስክሮችን እምነታቸዉን ለማስቀየር ወይም ሌላዉ ክርስትያን በይሆዋ ምስክሮች ላይ ጥላቻ እንዲኖረዉ ለማድረግ አይደለም፡፡ይሆዋ ምስክሮችን አስተምሮ እዉነታዎችን በማስረጃ በማቅረብ ይሆዋ ምስክሮችም ይሁኑ ሌሎች ክርስትያኖች አዉነታዉን እንዲረዱ መርዳት ነዉ፡፡
ይሆዋ ምስክሮች በሀይማኖታቸዉ ዉስጥ ብዙ መስዋእትነትን የሚከፈሉ ናቸዉ፡፡ብዙ ጊዜ እየዞሩ ከኣገር ኣገር በራሳቸዉ ወጪ ተቸጋግረዉ ያገለግላሉ፡፡በእምነቱ ዉስጥ እያሉ እንኳን ሰዉ በመሆናቸዉ በሚሰሩት ኣንዳንድ ስህተቶች  ከቤተሰቡቻቸዉ፣ከዎዳጆቻቸዉ፣ከሚወዱዋቸዉ መንፈሳዊ ጓደኞቻቸዉ የመገለልን እና የብቸኝነትን መስዋዕትነት ይከፈላሉ፡፡የዚህም ጦማር ኣንዱ አላማ ይሆዋ ምስክሮች ይህን ሁሉ መስዋእትነት የሚከፈሉለትን ሀይማኖታቸዉን በማስረጃ እንዲማረምሩ እና ሳይረፍድ በወጣትነታቸዉ ዘመን መንገዳቸዉን እንዲያዩ መርዳት ነዉ፡፡ ጦማሩም በተቻለዉ መጠን በአብዛገኛዉ ይሆዋ ምስክሮችን ጽሁፎችን ፣መጽሓፍ ቅዱስን እና ሌሎች ጽሁፎችን በማስረጃነት በመጠቀም ሚዛናዊ ማስረጃ ይሰጣል፡፡